>
5:01 pm - Wednesday December 2, 3542

ሂዱና ሞክሩት!!! (ስዩም ተሾመ)

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርስ ስምምነትን ለመቀበል መወሰኑን በመቃወም #ዓረና_ፓርቲ በመቃወም በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች #ትላልቅ ህዝባዊ ስብሰባዎች እና የተቃውሞ ሰልፎች እንደሚጠራ አስተውቋል፡፡ መልካም እንግዲህ ዓረና ፓርቲ በታላቋ መቀለ ከተማ በጠራው “ታላቅ” ሰላማዊ ሰልፍ 7 ሰዎች ብቻ ሮማናት አደባባይ መውጣታቸው ይታወሳል፡፡ አሁንም ድርጅቱ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች እጠራለሁ ባለው ህዝባዊ ሰብሰባና የተቃውሞ ሰልፎች፣ ከዓረና ፓርቲ ሊቀመንበር እስከ ፀሃፊ ያሉት ተጠራርተው ቢወጡ እንኳን በድምሩ 27 የሚሞሉ አይመስለኝም፡፡ እሺ ይህን ፅሁፍ በማውጣቴ አንዳንድ የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ዓረና በጠራው ስብስባና ሰልፍ ሊሳተፉ ይችላሉ በሚል ቁጥሩን ወደ 47 ከፍ እናድርገው፡፡ እንዲህ ፈስ ተጠብሶ 47 ሰዎች ለስብሰባና ተቃውሞ አደባባይ ከወጡ በኋላ “ለምን ወጣችሁ?” ሲባል ምን ብለው ይመልሳሉ? “የነፍስ አባታችን መለስ ዜናዊ የፈረመውን የሰላም ስምምነት ለመቃወም!” የእኛ መልስ ምን የሚሆን የመስላችኋል? “መልካም ከኤርትራ ጋር ጦርነት ነው የፈለጋችሁት? ዳይ… ሂዱና ተዋጉ!! አንድ የኦሮሞ፥ የአማራ አሊያም የሲዳሞ ልጅ ከእናንተ ጎን ቆሞ ይዋጋል ብላችሁ ከሆነ ሲያምራችሁ ይቅር! “እዛው እንደፍጥርጥራቸሁ!” የሚል ነው፡፡ ኢትዮጲያ የእናንተን “Inferiority Complex” ለማባበል ሰላምና ልጆቿን የምታጣበት ምክንያት የለም፡፡ እንደውም የምን ህዝባዊ ስብሰባ እና ተቃውሞ ሰልፍ ነው?! ባድመ ሆነ ኤርትራ እዚያው አጠገባችሁ አይደል? ዳይ! ሂዱና #ባድመ ላይ ዘብ ቁሙ! ልብና አቅም ካላችሁ ደግሞ አስመራ ድረስ ዝለቁ!!

Filed in: Amharic