>
5:13 pm - Friday April 18, 4842

እንኳን የኢሮብ ወረዳ ህዝብ የኢትዮጲያም ህዝብ ለሁለት ተከፍሏል!! (ስዩም ተሾመ)

#EBC <<በትግራይ ክልል #የኢሮብ_ወረዳ ነዋሪዎች መንግስት ለተግባራዊነቱ ይሁንታ የሰጠው #የአልጀርሱን ስምምንት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡ ስምምነቱ የኢሮብን ህዝብ ለሁለት የሚከፍል በመሆኑ በፅኑ እንደሚቃወሙት መግለፃቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላም ሀጎስ በተለይ #ለኢቢሲ ገልፀዋል>> በማለት ዘግቧል፡፡ እንኳን የኢሮብ ህዝብ የኢትዮጲያም ለሁለት ተከፍሏል! ደግሞ እኮ የኢሮብ ሆነ የኢትዮጲያን ህዝብ ለሁለት የከፈሉት ከእናተው መሃከል የወጡት #መለስ_ዜናዊ እና #ስዩም_መስፍን ናቸው፡፡ ስለዚህ ከፈለጋችሁ የመለስን አፅም፣ የስዩም ስጋ እንደ ችቦ ማቃጠል ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን፣ የኢትዮጲያ ህዝብ ለሁለት ሲከፈል በደስታ ያጨበጨቡ የኢሮብ ህዝብ ለሁለት ሊከፈል ነው ብለው ቢንጨረጨሩ የሚሰማቸው የለም፡፡ ያው መንገዱ ከፍት ነው፡፡ በፎቶ እንደሚታየው በሰልፍ ሄዳችሁና የኤርትራን ጦር መግጠም ትችላላቸሁ፡፡ ይህን ስታደርጉ ግን አጠገባችሁ ገላጋይ እንደማይኖር ልብ በሉ፡፡ በእናንተ ጦስ ስንት አመት እንለብለብ? ዳይ… ሂዱና ግጠሙ!!
Filed in: Amharic