>
5:13 pm - Saturday April 19, 4347

በኢንቨስትመንት ስም ጫት ያነፈዘውን ትውልድ በካናቢስ ለመጨረስ የተወጠነ ሴራ!!! (ሚኪ አምሀራ)

በኢንቨስትመንት ስም ጫት ያነፈዘውን ትውልድ  በካናቢስ ለመጨረስ የተወጠነ ሴራ!!!
ሚኪ አምሀራ
የአማራ ክልል ለአንድ የካናዳ ኩባንያ ካናቢስ የተባለዉን (አጤ ፋሪስ መሰለኝ) አምርቶ ወደ ዉጪ ሃገር በዘይትነት መልክ ለመላክ የ1000 ሺህ ሄክታር መሬት ፈቅዷል፡፡ ጫት የጨረሰዉ ወጣት ይሄን ካገኘን ደግሞ በቃ ጉዳችን ነዉ፡፡ካናቢስ አለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግበት ድራግ ነዉ፡፡  በጣም ትቂት አገራት ብቻ recreational cannabis ፈቅደዋል፡፡ አሜሪካ ሁለት ወይም ሶስት ስቴት፤ ካናዳ በቅርቡ እና ኔዘርላንድ ይመስለኛል ሌላዉ፡፡
ኢንቨስትመንትና የስራ እድል የሚፈጥር ቢሆንም ክልሉ ለእንደዚህ አይነት ድራግ የመቆጣጠሪያ regulation ያለዉ እራሱ አይመስለኝም፡፡ ኢንቨስትመንቱ በወረቀት ላይ ሲያዩት ብዙ ገንዘብ የሚመጣ ይመስላል እስከ 2 ቢሊየን ዶላር፡፡ ጥንቃቄ ካልተደረገበት በዛዉ ልክ ቀዉስ ሊመጣ እንደሚችል ደግሞ መታወቅ አለበት፡፡ጠንካራ ሪጉሌሽን ማበጀት አለያም ማቆም፡፡
 Amhara Investment commission  ማብራሪያ ብትሰጡን።
 
የካናቢስ ማምረት ጉዳይ፣ ትልቅ መዘዝ የሚያስከትል!!!
ያሬድ ጥበቡ

ለ27 ዓመታት ሲቀጠቀጥ የኖረውን የአማራ ክልል ሥራአጥ ወጣት በቀላሉ የሃሺሽ ሱሰኛ በማድረግ ህልውናውን ሊደመስስ የሚችል የዚህ የካናቢስ ማምረት ጉዳይ፣ ትልቅ መዘዝ የሚያስከትል በመሆኑ፣ የክልሉ ወላጆች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ምሁራን ለፕሮጀክቱ ያላቸውን ተቃውሞ ማሳየት አለባቸው። የካናቢስ ጉዳይ እንዲያውም ሃገርን የሚበክል አደንዛዥ እፅ በመሆኑ፣ በፌዴራል ደረጃ መያዝ ያለበትና፣ ፓርላማው ኢትዮጵያ ውስጥ እፁ እንዳይመረት የሚያግድ ሃገርአቀፍ ህግ እንዲወጣ አስፈላጊ ይመስለኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዚህን አደገኛ እፅ መዘዝ ተረድተው ከአሁኑ ያስቆሙታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እንዲያውም በመግለጫው ላይ ግልፅ እንደተደረገው ድርጅቱ በኬንያ፣ ኡጋንዳና ሩዋንዳም ተመሳሳይ ጥረት እያደረገ በመሆኑ፣ ዶክተር አቢይ ጉዳዩን ለአፍሪካ ህብረት አቅርበው፣ መላው አፍሪካ ለአደንዛዥ እፅ አምራቾች ዝግ መሆኑን የሚያሳይ አህጉር አቀፍ ስምምነት እንዲደረግ ግፊት ቢያደርጉ የመጀመሪያዉ አህጉርአቀፍ መሪነታቸውን ማሳያ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። አደንዛዥ እፅ ማምረት በፍፁም መፈቀድ የለበትም። ለመሆኑ የሃይማኖት መሪዎች የት አሉ? አሁን ነበር ድምፃቸውን ማሰማት የሚገባቸው አንድ ወቅት።

Filed in: Amharic