>

"ዶክተር አብይ አህመድ የህዝብ ለውጥ መሪ እንጂ የኢሀዴግ መሪ አይደሉም"  (ዶ/ር ብራሃነመስቀል ሰኚ) 

እንድ እሳቸው አባባል ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከድርጅት መሪነት ወደ ሀገራዊ መሪነት በማምጣት ህዝባዊ ትግሉን የበለጠ አጉልቶታል ባይናቸው
እኚህ ሚኒስትር ምንም በፓርቲያችው ውስጥ ቢመረጡም ከህዝቡ በመጣው ግፊትና ጫና የተመረጡ በመሆናቸው በሀገሪቷ ዙሪ ካሉት ዜጎች ሀሳብና ፍላጎቶችን በቀጥታ ለመስማትና ድጋፍ ማሰባሰባቸው ሚኒስትሩ ቀደም ሲል የገቧቸውን ቃልኪዳን ለማክበርና ለሥራቸው ግባት በመሆን ይረዷቸዋል ይላሉ በሳቸው አነጋገር conditional building meager ባሉት ንግግራቸው ጣቅላይ ሚኒስትሩ የቀጣይ እርምጃቸው በአጠቃላ ሀገር ውስጥ ያሉትን የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት አፋኝ ህጎችን መሰረዝ አማራጭ የሚዲያ ህግችን ከልካይ ህግን ማንሳት የአስቸኳይ ጊዜውን አዋጅ ማንሳት የመሳሰሉት ነው ብለዋል::
ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቤተመንግስት እስክ ክልሎች ድረስ ለህዝቡ የገቧቸውን ቃላት ወዜማ በዝርዝር አንኳሮችን ለቅሞ አውጥቶ ነበር ያንን ለማስታወሻ ይሆን ዘንድ ከዶክተሩ ንግግር ጋር ለማዛመድ ይረዳ ዘንድ ለማያያዝ ተሞክሯል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እስካሁን ቃል ለገቡት ተግባር ማስፈፀሚያ የሚሆን ፍኖተ ካርታ ይፋ ባያደርጉም በንግግሮቻቸው ቁልፍ የፖሊሲ ጉዳዮችን አንስተዋል። ለክትትል እንዲመቻችሁ በዘርፍ በዘርፍ አሰናድተነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉትን ቃል በቃል መቼና የት እንደተናገሩት በዝርዝር እደሚከተለው ተቀምጧል።
ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር
“…ኢትዮጵያ እያደገች ያለች ሀገር ስለሆነች፣ ሁልጊዜ ለረዥም ጊዜ ጥቂት ሰዎችን ወንበር ላይ ማቆየት አትችልም የሚል ሀሳብ ስላለ ትምሕርት እንዲሆን… ኢሕአዴግ እንደ ድርጅት የወሰነው ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ያልገባ ስለሆነ፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የምናስገባው… ማንም የኢትዮጵያ መሪ ከአሁን በኋላ ከሁለት ተርም በላይ [በሕገ መንግሥት ጭምር] ማሰሪያ የሚደረግለት… የዕድሜ ልክ ሥልጣን ኢትዮጵያ ውስጥ ያበቃ መሆኑን፣ አሁን ላለነው፣ ለሚመጡት ለማስተማር ጭምር መሆኑን ግንዛቤ ቢወሰድ ጥሩ ነው”
(ሀዋሳ፣ ሚያዚያ 18 ቀን)
“…ለሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲ ሥርዓት መረጋገጥ ወሳኝ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት ተጠናክረው፣ ከወገንተኝነት ጸድተው፣ ሕዝባዊ ተዓማኒነታቸው እንዲጎለብት… መወሰድ ያለባቸውን ቁልፍ እርምጃዎች በጥናት ላይ ተመስርተን የምንወስድ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ”
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ውስጥ፣ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም መርህ፣ በመደማመጥ የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ መሆን አለበት፡፡ ኢትዮጵያ የጋራችን፣ የኛ የሁላችን መሆኗን ተገንዝበን የሁሉም ድምፅ የሚሰማበት፣ ሁላችንንም የሚያሳትፍ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመገንባቱን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ዴሞክራሲ ሲገነባ መንግሥት የዜጎችን ሃሳብ በነፃነት የመግለፅ መብት ማክበር አለበት፡፡ ዴሞክራሲን ከዜጎች ሠላማዊ እንቅስቃሴና ከመንግሥት መሪነት፣ ደጋፊነትና ሆደ ሰፊነት ውጪ ማዳበር አይቻልም። በመሆኑም መንግሥት የዜጎች ሠላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይስተጓገል በፅናት ይሰራል”
(ፓርላማ ፣መጋቢት 24 ቀን)
 “ድርጅታችን ኢሕአዴግ በሀገራችን ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የተለያዩ ሥራዎች ቢሰራም ከሚጠበቀው አንጻር ሂደቱም ሆነ ውጤቱ ምሉዕ አልነበረም፤ አካሄዳችን ከመርሃችንና ከንግግራችን ሳይጣጣም ለዲሞክራሲ ሥርዓት መጎልበት መሄድ የሚገባንን ርቀት አለመሄዳችን ግልጽ ቢሆንም ይሕንን አሉታዊ ገጽታ ለመንደርደር እንደ መዘጋጃ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን በሙሉ ኃይልና የአብሮነት መንፈስ ልንረባረብ ይገባል፡፡ ይሕንን መሰረታዊ ጉዳይ ዕውን ለማድረግም ኢሕአዴግ ራሱን ገምግሞ ችግሮቹን ከመለየት ባሻገር ከችግሩ ለመውጣት በሁሉም ደረጃ በሚገኙ አደረጃጀቶቹ የሪፎርምና የለውጥ ሥራዎች ማካሄድ ጀምሯል…”
(ቤተመንግስት፣ ሚያዝያ 3 ቀን)
 “…ሕግ ሁላችንንም እኩል የሚዳኝ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ሲሆን ሕግ በተፈጥሮ ያለንን ሰብዓዊ ክብራችንን ያስጠብቅልናል፡፡ ይህን እውነታ በመረዳት በሀገራችን ዲሞክራሲ እንዲያብብ፣ ነፃነትና ፍትህ እንዲሰፍን፣ የሕግ የበላይነት ዕውን እንዲሆን አስፈላጊውን ማሻሻያ በማድረግ በዘርፉ ያለውን ክፍተት እንሞላለን”
(ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
“…ታዳጊውን ዲሞክራሲያችንን ለማዳበር ተጨማሪ የሕይወትም ሆነ የአካል መስዋዕትነት አያስፈልገንም፡፡ ባለፉት ዓመታት እንደ መንግሥትም እንደ ዜጎችም ከዲሞክራሲ ባህላችን አለመዳበር ጋር ተያይዞ በታዩብን እጥረቶች በዜጎቻችን ህይወት እና በግልም በጋራም ንብረቶቻችን ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት ደርሷል። ይህንን ሁላችንም ማስቀረት እንችልና ይገባንም ነበር፡፡ በተለያየ ጊዜ፣ መስዋዕትነት ለከፈሉ የመብት ተከራካሪዎችና ፖለቲከኞች፤ በቅጡ ሳይቦርቁ ህይወታቸው ለተቀጠፈ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች፤ ለሥነ ልቦናዊና አካላዊ ቀውስ ለተዳረጉ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
“…እንዲሁም ሰላም ለማስከበርና ሕገመንግሥታዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሲንቀሳቀሱ ህይወታቸውን ላጡ የፀጥታ ኃይሎች አባላት ለከፈሉት መስዋዕትነት ያለኝን አድናቆትና አክብሮት ለመግለፅ እፈልጋለሁ፡፡ ለተፈጠሩ ችግሮች እልባት በማበጀት ህዝባችንን እንደምንክስም ጭምር በዚሁ አጋጣሚ ቃል እገባለሁ”
 (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
 “…ውጤታማ ባልሆነ የተንዛዛ ስብሰባ የሚባክን ጊዜና ንብረትን በመቀነስ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለሕዝብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት ተገቢውን ምላሽ የማይሰጥ የመንግስት ሠራተኛንም ሆነ ተቋም ተጠያቂ ለማድረግ የሚቻልበት አካሄድ በመዘርጋትና በማጠናከር ችግሩ የሚቀረፍበት ሁኔታ ለመቀየስ እንቅስቃሴ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እንግልት እንዳይኖር የሚያስችል መንግስታዊ አሰራር እንዲፈጠር ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ እንደምንሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ”
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
“…የዲሞክራሲ እውነተኛ ጥንካሬ መለኪያና አመላካች ተደርገው ትልቅ ትኩረት ከሚሰጣቸው መካከል የፍትሕ ሥርዓቱ ተቋማዊና ሙያዊ ብቃት ቀዳሚነት እንደሚይዙ ይታወቃል፡፡ የሕዝባችን ብሶት ምንጭ የሆኑት የፍትሕ አካላት ነጻነታቸውንና ሙያዊ ሥነ ምግባራዊ ብቃታቸውን ባረጋገጠ መንገድ እንዲሰሩ፣ በሕገ መንግስቱ መሰረት ተጠያቂ እንዲሆኑና የፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችሉ መፍትሔዎችን በመውሰድ አስፈላጊው ሁሉ ይደረጋል”
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
በሕግና መመሪያ ተከልሎ የሚደረግ አድሎና በደል በማቆም፣ በፍትሕ ሥርዓቱ ሕዝቡ እውነተኛ ዳኝነት የሚያገኝበት፣ የሕግ የበላይነት የሚረጋገጥበት፣ ሠብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩበት፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነት፣ ከጉቦ የጸዳ አገልግሎት የሚሰጥበት እንዲሆን አበክረን እንሰራለን” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
“…የመብት ጥሰት ብሶት ያስከተሉ፣ ለኢ ፍትሐዊ ምክንያት የሆኑ ሕጎችን ከሕዝብ በሚገኝ ግብዓት በመፈተሽ አስፈላጊው ማሻሻያ ይደረጋል” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
ከኢህአዴግ ውጪ ያሉ ፓርቲዎችን የምናይበት መነፅር እንደ ተቃዋሚ ሳይሆን እንደ ተፎካካሪ፣ እንደ ጠላት ሳይሆን እንደ ወንድም፣ አማራጭ ሃሳብ አለኝ ብሎ እንደመጣ አገሩን እንደሚወድ የዜጋ ስብስብ ነው። ስለዚህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ የተመቻቸና ፍትሃዊ የመወዳደሪያ ሜዳ እንዲኖር በመንግሥት በኩል ጽኑ ፍላጎት ያለ በመሆኑ ስለ ሠላምና ፍትህ በልዩ ልዩ መንገድ የምትታገሉ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች፣ አብሮነታችንንና ሠላማችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ፤ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንንም አሳልፈው የሚሰጡ የአስተሳሰብ መስመሮችን በአርቆ አስተዋይነትና ሀገራዊ ፍቅር፤ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተሻለ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት እንድታግዙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ”
(ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
ትርጉም ያለው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲጎለብት ኢሕአዴግ ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችም መጠናከር ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ተዓማኒነት ያለው፣ ፍትሐዊ በሆነ የመወዳደሪያ ሜዳ ላይ የሚከናወን፣ እውነተኛ ፉክክርና የሀሳብ ፍጭት የሚታይበት እንዲሆን ለማድረግ ከወዲሁ በቅንጅት እንደምንሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡”
 (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
ከተቀዋሚ ፓርቲዎች ጋ] ለፉክክር የሚመች ሜዳና ነጻነት እንዲኖር በማድረግ ለሀገራችን፣ ለሕዝባችንና ለድርጅታችንም የሚበጅ ፖለቲካዊ ዐውድ ለመፍጠር እተጋለን፤ ሌት ተቀን እንሰራለን …”(ቤተመንግስት፣ ሚያዝያ 3 ቀን)
“አሁን በጀመርነው አዲስ ምዕራፍ፣ ዘረፋን፣ የሀብት ብክነትን እና የተደራጀ ሙስናን፣ መላው ህዝባችንን በሚያሳትፍ እርምጃ ለመመከት ሌት ተቀን እንተጋለን”
 (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
በግብርናው ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት፣ በረሃዎቻችንን ወደ ገነት ለመቀየር የመስኖ ልማት ሥራዎችን በስፋትና በተቀናጀ መልኩ በመተግበር፣ የአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎችን፣ የታዳጊ ክልሎች ላይ ሠፊ ኢንቨስትመንት በማካሄድ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተገቢውን ትኩረት ሠጥተን እንሰራለን”
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
ጉቦና የጥቅም ሽርክና፣ ዝምድናና አድሏዊ አሰራር ጎጂ ባሕል መሆኑን አውቆ፣ ሙያውን አክብሮ፣ ለኃላፊነቱ ክብር ሠጥቶ የሚያገለግል የመንግስት ሠራተኛና አመራር እንዲፈጠር ከመንግስት በኩል ጽኑ ፍላጎት ያለ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ይሕን ለማሳካትም ከሚወሰዱ እርምጃዎች መካከል በዋናነት በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚደረግ ምደባ በዕውቀት፣ ክሕሎትና ችሎታ… ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛ ቦታ እንዲሰማራ በማድረግ የመንግስትን የማስፈጸም ብቃት እናሻሽላለን”
 (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
“…ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውጪ ምንዛሪ እጥረት የንግድ እንቅስቃሴ እንዲዳከም፣ መዋዕለ ነዋይ በሚያፈሱ ባለሀብቶች መካከል መተማመን እንዲቀንስ፣ የዋጋ ንረት እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኗል፤ በአሁኑ ወቅት በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በስፋት እንደ መሰማራታችን መጠን የውጪ ምንዛሪ እጥረት ማጋጠሙ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ችግሩ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይወጣና ከሥር መሰረቱ እንዲቀረፍ አስተማማኝ የሆነ የገቢና ውጪ ንግድ ሥርዓት እንዲሰፍን የግብርናና ማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በጥራትና በብዛት ወደ ውጪ ለመላክ በትጋት የምንሰራ ይሆናል”
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
…እኛ የትውስት አመራሮች ስለሆንን ባለሀብት መፍጠር፣ ሀገር መቀየርና መልቀቅ ነው፤ ምናልባት ከእኛ መካከል [ከመንግስት ሹማምንት] “የሀብታሞች ኑሮ ያማለላችሁ ካላችሁና ሀብታም መሆን የምትፈልጉ ካላችሁ ይቻላል፤ ግን ለቃችሁ በዚያኛው ወገን ተሰለፉ” ተባብለናል
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
“በእኛ በኩል የምናስተካክላቸው በጣም በርካታ ነገሮች አሉ፤ የብላክ ማርኬት መናኸሪያ እዚህ ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ መሆኑን እያወቅን ዝም ብለን ያየንበት መንገድ ይቀየራል፡፡ የኮንትሮባንድ ማከማቻዎች ጉዳይም ይቀየራል”
(ሸራተን ሆቴል ፣ሚያዚያ 8 ቀን)
“…አሁን የውጪ ምንዛሪ ችግር አለ ብቻ ሳይሆን ብዙዎቻችሁን መጠየቅ የምፈልገው ዱባይና ቻይና ያስቀመጣችሁትን እንድትመልሱ ነው፤ እንደ መንግሥት ሳይሆን እንደ አገር ችግር አለብን፤ ውጪ ምንዛሪን በተመለከተ ሀገር ችግር ላይ ነው ያለችው፤ እናንተ ግን ከዘመድም ከአዝማድም፣ ከተቀመጠውም በከፍተኛ ደረጃ እንድትመልሱ እጠይቃለሁ፤ እንድትመልሱ ስል ያው ይገባችኋል፤ ችግር ውስጥ ነው ያለነው አግዙን፤ ብሩን ስጡን ሳይሆን መልሱት፤ አሁን ካገዛችሁን ያኔ አግዘን ነበር ብላችሁ ደግሞ አንድ ቀን ትጠይቃላችሁ፤ እናንተ ችግር ሲሆን ጠይቃችሁ፣ እኛ ስንቸገር አለን የማትሉን ከሆነ ይኼ መልካም ጉርብትናም ዝምድናም አይደለም፡፡ አንዱ አንዱ ላይ አድቫንቴጅ እየመታ ስለሚሄድ እኛንም ችግሩን ለመፍታት አያነቃቃንም፤… የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ችግር ተረባርበን ካልፈታነው አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ የምናደርገውን ከተሰራ በኋላ ብናገር ይሻላል”
(ሸራተን ሆቴል ፣ሚያዚያ 8 ቀን)
የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል አለመኖር ፣ ሥር የሰደደ ድህነት ፣ የተደራጀ የሙስና እና ብልሹ አሰራር መስፋፋት፣ የመልካም አስተዳደር እጦት ተደማምረው ሰፊና ውስብስብ ፈተና ደቅነውብናል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ ወገኖቻችን ከመኖሪያ ቀዬአቸው ለመፈናቀል፣ ለህይወት እና ንብረት መጥፋት ተዳርገው እንደነበር ይታወሳል። ዜጎች በአገራቸው ውስጥ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር እና ሃብት የማፍራት መብታቸው መከበር አለበት፡፡ በመሆኑም እንደዚህ አይነት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እንዲያበቃና ዳግም እንዳይፈጠር መሥራት ይኖርብናል”
 (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
ከሁሉ በላይ ከዚህ የተፈናቀሉ… ከዚያ የተፈናቀሉ ሰዎች ለሁላችን ቁስል፣ ለሁላችን አሳዛኝ… ድጋሚ መስማት የማንፈልገው ክስተት መሆኑን አምነን ባለን አቅም ሁሉ ተረባርበን ወደነበሩበበት እንዲመለሱ፣ ከሕዝባቸው ጋር እንዲታረቁ፣ የትናንትናውን ታሪክ በፍቅርና በአዳዲስ ድል እንዲቀይሩ የፌደራል መንግስት ከሁለቱ ክልሎች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ”
 (ጅግጅጋ፣ መጋቢት 28 ቀን)
የጸጥታና የደሕንነት ተቋማት ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዱ፣ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን እና የሀገር ሉዓላዊነት የሚያስብጠቁ፣ የሀገር ኩራትና መመኪያ ሆነው እንዲቀጥሉ በቅርበት እንሰራለን”
የውጪ ግንኙነት
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
“… ከኤርትራ መንግሥት ጋር ለዓመታት ሰፍኖ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃም ከልብ እንፈልጋለን። የበኩላችንንም እንወጣለን፡፡ በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገር ህዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችንን በውይይት ለመፍታት ያለንን ዝግጁነት እየገለፅኩ የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ አቋም እንዲወስድ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ”
(ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
 “…የትምህርት መስፋፋት ይበል የሚያሰኝ የመንግሥታችን ስኬት ቢሆንም ይህ የትምህርት ሽፋን ዕድገት በጥራት እስካልተደገፈ ድረስ ልፋት ጥረታችን ሁሉ የምንተጋለትን ውጤት ሊያመጣልን አይችልም። በመሆኑም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉትን የእውቀት አለሞቻችንን በጥራት ላይ አትኩረው እንዲሰሩ መንግሥት በፍጹም ቁርጠኝነት ይረባረባል”
(ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
“…ኢትዮጵያ ለወጣቶቿ ተስፋ የምትሰጥ እንጂ፣ ተስፋ የምታስቆርጥ አገር እንዳትሆን የምንችለውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ፡፡ በሚቀጥሉት ጊዜያት ለወጣቱ የሥራ ዕድል መፍጠር ብቻ ሳይሆን ወጣት ባለሀብቶች በብዛት እንዲፈጠሩ እንሰራለን፡፡ ለዚህ እንቅፋትና መሰናክል የሚሆኑ አመለካከቶችና የተንዛዙ አድሏዊ የሆኑ አሰራሮችን አስወግደን ፍትሃዊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት እንዲኖረን መንግሥት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
“…መንግሥታችን ከዚህ ቀደም ከነበረው ፍጥነት እና የትግበራ ስኬት በላቀ መልኩ ለሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት ይሰራል።” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
…ሥራ አጥነት ወጣቶቻችንን ለወንጀል፣ በሱስ ለመጠመድ እንዲሁም ለስደት ሲዳርግ ተስተውሏል፡፡ ይሕንን ሁኔታ ለመቀየር መንግስት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ”
(ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
“…ለሁላችንም የምትበቃ በዚያው ልክ ግን የሁላችንንም ተሳትፎ የምትፈልግ ሀገር አለችንና ዕውቀታችሁንና ልምዳችሁን ይዛችሁ ወደሀገራችሁ መመለስና ሀገራችሁን አልምታችሁ መልማት ለምትሹ ሁሉ እጃችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን፡፡ በውጪ ሀገራት ኑሯችሁን ላደረጋችሁትም ቢሆን በማንኛውም መልኩ በሀገራችሁ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑና ሀገራችንን በሁሉም መልክ ለመቀየር ለምታደርጉት አስተዋጽኦ መንግሥት ያልተቆጠበ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል”
(ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)
…መንግስት የሕዝባችንን ሁሉን አቀፍ ጥንካሬ መሰረት በማድረግና የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ሀገራዊ አንድነታችንን ይበልጥ ለማጎልበት በጽናት እንደሚሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)
ባለፈው አንድ ወር : ጠሚር አብይ እስካሁን ያደረጓቸው ንግግሮች ከበቂ በላይ አንድነትን የሚያጎለብቱና ቅን ናቸው። ይህን ቅን ሀሳብ ከስሜት በዘለለ በየደረጃው ለማስፈፀም የሚረዳ ስትራቴጂና ግብ አልተቀመጠም። ከገዥው ፓርቲ ርዕዮተ አለም ጋርስ እንዴት እንደሚጣጣም መፈተሽ አለበት። ምንጭ ዋዜማ
Filed in: Amharic