>

ለኦሮሞ የግእዝ ፊደላት ከላቲኑ ይልቅ ሀሳብን በቀላል ሁኔታ ይገልፃሉ- ዸ ዺ ዻ ዼ ዽ ዾ ዿ ዿ

ከሚሊዮን አየለች
 ሀሳቡ ግዙፍና ጥልቅ ቢሆንም ለዚህ ገፅ እንደሚመጥን አድርጌ  ከላቲን ይልቅ የግህዝ ፊደላት ለኦሮሚኛ ቋንቋ  እንዴት  የተመቸ እንደሆነ ለማሳየት እሞክራለሁ ፡፡
የግእዝ ቋንቋና ፊደላትን አሁን ላለው ላበዛኛው በተለይም ፅንፈኛ ለሆኑት የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚቀበሉት አይደለሙ ያም ቢሆን እውነታውን ተረድተው የቅድመ አባቶቻቸውን ታሪክ ላይ ሊንተራሱ የጠገባ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
 ግዕዝ ማለት ምን ማለት ነው 
 ግዕዝ  በብዙ ሊቃውንት እና ተመራማሪያን ቋንቋው ከ3000 ዓመት በፊት የነበረና ሰዎች እንደሚጠቀሙበት መነሻውንም ያገኘው  ጋዛ ከሚለው አጋዚን ከሚባሉት ሰዎች ነው  በማለት ያስቀምጡታል ይህ  ፍረጃ  ብዙ ታማኝነት ባይኖረውም በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ተብሎ ከ4000 ዓመት በፊት በንጉስ  ኢትዮጵ  አማካኝነት ኢትዮጵያኖች ይጠቀሙበት እንደነበረና የመንግስትና የሕዝብ ቋንቋ እንደነበረ  አያሌ ማረጋገጫዎች ያመለክቱናል ፡፡
ይህም ለተለያዩ አማካኝነት ኢትዮጵያዊያ ሊቃውንቶች የከተቧቸው  ጽሁፎችና የአይማኖት ጽሁፎችን  እንደ አባይ ማስረጃ አድርገው ያቀርቡልናል ፡፡
 ግዕዝ በሀይማኖት እይታ 
ግዕዝ ማለት  የመጀመሪያ ቀዳሚ ቋንቋ ከመፈጠሩ በፊት መላእክቶች  ይግባቡበት  የነበረ ልእለ ሀያል የሆነ ቋንቋ ነው ፡፡ግዕዝ ወገን የለውም  የዚህ አካል የነዚያ ቋንቋ ተብሎ  አይፈረጅም በአብዛኛው ቋንቋዎች ወገንተኛ ናቸው  ከስያሚያቸው  በመነሳት የእከሌ በማለት ስያማቸውን  ልናስቀምጥ እንችላለን ፡፡ ለምሳሌ  በጽርህ የጽር ቋንቋ በሮም ሮማይስጥ  በኢቦር (ኢብሩ) ዕብራይስጥ  በሀረብ ሀረብ  ከእንግሊዝ እንግሊዘኛ እንዲና የመሳሰሉትን እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል ፡፡
የግዕዝ ቋንቋና ፊደላት ከዝነዚህ ተለይቶ  ይሄ ነው ልንለው  አንችልም  ግዕዝ ማለት አጋዚ – እግዚአብሔር በማለት ወገንተኝነቱን  ከሀለሙ ፈጣሪ ከእግዚአብሔር ጋር ያደርጋል ፡፡
 በተመራማሪዎችም እና በሀይማኖትም በኩል በግዕዝ ቋንቋ ምንነትና አመጣጥ  የተሰጠው ትንተና  የግዕዝ ፊደላት ቀደምት መሆኑን ያረጋግጥልናል ፡፡ይህ ቀደምት የሆነ ቋንቋ  ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ፊደሎች እንደ እናት ሆኖ አያገለገለ ያለ ቋንቋ ነው ከግዕዝ ፈደላት ውስጥ ገዝፈው  ከወጡት ቋንቋዎች መካከል  አማሪኛና ትግሪኛ በአባይት  ማሳያነት ልንመለከታቸው እንችላለን ፡፡ የአማሪኛና የትግሪኛ ቋንቋዎች በአብዛኛው የተጠቀሙት የግዕዝ ፊደላት ነው ፡፡ የግዕዝ ፊደላትን በራሳቸው ቋንቋ ቅላፅ  እንዲሆንና ጥቂት ማሻሻያ አድርገውበት በግዕዝ ፊደላት ውስጥ በአማሪኛውም በትግሪኛውም ቋንቋ ቅላፅ የሌሉትን  በመጨመርና ፊደላቱን ተጠቅመውበታል ፡፡
ኦሮሚኛ ቀድሞ ይጠቀሙበት የነበረ ፊደል  ምንድን ነው
የኦሮሚኛ ቋንቋ  እነደማንኛውም ሀገራችን ውስጥ እንዳሉት አያሌ ቋንቋዎች መካከል ከብዙ ሺህ ዓመት በፊት ይነገርበት የነበረ  የራሱ ስነ ቃል ፣የራሱ ተረቶች ያሉት  ግዙፍና ትልቅ ቋንቋ ነው ፡፡ይህ በብዙ ሺህ ዓመት እየተነገረበት ያለ ቋንቋ  ይጠቀምበት የነበረበት ፊደል ምን ነበረ ፊደል ምን ነበረ ብሎ መጠየቅ ተገቢም አስፈላጊም ነው ፡፡
 ኦሮሚኛ ቋንቋ በቅርብ ጊዜ  በላቲኑ ቋንቋ ከመፃፉ በፊት ይጠቀምበት የነበረው በግዕዙ ቋንቋ ነበር እዚህ ላይ እንደማስረጃ  አርጊ ለማንሳት ፍሮፌሰር  ፍቅሬ ቶሎሳ‹‹የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ ››  ብለው ካጠናከሩት  መፃፍቸው ውስጥ በገፅ 100 ላይ የጠቀሱት አናሲሞስ ነሲቦ አውሮፓ ተምሮ ከመጣ በኃላ  መፃፍ ቅዱስን  በግዕዝ ፊደላት  ወደ ኦሮሚኛ ተርጉሞታል እንግዲህ እዚጋ ልብ ሊባል የሚገባው  አናሲሞስ ነሲቡ እውቀትን የቀመሰው  አውሮፓ ሄዶ ነው ነገር ግን ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲመጡ ቋንቋውን  ከመቀየር ይልቅ ግዙፉን መጽሐፍቅዱስ አንድ በአንድ  በግዕዝ ቋንቋ ወደ ኦሮሚኛ ቋንቋ  ተርጉሞታል ይህ የሚያመለክተው የኦሮሚኛ ቋንቋ ፊደላት  ቀደም ብለው በግዕዝ እንደሚፃፍና ታላላቅ የኦሮሞ  ሊቃውንት  ጽሁፋቸውን በግዕዝ ፊደል በኦሮሚኛ እንደከተቡ ነው ፡፡
የላቲኑ ፊደል እንዴት ለኦሮሚኛ  መጠቀሚያ ሆነ  
እዚህ ላይ  ሁለት አሳቦችን ማንሳት የሚቻል ነው የላቲን ፊደላት ወደ ኦሮሚኛ ዘልቀው የገቡትና  የኦሮሚኛ ፊደል  ቀድሞ ይጠቀምበት የነበረው የግዕዝ ፈደላት  የቅርፅና የባህል ፣የታሪክ ለውጥ አድርጎ  በላቲን መፃፍ የጀመረው በሁለት  መልኩ ነው
1.  በኢትዮጵያ ውስጥ  ይመላለሱት የነበሩት  ሚሶናውያን የያዙትን  መፅሀፍ  ቅድስ  በየ ቦታው  ዞረው ለማስተማርና ከብዙ ቋንቋና ባህል ጋር ለመተዋወቅ ሲሉ የኢትዮጵያን ሀገር ቋንቋዎች እራሳቸው እንደሚገባቸውና ለማንበብ አንደሚመቻቸው ብለው በራሳቸው ቋንቋ በለሰቲን እየከተቡ ቋንቋውን ያጠኑ ነበር በዚኽም  በየሄዱበት ሁሉ ቋንቋን በራሳቸው  ፊደል እየገለበጡ ህዝቡን ያስተምሩት ነበር ከእነዚዘኛ ኢትዮጵየውን ህዝቦችም መካከል የኦሮሞ ክልል ይገኝበታል በዚኸ ክልል ውስጥም  ማስዮናውያን  ቋንቋውን  ወደ ራሳቸው ፊደል ለውጠው የመፃፍ ቅዱስን ትምህርት ለህዝቡ  ያስተምሩ ነበር በዛሽ ትምህርት ውስጥ  ከሰሩት መካከል የቀድሞ የፖለቲካ ሰው የነበረው በመንገስት ሀይለ ማርያም ጊዜ  በፖለቲካ  አመለካከቱ ህይወቱ ያጣው ሀይሊ ፋዳ እና ሌሎችመረ  ኢትዮጵያን ይገኙበት ነበር ፡፡
2. በሁለተኛ ደረጃ የላቲን ፊደል  በኦሮሚኛ ቋንቋ እንዲሆን  አድርገው የቀመሙት ግዕዙን ከቤተክርስቲያን ከኦርቶዶክስ ሀይማኖት ጋር በማስተሳሰርና የኦርቶዶክስ ሀይማኖትን ደግሞ የአማራ ሀይማኖት ለማድረግ ለአማራ ያላቸውን ጥላቻ ሊገልዮበት ከዛሬ 35ዓመት ጀምሮ በነሊጮ ላታና በወዳጆቻቸው  አተገባበሪነት  የተሰላ ስሌት ነው ፡፡በመሰረቱ የአማሪኛ ፊደል ከግዕዝ ወጣ እንጂ ግዕዝ የአማራ አይደለም  አስቀድመን ከላይ የተመለከትነውን የግዕዝ ፊደላት ለአያሌ ኢትዮጵያውያን  ቋንቋ መሰረት የሆነና ቡዙ የኢትየጵያ ቋንቋዎች የግዕዝ  ፊደላትን  እንደሚጠቀሙ በላዩም ግዕዝ  ወገንተኛ አለመሆኑና የእከሌ ቋንቋ ብቻ  አለመባሉን ነው ሊሎች ቋንቋዎች ሁሉ ወገን አሏቸው የራስ ክልል  የዚኸ ሀገር  ሊያሰኛቸው የማይል ስመ ስያሜ ይዘው ነው  የተሰሩት ግዕዝ ግን ከገዛኽ ለየት ባሉ ወገናዊ አይደለም
በኦርቶዶክስ  ሀይማኖት ውስጥ አያሌ የኦሮሞ  ሊቃውንት ጥንትም አሁንም ድረስ የግዕዝን ቋንቋን አቆላጥፈው የመናገርና በግዕዝ ቅኒ የሚቀኙ ታላላቅ ሊቃውንት ይገኙበታል  እንደማሳያ ለማንሳት በኢጣሊያ ወረራ ጊዜ  ህዝቡንም መሬቱንም  ለኢጣሊያ እንዳይገብሩ  ገዝተው  በስማዕትነት ያረፉት ኢትዮጵያዊው ጳጳስ አቡነ  ጴጥሮስ ትውልዳቸው ከፍቼ ሰላሌ መሆኑ ልብ ይለዋል  የደብረ ሊባኖስ  መነኩሳት በአቡዛኛው የኦሮሞ ሊቃውንት  ስለመሆናቸው  ነጋሪ የማያሻም ሀቅ ነው  ይህ እንደዚህ እንዳለ  ሀይማኖቱን ለአነድ ወገን ሰጥቶ የራሱን ቅድመ አባቶቻችን የሆኑትን ታላላቅ ታሪክኮች የግዕዝን ፊደላት ከአንድ ወገን ጋር ማላከክ ተገቢም  ትክክለኛም ውሳኔ አይደለም የቀደሙት አባቶቻቸው ይጠቀሙበት የነበረው በዚሁ የግዕዝ ፊደል ነውና ዛሬ ልጆቻቸው የሆንን እኛም ለኦሮሞ ለሱማሌውም ለሌሎችም ክልሎችከውጪ ከመጣ መጤ ቋንቋ ይልቅ አባቶቻችን  ከአለም አስቀድመው በደረሱ ወገን አልባ ፊደል ብንጠቀም የአንድን ቋንቋ ለለኛው  ለመልመድ በቀላሉ  ለማንበብም ይረዳዋል ፡፡
 የኦሮምኛ ፊደል የግዕዝን ፊደል ያለመጠቀም ለሊላኛው ምክንያት 
በኦሮምኛ ቋንቋ ውስጥ 10 አናባቢ  ሆኔያት ሲኖሩት በግዕዙ ፊደላት ግን  7አናባቢ ቡቻ  ናቸው ያሉት በኦሮሚኛ የቋንቋ  ቅላፂ ውስጥ የሚጠቀምባቸው  ቀደምት  ምላስን  ብትናጋ ጋር  በማገናኘት የሚወጣው ዸ ዺ ዻ ዼ ዽ ዾ የሚመስል  ፊደል ነገር ግን ድምፅ ሌላ የሆነ  ቃል አለ ይህንን ቃል በግዕዙ ውስጥ ማግኘት አይችልም  የሚለው ሁነኛ  መከራከሪያ  አድርገው ይይዙታል በዚህ በኩል  እኔ እስከማውቀው በእኔ እንኳን የዕድሜ ደረጃ  ላይ የደረስኩባቸው የአማሪኛና የግዕዝ ፊደላት የዚህን ፊደል በትክክል አስቀምጠዋቸዋል ፡፡
ዸ ዺ ዻ ዼ ዽ ዾ አይነት ምልክት ያለው በአማርኛም በግዕዝም የድምጽ ቅላፅ ውስጥ የሌለ ነገር ግን የኦሮሚኛ ቋንቋ  ተናጋሪዎች ብቻ የሚጠቀሙበት የነበረ ሆኔ ነው በዚህም ምልክት በኦሮሚኛ የሚፃፉት በዻ ዻ  እና የመሳሰሉት  ስሞችንም ቃላቶችንም መፃፍ የሚችል በመሆኑ  ቋንቋውን ከፖለቲካ  ጥላቻ ነፃ አድርገው  በቀላሉ ሌሎች የማህበረሰቡ  ክፍሎችም የሚሊዮን  ህዝብ ቁጥር  ያለው ብሄር ቋንቋ እንዲረዱትና  በቀላሉ  እንዲለምዱት ማድረግ ይቻላል ሆኖም የኦሮሞ ተወላጆችም የራሳቸውን  የጥንቱነ  ቋንቐዋቻን ከመጤ  ቋንቋ ለይተው መፃፍ አስችሏቸዋል ፡፡
 ቋንቋ የሚወራረሰው  አንድ በባህል ተፅህኖ ስር ሲወድቅና  በቀኝ ግዛት ውስጥ  ሲንበረከክ በቋንቋና በፊደል መበረዝ  በህዝብ ውስጥ ያመጣባቸዋል ምስጋና ለቀደምት ለኦሮሞ ሌሎችም  ኢትዮጵያዊያን ቤሄሮች ይሁንና የዚህን አይነት ግዛት እንዳንገዛ በተቀናጀ ሁኔታ አጥንታቸውን ከስክሰውና ደማቸውን አፍስሰው  የታፈረችና የተከበረችዋን  ኢትዮጵያን ትተውልን አልፈዋል ፡፡
( ምንም እንካ በአሁኑ ዘመን አሳፋሪ ትውልዶች ሆነን በመንፈስ የተገዛን ብንሆንም )ታዲያ የኦሮሞ ህዝብ ከእንደዚህ የባህል ተፅህኖ ነፃ ሆኖ የኖረ በቀኝ ግዛትነት ማንም ያልደፈረው የአንዲቷ  ኢትዮጵያ  ክፍል ሆኖ ሳለ እንዴት የማይሆንና መጤ በሆነ የውጪ ቃላት ሊጠቀም ይችላል ፡፡ ይህ አይነቱ ድርጊት የራስን ክብር አሳልፎ መስጠት በራስ ፍቃድ በቀኝ ግዛት ተገዝተናል ብሎ ከማመንም ይመነጫል ፡፡ አሁን ላይ እየተጠቀምንበት ያለው የኦሮሚኛ የላቲን ፊደላት በጥቅሉ ለማንበብም  ለመፃፍም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው አንድ ምሳሌ ላንሳ 
‹‹ በአንድ ወቅት አንድ አካባቢ ሄድኩና የኦሮሚኛ ተናጋሪዎች ስላሉበት እና በአብዛኛው በኦሮሚኛ ቋንቋ ስለሚሰራ  የንግድ ቤት ማስታወቂያውን በአማሪኛና በኦሮሚኛ እንዲጽፍ ይገደዳል ይህ ወዳጄ የኦሮሚኛ ተናጋሪ ነው ነገር ግን የኦሮሚኛ ቋንቋውን መፃፍ ስለማይችል ኦሮሚኛ ትርጉም ወደ ሚፃፍበት ይሄድና የአማሪኛውን ወደ ኦሮሚኛ   አስተርጉሞ ያጽፍና በባነር ያሰራና የንግድ ቤቱ ላይ ይለጥፈዋል ይህን ያዩት  የዘርፉ ሰራተኞች ኦሮሚኛ በትክክል አልተፃፈምና አውርድ ተብሎ እንደገና አፅፎ አሰቀለ ›› ይህ አይነቱ አሰራር ኦሮሚኛ ቋንቋን የሚናገርሩት እንኳን  ፊደሉን በአግባቡ መጻፍ ስለማይችል እንዲሁም በትክክል አልፃፉም ስለተባለ ለባለ ንብረቱ የጊዜም የገንዘብም  እጦት አጋጠመው ፡፡ ፊደላቱ በግዕዝ ዋናው በሆነና እያንዳንዱ ቃላት የየራሳቸው  ወካይ ስለሚኖራቸው  ለሁሉም ፊደላት አናባቢ ማስገባት ስለማይጠበቅ  ማንም ሰው በቀላሉ ተረድተው ሊጽፍ ይችለዋል ፡፡ ለዚህም  ሁሉም የህብረተሰብ አካል ቋንቋውን በቀላሉ ለምዶ ህዝብ ለህዝብ ያለውን   ግንኙነት የመለጠ የተሳለጠ ይሆናል ፡፡
የኦሮሚኛን ቋንቋ በላቲን ሲፃፍ  እጅግ በጣም ጊዜና ብዙ ገንዘብ ይወስዳል  ቋንቋው በላቲን ሲፃፍ ብዙ የሚደጋግማቸው ሆሄያት ሲኖሩት ለግዕዙ ግን እያንዳንዱ ፊደላት የራሱ ወካይ ፈደላት አላቸው ፡፡ ለምሳሌ 
Oromoo   ኦሮሞ  
Seenaa  ሲና
Ilmoon  አልማን
እኘህንና የመሳሰሉትን ቃላቶች በላቲን ሲፃፉ በጣም ብዙ ፊደላት የሚፈልጉ  ሲሆኑ በግዕዝ ፊደላት ሲፃፍ ሁሉም እያንዳንዳቸው እራሳቸውን የሚወክሉ አሏቸው  በላዩም አማሪኛ የማይጠቀምባቸውን  ቨ ፐ እና መሳሰሉትን ፊደላት መጠቀም የሚያስችል ይሆናል በመሆኑም  በብዙ ምክንያቶች የኦሮሚኛ ፊደላት ብዙውን ፊደላት ቢጠቀም አዋጪም ይሆንለታል ፡፡
1. ኦሮሞ ቋንቋእንደ አማሪኛ ሁሉ የፌደራል ቋንቋ ሆኖ ለማገልገል የኢትዮጵ ሕዝቦች  በቀላሉ  ቋንቋውን እንዲያውቁትና እንዲረዱት  መዘጋጀት ይሆርበታል፡፡
2. የላኛው ጊዜንም ገንዘብንም ይቆጥብልናል  በላቲኑ ፊደል ሙሉ ሉክ የምንጽፈውን  ጽሁፍ በግዕዙ ፊደል ከእሩብ ሉክ በታች በመፃፍ በኦሮሚኛ የሚታተሙትን መጻህፍት ጋዜጦችንና መጽሄቶችን በቀላሉና በትንሹ ዋጋ በማተም ለህዝቡ ተደራሽነት ማድረግ ይቻላል ፡፡
በመጨረሻም  በማወቅም ባለማወቅም በዘርና በብሄር ጥላቻ ላይ ተጥዳቹ ገናና የነበረውን ታሪክ አበላሽታችሁ ትውልድን የበረዛችሁ የኦረሞ ምሁራን ነን ባዮች በህይወት ያላችሁ ህዝቡን ወደ ትክክለኛውን ኢትዮጵያዊ መንፈስ ቆማችሁ ይቅርታ ልትጠይቁ ይገባል ያጠፋችሁትን ጥፋት መልሳችሁ ወደ ትክክለኛው መስመር በማምጣት ልትክሱት ይገባል፡፡
ቸር ይቆየን 
ሚሊዮን አየለች 
Filed in: Amharic