>
5:13 pm - Sunday April 19, 4274

አደራህን እንዳይሞቱብን ?!? (አዳም መኮንን)

ሳያቸው ያሳዝኑኛል፣ ውስጤን ይበሉታል፣ ውለታቸውን ውሀ በላው፣ ልፋታቸው ገደል ገባ፣ እሳትና ጭድ ሳይቀጣጠሉ ቀሩ፣ ስንት የደከሙበት ከሸፈ፣ የከፍታ ያሉት ዘመን ዳገቱን ካቅማቸው በላይ በአሸዋ ገንብተውት ተንዶ ቁልቁል አወረዳቸው፣በቃ ለፍተው ለፍተው የባለ ራዕዩንም የነሱንም ራዕና ህልም ሳያሳኩ ይሄው ጭንቅላታቸው በረንዳ ሆነ፤ ፀጉር ያለውም ከነማሰቢያቸው ጭምር ሸበተ አረጁ ጃጁ።
በጣም ያሳዝኑኛል ቅማላቸውን ካራገፊ፣ በረባሶና ሰቨን ዶር ጫማ አውልቀው ደረጃውን የጠበቀ መጫማት ከጀመሩ፣ ጥብቆ ቁምጣቸውን በሱፍ ከቀየሩ፣ ከደደቢት ወጥተው ከተማ ከገቡ፣ ገንዘብ፣ ሥልጣን፣ ዝና፣ ክብር ካገኙ ባለፈው ለታ 27 ዓመት አለፋቸው ግን ምንም አልተቀየሩም በቃ አሁንም የሰው ደም ይጠጣሉ ሥጋውንም ይጎርዳሉ።
አሁን በቀደም ለታ እዋይ እንታ መፂዩ? እንታ እዚ ግርግር በማለት ስዩም መስፍን የሥነአእምሮ ጦርነት ታውጆብናል አለ፤ ያን ለማለት ያበቃው ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያን ደጋግሞ ስለጠራት ነው።
 አይ መረገም ደጉ…?! ክፉና ደጉን እንኳ መለየት ተሳናቸው። ኢትዮጵያ ሲባል መስማት አይወዱም። ከሰሙም መስቀል እንደዬ ሰይጣን በርቀት ነው!! አባይ ፀሀዬ ትምክተኛና ጠባብ የአፉ ማስቲካ ናት አሉ። ተኝቶ ሲያቃዥ ማነው?…. ምንድነው?… ት..ት.ትምክተኛ ነ..ነው? ጠ..ጠ..ጠባብ በማለት ሌሊቱን ሲቃዥ ውሽማውን እንቅልፍ ነስቷት እንደሚያድር ተናግራለች።
ለአንዱ ወዳጄ ቢቀርባቸውስ?፣ ጡረታ ቢወጡስ? ብዩ ሳናግረው  ለምን? ብሎ ጠየቀኝ፤ መልስ ሳልሰጠው አስከትሎ ብቻ ይሙቱ እንዳትለኝ አባቴ ይሙት እቀየመሀለሁ!! ብሎ አንባረቀ፤ እኔም ምነው ሰላም አይደለም እንዴ ስለው… ማዕከላዊ ጥፍር መንቀል፣ መግረፍ፣ ብልት ላይ 2 ሊትር ውሀን ለረጅም ሰዓት ማንጠልጠልና የስቃይ አይነቶችን ሳላሳያቸው እንዳይሞቱብኝ በፀሎትህ እርዳኝ ብሎ እሱ ፀሎቱን አዛው ጀመረ።
አረመኔነታቸው ሕዝባችንና አገራችን ላይ ብዙ ጉዳት አድርሷል ማንም ሊራራላቸው እንደማይችል ስለሚያቁ ሁሌም ፍርሀት ውስጥ ናቸው፤ አይደለም እነሱ ደንግጦ የሞተው ንጉሳቸው መቃብር በወታደር ይጠበቃል።
 እኔ ያሳዝኑኛል የምር አንጀቴን ይበሉታል በተለይ ስዩም መስፍን ከነ ውሸቱ የሚያሳዝን ሚስኪን።
Filed in: Amharic