>
5:18 pm - Saturday June 15, 0024

የባድመ ነገር (ከአቶ ገብረመድህን አርአያ)

 

ዛሬ በሃገራችን ኢትዮጵያ  የህዝብ ትልቁ መነጋገሪያ የሆነው  የህ.ወ.ሓ.ት.( ኢህአደግ )ስርአት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተሰብስቦ ካሳለፋቸው ወሳኔ አንዱ የኢትዮ፟-ኤርትራ ግንኙነት በተመለከተ ነው ።

የአንዲት ሉአላዊት ሃገር ኢትዩጵያ ልጆች ሁነው ለስንት ሺህ አመታት አብረው የኖሩ አንድ አካል አንድ ህዝብ

በመሆን  የኖረ ህዝብ፤ በሁለቱ ወንድማሞች ሃገራት ሲባል  በጣም ከባድ ነው ።አሁንም የኤርትራ ህዝብና የእትዮጵያ

ህዝብ ፤በባህል፤በቋንቋ ፤በሥጋ ዝምድና ወዘተ የተሳሰሩ ህዝብ ስለሆኖ ተመልሶ መተቃቀፉና ወደ አንድነቱ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም ። ኢትዮጵያ ሃገራችን በአንድነት እንገነባት አለን ።ዛሬ በውጭ ሃገር የሚኖሩ  በኤርትራ ህዝብና በኢትዮጵያ ህዝብ የሚታየው መልካም መግባባት ፍቅር የአንድነት ሰላም ፤በደጉም ፤በክፉም መተባበርና መደጋገፍ በግልፅ ይታያል ፤ ለቸሩ አምላክ የሚሳነው የለምና ወደ ቀድሞው አንድነታችን ይምልሰናል ። ይህ ባጭሩ ካልኩ ፤የኤርትራ እና የኢትዮጵያ  ክፉ መዘዝ የመጣ ከየትኛው መዓዝን ተነስቶ ነው ።እውነት ባድመ በኤርትራ ግዛት ውስጥ ነበረች ?ለኢትዮጵያ ሊቃውንት ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተወው ።

     የንፁሓን ደም የፈሰሰው በምን ምክንያት የተነሳ ነው ።ሁሉም ነገር  መነሻ አለው ፤በዚች ዓለም አንዱን ነገር ሊያምር ወይም ሊበላሽ የራሱ የሆነ ምክንያቶች አሉት(cause and effect ) ።አንድ ነገር የመነሻ ምክንያት  ከሌለ አንድ ምክንያት አይከሰትም ።

      በኢትዮጵያና በኤርትራ በባድሜ የተፈጠረው ክ100ሺህ በላይ የሰው  ሂወት የቀጠፈው ፤የሃገር ሃብትና ንብረት ያወደመው ደም አፋሳሽ ግጭት የፈጠረው የራሱ ምክንያት አለው ።ይህ ምክንያትም የዛን ጊዜ ስሙ ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት)የዛሬው ስሙ ፤ህ.ወ.ሓ.ት.)የፈጠረው ፀረ ህዝብ ፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ደደቢት ይዞት የመጣ ነው ።

አንዳንድ ሊሂቃን እንድሚናገሩት ይህ ጦርነት የተነሳው በኢኮኖሚ ሳቢያ ነው፤ሌላ የተማረ  ምሁር ደግሞ ሌላ ይናገራል፤ነገር ግን ይህ አውዳሚ ጦርነት የተነሳው ፤በባድሜና በሌሎች የመሬት ይገባኛ ጥያቄ ነው ፤ ለጦርነቱ መንሰኤ ዋና ምክንያቱ  ይህ ነው ;። ይህን በድፍረት የምናገረው የተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.)የመጀመሪያው ከምስረታው ትንሽ ወራት ቆይቸ የተቀላቀልክት የበረሃ ወይም ሜዳ ታጋይ የነበርኩ ከ15 ዓመታት በላይ የታገልኩለት ድርጅት የመሪዎቹ ሤራና ተግባር ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ ሆነው ደደቢት የወረዱ መሆናቸው በሚገባ ስለማውቃቸው ነው ። በኋላ አውግዠው የወጣሁ ።

        ህ.ወ.ሓ.ት.( ማ.ገ.ብ.ት.)(ተ.ሓ.ህ.ት.)በየካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ብረት ታጥቆ ደደቢት በረሃ እንደገባ ፤ብዙ ችግር ነበረው ፤ከችግሮቹ ፤በሽታ፤ርሃብ፤ወ.ዘ.ተ.ብረት፤ጥይት፤ስንቅ፤ ሌላም ከባድ እጥረት ነበሩት ፤ በጣም የተጎሳቋለ ድሃ  ድርጅትም ነው ።ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔው ለጊዝያዊ ጠቅሙ ሲል የማቆፍረው ጉድጓድ የለም አሁንም እንደዛው ፤የምይሰራው የማጭበርበር የማይዋሸው ጉድ የለም ይዋሻል፤ አስመስሎ ተናጋሪ፤ ከሃዲ፤ ዘራፊ ፤ሽብርተኛ እባብ ተንኮለኛ በዓለም ተዋዳዳሪ የሌለው ህ.ወ.ሓ.ት. ብቻ ነው ።፤ብረት፤ ጥይት፤የእጅ ቦምብ፤አርፒጂ ወ.ዘ.ተ.ለማግኘት ሲል በተወሰነ እንኳን ከሻእብያ ቢያገኝም በበለጠ የታጠቀ የተደራጀ ጀብሓ (ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ ) ስለነበር   ክዚሁ ድርጅትም ቀደም ሲል ትንሽ እርጥባን ቢያገኝም እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት.ማፍያ አምራር ዘዴ አገኘ ፤ ጊዜው 1969 ዓ.ም. ።በዚሁ ወቅት የነብሩ አመራር ስማቸውን መግለፅ አስፈላኢ ነው ።

                የነበሩ የህ.ወ.ሓ.ት. ከፍተኛ አመራሮች ፤

1ኛ    አረጋዊ በርሄ   (የደደቢት ስሙ በሪሁ በርሄ) ሃላፊነቱ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት ሊቀ መንበርና  የሰራዊቱ አዛዥ ፤የበላይ ሃላፊ

2ኛ   ፋንታሁ ዘርአፅዮን (የደደቢት ስሙ ግደይ ዘርአፅዮን)ሃላፊነቱ፤ የህ.ወ.ሓ.ት.ም/ሊቀ መንበርና አስተዳደር የሓለዋ ወያኔ ሃላፊ

3ኛ   አምባየ መስፍን  ( የደደቢት ስሙ ሥዩም መስፍን ) ሃላፊነቱ ፤በአስተዳደርም በወታደራዊም ተባባሪ በኋላ የውጭጉዳይ ሃላፊ

4ኛ   አምሃ ፀሃየ       (የደደቢት ስሙ አባይ ፀሃየ     )ሃላፊነቱ ፤ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ  የህዝብ ግንኙነት ዋና ሃላፊ)

5ኛ   ወልደስላሴ ነጋ   ( የደደቢት ስብሓት ነጋ    )ሃላፊነቱ ፤ የሓለዋ ወያኔና የግደይ ዘርአፅዮን ተባባሪ )

            እነዚህ ክ1—5–ተጠቅሰው ያሉትን ፖሊት   ቢሮ ሲሆኑ ድርጅቱን በሙሉ ሃላፊነት የሚመሩ ናቸው ።ፖሊሲ  እቅዱች የሚያወጣሉ በተግባር ያስፈፅማሉ ፤ሁሉ ሥልጣን ጠቅልለው የያዙ ስለሆኑ ማንም ነገር በእነዚህ ተእዛዝ  ተፈፃሚ ይደረጋል ።

      ከላይ በተጠቀሱ ፖሊት ቢሮ በ1968 ዓ.ም.መጨረሻ ተመርጠው የመጡ ተለዋጭ ማእከላይ ኮሚቴ ፤

1ኛ   ለገሠ ዜናዊ  (የደደቢት ስሙ መለስ ዜናዊ ፟)ሃላፊነቱ ፤ የአባይ ፀሃይ ምክትል የፕሮፓጋንዳና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ከአምስቱ ከፍተኛ አመራሮች በማንኛው ወሳኔ የማይለይ ።

2ኛ   ወለስላሴ አብርሃ (የደደቢት ስሙ ስየ አብርሃ ) ሃላፊነቱ ፤የአረጋዊ በርሄ ተባባሪ

3ኛ   ትኰእ ወልዱ  (የደደቢት ስሙ አውዓሎም ወልዱ)ሃላፊነት ፤ በወቅቱ የህዝብ ግንኙነ ትተባባሪ አስተባባሪ

4ኛ   አፅብሃ ዳኘው  ( የደደቢት ስሙ ሸዊት ዳኘው )አልቆየም በ3 ወሩ ቆይታ ስብሃትን መለስ ዜናዊ ትእዛዝ በጥይት ተደብድቦ  ከተረሸ በኋላ ፤ ተተኪ ብለው ያመጡት ፤ራሰወርቅ ቀፀላ ( የደደቢት ስሙ አታክልት ቀፀላ )

የማእከላይ ኮሚቴ እንደያዘ ከ6 ወር ቆይታ በሳሞራ የኑስ እጅ ጎንባስ ሞሞና በተባለ ቦታ አስገደሉት ዋና መሪዎች ተባብረው ።

                            ለጥቅም ሲሉ የተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.) መሪዎች በኢትዮጵያ ሉአላዊነት የፈፀሙት ሤራ።

ወያኔ በኢትዮጵያ ሏላዊነት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ያልፈፀመው በደል  ያልፈፀመው ግፍ የለም ፤ከደደቢት ይዞት የመጣው ኢትዮጵያን ማውደምና ህዝብዋን መበታተን ወደ እርስ በራስ እልቂትና ደም መፋሰስ አሁንም ቀጥሎበታ ፤ይህች በምኒልክ ትናንትና የተፈጠረችው ኢትዮጵያ ይምትባል የአማራው (ኢትዮጵያ ) ግዛት ለወደፊቱ ሕብረተ ሰብአዋዊ  ቅሳነት እንደማይኖራት ነው ይምናደርጋት ብለው ይተነሱ ወንጀለኛ ሽብርተኛ ህ.ወ.ሓ.ቶች ናቸው። የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንያት የዛሬው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁኔታ ተመልከቱ። ወደ ዋናው ሃሳቤ ላምራ ።

     ጀብሃ ቀደም ብሎ የተፈጠረ ነው ፤ሻዕብያም ክጀብሃ በ1961ዓ.ም. እ. ኤ.አ. ተገንጥሎ ለብቻው የተደራጀ  ድርጅት ነው።ገና ህ.ወ.ሓ.ት.ሳይደራጅ ደደቢት በረሃ ሳይወጣም፤ የባድሜ አካባቢ የኤርትራ ነው ፤ሳይሉ ባድሜ ረግጠዋት አያውቁም ነበር ።ረግጠዉት አያውቁም ብቻ ሳይሆን የባድሜ ወረዳዎች ሁሉ አያውቁትም ዓዲ ሃገራይ፤ሸላሎ፤ዓዲ ነብሬኢድ፤ዓዲ ፀፀር፤መንጠብጠብ፤እንዳጉሬዛ ፤ሞጉእ ፤ሱር፤ሰመማ፤መሬቶ፤ ወ.ዘ.ተ የጀብሃም ሆነ የሻዕብያ የራሳቸው ትግል ከጀመሩ ቦታው አያውቁቱም ።ባድመ ፤ባዳ፤ኢሮብ፤ዓሊቴና አያውቁትም ፤ዛላምበሳ ሞቅ ያለች ከተማ የዓዲግራት ወረዳ አንዳአንድ ነገር ለመግዛት ያውቋታል፤የትግራይ ኢትዮጵያ መሬት መሆኑም በሚገባ ያውቃሉ ።የኤርትራ መሬት ነው ብለውም በየአካባቢው ከሚኖረው ህዝብ የፈጠሩት ችግር አልታየም ፤አልተሰማም ፤ምክንያቱም የትግራይ ጠ/ግዛት ቦታ መሆኑ በተገቢ ሰለሚያውቁት ነው ።     ተ.ሓ.ህ.ት.( የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት)ደደቢት ከገባም በኋላም ከሻዕብያም ሆነ ከጀበሃ የኛ ፤ የኤርትራ መሬት ነው ብለው የጠየቁበት ስንዝር የምታክል መሬት የለችም አልጠየቁም ስለ መሬት ይገባኛል አልተነሳም የሚያነስቡበት ምክንያት የላቸውም ።እስከ 1969ዓ.ም. ማለት ነው ። ወያኔ በዚሁ ጊዜ በብዙ ጠላት የተከበበ ነው ፤ ትጥቁ ትንሽ ኋላ ቀር ነው ፤መውጫ መዳኛ ይፈልጋል ሆነም ቀረም ያለው ግንኙነት ከሻዕብያ ብቻ ነበር ፤ከጀብሃም በመጠኑ ።

   በዚሁ ወቅት 1969 ዓ.ም. አጋማሽ ወሩን አላስተውሰውም ። የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር በድብቅ ተሰባስበው በትግራይ ህዝብ ከባድ ረቂቅ  የክህደት ሤራ ፈፀሙ ፤የፈተሉት ሤራ ለሻዕብያና ጀብሃ በኤርትራ ዳር ደንበር የሚገኙ የትግራይ ጠ/ግዛት ከባድመ ባዳ አፋር የነሱም ስለሆነ ገብተው ህዝባቸው ያስተዳድሩ ብለው ፖሊት ቢሮው ወሰነ አምስቱም ተስማሙ  ። በሁለት ተከፋፍለው ያዙት እቅድ ፤አራት የፖሊት ቢሮ አባላት ።ሁለቱ ወደ ሻዕብያ ፤ሁለቱ ወደ ጀብሃ ከፍተኛ አመራሮች ተጓዙ ፤በቆጦረው ቀንም ደረሱ ።የሁለቱም መልእክተኞች ማለት የህ.ወ.ሓ.ት.(በዚያን ጊዜ ስሙ ተ.ሓ.ህ.ት.) (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ )ይዘዉት  የሄዱት መለክት አንድ ነው ።መልእክቱ፤ከባድሜ አንስቶ እስከ ዓዲ ፀፀር ፤እንዳ ጉሬዛ   ፤ከዛም ከእገላ እስከ አጋሜ (ዓዲግራት) አውራጃ፤ያሉ  ወረዳዎች አብዛኛው ነዋሪው ህዝብ ኢርትራዊ ነው፤ ለምን እዛው ገብታቹህ ህዝባቹ አትመሩትም አታስተዳዱሩትም በተ.ሓ.ህ.ት.በኩል ሙሉ ፍላጎታችን መሆኑ እናረጋግጣለን ። ስለ መሬት ጥያቄ የሚነሳ ካለም  በሌላ ጊዜ እንነጋገርበት አለን ። በማለት ቃል ገብተው ተመለሱ ። ጀብሃም ሆነ ሻዕብያ ይህን የደረሳቸው መለክት በይፋ ተናግረዋል ፤የኤርትራ ትግል ከየት ውዴት መለስ ዜናዊ በፃፈው መፀሓፍም ከዚህ አያይዞ በአደናጋሪ መልኩ ያስቀመጠው አለ ።በጀብሃ በኩል ያገኘው ምላሽ ፤ከደስታው ብዛት ፈነጩ  (ወያኔ ) ወይን ሰማይ ላይ አወጥዋት ፤የተለያዩ ወታደራዊ ትጥቅ ፤ጥይት፤የእጅ ቦምብ ፤አነስተኛ ወታደራዊ መገናኛ ሬድዮ ፤በመጠኑም የፅሕፈት መሳሪም ወ.ዘ.ተ. ሰጡ ።በሻዕብያ በኩል ምን እንደተደረገ አይታወቅም ፤ምክንያቱም ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ከትግሉ መነሻ ጀምሮ  እስከ መጨረሻው የሻዕብያ ጥገኛ (parasite) ስለሆነች ይህ ሰጡ ይህ አደረጉ ብለህ አታውቀውም ሁሌም የተለያዩ ንብረት ስለሚሉኩ ።ይህ ውሳኔ ከተደመደመ በኋላ በየቦታው እያናፋ የገባው ጀብሃ ነበር ። በ1969 ዓ. ም. የክረምት መግቢያ ጊዜ ወሩ ሰኔ ይመስለኛል ስለዘነጋሁት ይቅርታ ፤  የህ.ወ.ሓ.ት.ፖሊት ቢሮ አመራር ከላይ ስማቸው የተጠቀሱ አምስቱ 6ተኛው መለስ ዜናዊ ተጨምሮ ለህ.ወ.ሓ፣ት፣ታጋይ በሙሉ ግልፅ በሆነ አዋጅ መሰል መልእክት አስተላለፉ ፤በተለየ ደግሞ ለህ.ወ.ሓ.ት.የህዝብ ግንኙነት አባላት በሙሉ ከነማስጠንቄቃው ጭምር አሁንም በሂወት የሚገኙ አሉ ይህን በአመራሩ የወረደ ትእዛዝ እንደማይረሱትና እንደሚያውቁት አስረግጨ ለመናገር እፈልጋለሁ ፤ይህን ከካዱ የሰው ፍጡር አይደሉም ።የሻዕብያና የጀብሃ ታጋዮች የኤርትራዊ ህዝባቸው ከባድመ እስከ ሸራሮ ፤ዓዲ አውዓላ ፤ዓዲ ሃገራይ ፤ዓዲዳዕሮ፤ጭላ፤ሰመማ ፤እገላ ፤ዓጋሜ (ዓዲግራት)ባዳ ኢሮብ ዓሊቴና አፋር ወ.ዘ.ተ.ህዝባቸውን ለማደራጀት ሰለሚንቀሳቀሱ ፤ማንም የተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.) ታጋይ እንቅፋት እንዳይፈጥርባቸው መጠንቀቅ አለበት፤የፈጠርነው መልካም የትግል ትብብር እንዳታበላሹ ተጠንቀቁ  ፤ህዝባቸው በፈለጉት ቀን ስዓት ቦታ መጥራት ማደራጀት ማስተማር መብታቸው ነው ፤እኛ ተ.ሓ.ህ.ት.እናስተዳድራለን ፤ሻዕብያም ጀብሃ ያስተዳድራሉ በሶስታችን የተዳደራል እናንተም ሥራቹህ ሥሩ እነሱም ይስራ ፤በማለት ህዝቡ በሶስቱ አረሜነዎች ገዳዮች እጅ ወድቆ ከ1969 ዓ.ም. እስከ 1972 ዓ.ም ቀጠለ ።.በዚህ ጊዜ በእነዚህ ቦታዎች ኢርትራዊም ሆነ ኢትዮጵያዊው የትግራይ ህብረተሰብ አሰቃቂ ግፍ ተፈፅሞበትል ፤በጀብሃ በኩል የሚፈፀመው ሶቆቃና አፍነው ፤ የሻዕብያ ሰላይና ደጋፊ ነህ እየተባለ የቤተሰብ ሃላፊ ሁሉ በሌሊት እየታፈነ የውሃ ሽታ ሆኖ የቀረው ቤቱ ይቁጠረው ።በሻዕብያ በኩልም ልክ ጀብሃ በሚጠቅምበት ስልት የጀብሃ ሰላይና ደጋፊ እየተባለ የስንት ንፁሃን ቤት ፈረሰ ደብዛቸው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ።በወያኔ በኩል ሲፈፀም የነበረው ግፍና ሶቆቃ ክፉ አሰቃቂ ከመሆኑም በላይ ታሪክ የማይረሳው በህዝቡ ላይ አረሜናዊ ግፍ ነበር የፈፀመው ፤በጀብሃና በሻዕብያ የሚፈፀሙ ግፍ እንዳሉ ሆነው ፤ወያኔ በበኩሉ ደግሞ ለዚሁ ህዝብ የተለያዩ ስሞች በመስጠት ፤የደርግ ሰላይ ፤ኢድዩ፤ኢህአፓ፤ፀረ ት.ሓ.ህ.ት.፤ፀረ ኢርትራ ትግል፤ ፊውዳል፤ የአማራ አሽከር፤የሽዋ አማራ ፤ሌላም እያለ ፤የሚፈልጋቸው ሁሉ በቀንና በለሊት እያፈነ ሓለዋ ወይኔ እያስገባ ወንዱም ሴቱም እየገደለ ህብረተሰቡን በሲኦል ስቃይ ውስጥ ወደቀ  ፤ወያኔ በመግደል ብቻ አልተመለሰም ፤ጥሮ ግሮ ያፈራው ሃብት ነብረቱም ወርስ ለተ.ሓ.ህ.ት. (ህ.ወ.ሓ.ት.)እየተባለ ሃብቱ ተወርሶ ልጆቹ በባዶ ቤት ተጥለው የቀሩበት ከ1968 ዓ.ም አጋማሽ .ጀምሮ ነው ።የገንዘብ መቀጫም ሶስቱ ህ.ወ.ሓ.ት. ጀብሃ . ሻዕብያ ለአንድ ሰው ምክንያት ሲያጡበት ለስብሰባ ተጠርተህ አልመጣህም ይህን ያህል ብር ተቀጥተሃል ይባላል፤ያለው ከብት፤ፍየል ፤ያለዉን ሽጦ፤ይከፍላል ።በዚሁ በዛሬ አወዛጋቢ መሬት ተብሎ እየተጠራ ያለው ቦታ ተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.)ከሻዕብያ፤ ከጀብሃ ጥቅም አገኛለሁ ብሎ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ግቡ ህዝባቹህ አድራጁ ምሩ እያለ መርቶ ያገባቸው ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ነው ።በዚሁ የነሳም የመሬት ይገባኛል ጥያቄ በጀብሃ በሻዕብያ ተነሳ ። የኢትዮ–ኤርትራ ጦርነት የህ.ወ.ሓ.ት.ማፍያ አመራር በ1969ዓ.ም..በፈፀሙት የከሃዲነት የሤራ የሥራ ወጤትም ነው ። መሪዎቹም ከላይ የተጠቀሱ ናቸው ።

.ጀብሃ በወያኔ ፈቃድና ፍላጎት መሰረት  በሚንቀሳቀሰበት በትግራይ መሬት ሁሉ ፤ በነዋሪው ህዝብ  ማሰር ፤መደብደ፤ ማሰቃየት ፤ሃብት ንብረት መዝረፍ ፤አስገድዶ ሴቶች መድፈር ፤ በግልፅ ያንፀባርቅ ነበር፤ በወያኔ በኩል ጀብሃ ይህ ሁሉ ችግር ሲፈጠር ያሳየው ተቃውሞ ህዝቡን መከላከል  ሙከራም ፤አላደረገም ።ከዚሁም አከታትሎ ጀብሃ እና ሻዕብያ በተ.ህ.ሓ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.) ፈቃድ መሰረት ለሁሉ ኤርትራዊ ነኝ ለሚል ሰው የመታወቂይ ወረቀት ተሰጠው ፤ ጀብሃ በብዛት በትግራይ ውስጥ በተለያዩ  ወረዳዎች ፤ቀበሌ እየመለመለ ምልሽያዎች እያስታጠቀ በብዛት አቋቋመ ፤የኤርትራ ትግል ከየት—– አንብቡ ፤ ይህ ጉዳይ የታች አድያቦና የላይ አድያቦ፤ የእገላ ፤የጭላ ፤ነዋሪው ህዝብ በግልፅ ያውቃል ህዝቡ ራሱ ምስክርነቱ የሚሰጥበትም ነው ። በሻዕብያ በኩል ብዙም አልሄደበትም  ጀምረው ነበር አልገፉበትም ። ጀብሃ ከዚሁ በመነሳት በከረረ መልኩ ይህ ሁሉ የኤርትራ መሬት ነው የሚል ጥያቄው አበርትቶ ገፍቶ ነበር ፤

ታች አድያቦ ፤ላይ አድያቦ የኤርትራ መሬት ነው ፤ጀብሃ በሰላማዊ  ችግር እየፈየረ መጣ ፤ሻዕብያም የጀብሃ መንገድ ተከትሎ የመሬት ጥያቄው አነሳ ልዩነቱ ሻዕብያ በወያኔ ከሰማይ የወረደለት ሕብስተ ማና በጥንቃቄና በዲፕሎማሲ ቀጠለበት  ፤ውሻ በከፈተው ቀዳዳ ጅብ ገባ የሚባለው ተረት በትክክል ይህ ማለት ነው ፤ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት.በከፈተው ቀዳዳ ጅቦች ገቡ። በ1969 ዓ.ም. ወያኔ በከፈተው ቀዳዳ ማለት ነው ፤ይህም ለጊዚያዊ ጥቅም ፤ዛሬ በባድሜ የተፈጠረው ደም አፋሳሽ፤ ኢትዮጵያዊው የትግራይ ህዝብ ለመከራ የተዳረገው ፤ተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.) በ1969 ዓ.ም.ለጊዛያዊ ጥቅሙ ለማግበስበስ  ሲል ጀብሃና ሻዕብያን ጠርቶ መሬቱን የናንተ ነው ብሎ የኢትዮጵያ የትግራይ ጠ/ግዛት በኤርትራ አዋሳኝ ያሉትን አሳልፎ የሰጠው ራሱ ህ.ወ.ሓ.ት.ነው ።ከዚህ በፊት ፤ባድሜ፤ ኢሮብ ፤ባዳ ፤ዓሊተና ፤ዳልገዳ ፤ዛላምበሳ ፤እገላ ፤ታች አድያቦ ፤ላይ አድያቦ ፤በሙሉ በትግራይ ግዛት ውስጥ እንደነብሩ ፤አንደሆኑም ፤ ቀድሞ በሥልጣን የነበሩ ፤ባለ ሥልጣናት ተረጋግጦ ያለፈ  የተፃፈ ነው ።ማንም የኤርትራ ባለሥልጣንም እነዚ ቦታዎች የኤርትራ ናቸው ብሎ አላስተዳደረም አልገዛም አልጠየቀም ፤ጣልያን እንደተሸነፈም የመጀመሪያው የትግራይ ጠቅላይ ገዥና ሙሉ እንደራሴ ተብለው የመጡ ደጃዝማች ክፍሌ፤ቅጥሎም ክቡር ልዑል ራስ ሥዩም መንገሻ የመጨረሻው ራስ መንገሻ ሥዩም ነበሩ ፤ይህ ቦታ ሲያስተዳድሩት የነብሩ እነዚህ ናቸው ።ከእነዚህ ብቁ ማስረጃ የለም ፤የወያኔ መናፍቅ ከሃዲዎች ግን እንኳን ስለ ሃገር ስለ ህዝብ ይቅርና ስለ ራሳቸው ማንነትም አያውቁም ።

      ይህ ፋሽሽት   ህ.ወ.ሓ.ት ድርጅት . ተግባርና ዓላማው  ፤በኢትዮጵያ ሉአላዊነት፤ ታሪክ ይቅር በማይለው፤ ሃገር  አፍርሰዋል ኤርትራን አስገንጥለዋል ፤የጎንደር ጠ/ግዛት ዳር ድንበር ከ745 ኪሎ ሜትር በላይ ለምና ታሪካዊ አፄ ቴድሮስ፤አፄ ዮውሓንስ የተሰዉለት  ፤ ለምና ድንግል መሬት ፤ ለሱዳን መንግሥት አሳልፈው ሽጠዋል፤ወ.ዘ.ተ የጎንደር ጠ/ግዛት የሰሜን አማራ መሬት በጉልበታቸ ወረው የአማራውን ዘር አጥፍተው  የትግራይ አድርገዋል ፤ከወሎ ጠ/ግዛት ከሓሸንጌ አንስቶ እስከ ራያና ቆቦ ድረስ ያለው ለም መሬት ወረው ወደ ትግራይ ቀላቅለዋል ፤ከአፋርም እንደዚሁ ።የተፈጠሩበት አላማቸው ይህ ነው ።

    ከ1971ዓ.ም.ወደ መጨረሻው አካባቢ  ጀምሮ በሻዕብያና በጀብሃ ፤በህ.ወ.ሓ.ት. በኢ.ህ.አ.ፓ .ወደ ጦርነት የሚያመር ግብግብ  ስለተፈጠረ ሁኔትዎቹ ፤በፍጥነት እየተቀየሩ ሄዱ ፤ከ1972 ዓ.ም. አንስቶ በጀብሃና በሻዕብያ አንዱን ለአንዱ  አድፍጦ ማጥቃት እየተስፋፋ ሄደ ፤ወያኔ በኢትዮጵያዊው በኢ.ህ.ፓ.ም.ላይ ዘምተ ፤ከህዳር ወር 1972 ዓ፣ም እስከ ታህሣስ ወር 1972 ዓ.ም. ወያኔ በኢህአፓ ሙሉ ጦርነት ከፈተ ፤ሻዕብያም በጀብሃ ላይ የመጨረሻ ጦርነቱን ጀመረ ።ጦርነቱ በዚሁ ደረጃ በነበረበት ጊዜ በ1969 ዓ.ም. ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ባመጣው ሰበብ ጀብሃና ፤ሻዕብያ ፤ትግራይ ውስጥ ገብተው ፤ሲያሙሱ ፤ህዝቡን ሲያጠቁ የነበሩ በተነሳው የእርስ በርሳቸው ጦርነት ትግራይን ለቃው ወጡ ።የመሬት ጥያቄ ግን በሻዕብያ ተጠናክሮ የተጀመረው ጦርነት ሳይራዘም ሻዕብያ በዚሁ የመሬት ጥያቄ ድርድሩን ለምቀጠል ሁለት የሻዕብያ ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት  ተመድበው › በህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊት ቢሮው በኩልም ሁለት ተዳራዳሪዎች መረጠ 1ኛው አባይ ፀሃየ 2ኛው መለስ ዜናዊ እነዚሁ የህ.ወ.ሓ.ት.ና የሻዕብያ ተመርጠው የቀረቡ ሥራቸው ይህ የመሬት የይገባኛል ጥያቄ በሁለቱ ድርጅቶች ተነጋግረው ውሉን ማጠናቀቅና ማሰር ብቻ ነው ። ሁለት ጊዜ ተሰባስበው በ1972 ዓ.ም. በሸራሮ ማይኩሕሊ ፤ከአንድ ወር በኋላም ሸራሮ ከተማ ውስጥ በድርድሩ ተቀምጠው ፤በቀጣዩ ህዳር ወር 1972 ዓ.ም. እገላ ወረዳ ውስጥ፤ ዓዲ ጨጓር ከጾሮና የአንድ ስአት ተኩል ርቀት በምትገኝ በጎነፀ ቀሺ የሻዕብያ ደጋፊ ቤት ተገናኝተው ፤ለአንድ ቀን ተወያይተው መለስ ዜናዊን አባይ ፀሃይ አምነው የኤርትራ መሬት ግዛት ነው ብለው አረጋግጣው የኢትዮጵያ ትግራይ ጠ/ግዛት አሳልፈው ፈርመው የሰጡበት በዚሁ  ጊዜ ነው ። ሻዕብያ ባገኙው የአጋጣሚ ትልቅ ዕድል ፈጠረላቸው በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኤርትራውያን ከማስደሰቱ በላይ ትልቅ የድጋፍ አጋር ሆነላቸው።የወያኔው የተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.) መሪዎች አባይ ፀሃየን መለስ ዜናዊ የኤርትራ መሬት ነው ብለው አሳልፈው ሰጥተው ፈርመው የኢትዮጵያ የትግራይ መሬት አስረክበው ቁጭ አሉ ።ሕዳር ወር 1972 ዓ ፤ም፤ ድርድሩ ተደብቀው ሳይሆን በግልፅ ነበር፤ ብዙ የህ.ወ.ሓ.ት.ታጋይ በሻዕብያ በወያኔ የተደረገው የይገባኛል የመሬት ጥያቄ በሁለቱ ስምምነተ መጠናቀቁ ያውቃል ።

          ይህን ከተጠናቀቀ በኋላ ከተፈራረሙበት ከታህሳስ ወር 1972 ዓ.ም.የመሬት ይገባኛል ወይም መሬቱ በተመለከተ ጥያቄ  ተነስቶም ተሰምቶም አያውቁም ፤ወያኔና ሻዕብያ በጥብቅ ምስጢር ይዘዉት ቆዩ፤ለምን ቢባልም ከኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ  በጦርነት አውድማ ተጠምደዋል፤ የቀይ ኮከብ ዘመቻም እየመጣ እየተቃረበ ነው ፤የራሳቸው ህልውናም አያውቁም ነበር ፤ በተለይ ይህን የሚመለከተው ሻዕብያ ሲሆን  ሙሉ ጦርነቱ ኤርትራ ውስጥ ነበር።ትግራይ ውስጥ ብዙ ውጊያ አልነበረም ።በግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. ፋሽሽት ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ኢትዮጵያ ወሮ በቅኝ አገዛዝ ስርአቱ ከተቆጣጠረ፤ ሻዕብያም ኤርትራ ከተቆጣጠረ ፤የባድመ ጉዳይ ለተወሰነች ጥቂት ጊዜ  ረገብ ብላ በትቆይም አላነሱትም ብየ አላምንም ያነሱታል ፤ በተለይ የሻዕብያው መሪ ይህ ከሰማይ የወረደለት ዕድል ከጁ እንዳያመልጠው ከብዙ ኤርትራውያንም በሚመጣው ግፊት ፤ድንበሩ በተሎ መካለሉ እንዲፈፀም ሃያል ግፊት አለ ፤ ፤የኤርትራው መሪም ራሱ  ኢሳያስ አፈወርቅ፤ በከሃዲው የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር የተሰጠው ሰፊ የትግራይ መሬት ተሎ ብሎ መጠቅለል ይፈልግ ነበር፤ ኢሳያስ አፈወርቂ አስረክበኛ እያለ ግፊቱን በመለስ ዜናዊ ያሳድር እንደነበረም ጉዳዩ በሚያውቁ ሰዎች ሲነገር የነበረው ሃቅም አለ ፤ለመለስ ዜናዊና ድርጅቱ ይህ ትልቅ ችግር እንደሚፈጥርበት የተረጋገጠ በመሆኑ  ፤ የሚመራው ድርጅት ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ትም ሆነ አባሎቹ .ለውድቀት ስለሚዳርጋቸው ፤ ከህዝብ የሚነሳው ተቃውም ሊመክተው ስለማይችል ትልቅ ፍርሃት ለቀቀበት ሌሎች አመራርም ተጨምረው ፤ለሥልጣኑ ብሎ ነው ።መለስ ዜናዊ ጊዜው ሲያጓትተው የነበረ ፤ባንዳ የባህዳ ልጅ ፤ የመቀነት ቆራጭ ልጅ ፤ከሃዲ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ህዝብ ወረበላ ፤ለህዝብ ለሃገር ተቆርቁሮ አይደለም ያዘገየው ።ብ1972  ዓ .ም . እሱና አባይ ፀሃየ የኤርትራ መሬት ፤ኢትዮጵያ በወረራ የያዘችው ስለሆነ የኤርትራ መሆኑ አረጋግጠናል ብለው ነው የፈረሙት፤ ከዘመን ዘመን እየተሽጋገር የመጣው የትግራይ ጠ/ግዛት ትውልድ ዘሩ መሬቱ ከነህዝቡ የሸጡት። እንደ ህ/ወ.ሓ.ት.መሪዎች ነውረኝ ጉደኛ ከሃዲ በዚህ ዓለም ውስጥ ይኖራል? ፤ከምን የታሪክ መዝገብ አግኝተው ነው፤ ምስክርነታቸው የሰጡት፤ በጣም አስገራሚ ዓይን ያወጣ ውሸት  ። ነገ ሃቁ ይወጣል ። ሃገርና ህዝብ አፍርሰው በትነው ፤ከህዝብ ፍርድ አያመልጡም ።

        ስለሆነም የኢትዮ—-ኤርትራ ጦርነት መነሻ በዋናነቱ ይህ ነው ።ይህም ወያኔ ያመጠው ችግር ፤ከላይ የተጠቀሱ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር. ይህን  ችግር ፈጥረውም ፤ዛሬ ከደሙ ንፁህ ነኝ ብለው ፤የፈፀሙት ወንጀል ክደው ፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ፤ሌላ ይናገራሉ ፤ ይጠየቁበታ ህዝብ ላይ የተፈፀመ  ወንጀል በመሆኑ ።

የባድመ ፤የጾሮና ፤የቡሬ ወ.ዘ.ተ.እና የአልጀርሱ  ስምምነት ጉዳይ ሁሉ ኢትዮጵያዊ በተገቢው የተከታተለው ፤የሚያውቀው ፤እዚህ ብዙ አስፈላጊ አይሆንም ።

                                                   

Filed in: Amharic