ታዬ ደንደአ
* ጅብ እንደልቡ ግጦ የበላን በአቅሙ ሳይሆን አንዳችን በሌላችን ላይ ጅብ በመሆናችን ነው!
ከዝህ በፍት ብያለዉ። አሁንም ደግሜ እላለሁ። ኦሮሞ እና አማራ ከህዝብ ብዛትም ሆነ ከቆዳ ስፋት አንፃር የኢትዮጵያ መሠረት ናቸዉ። ታሪክም ይህንኑ ይመሰክራል። ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚፈልግ ጠላት ሁለቱን ህዝቦች ያጋጫል። ጅብ እንደልቡ ግጦ የበላን በአቅሙ ሳይሆን አንዳችን በሌላችን ላይ ጅብ በመሆናችን ነዉ።
አሁን የተለያዩ ሰበካዎች እየተሰሙ ነዉ። ኦሮሞ እና አማራ የተለያዩ ባንዲራዎችን ይዞ አደባባይ ሲለወጡ ነገ ጧት ሊዋጉ ነዉ በማለት ሟርት ጀምሯል። በሬዲዮና በቴሌቭዥን ራሳቸዉ ለራሳቸዉ ሲያወሩ ሰምተናል። ግን ባንዲራ ፈፅሞ ሊያጋጨን አይችልም። ትስሰራችን ከባንዲራ በላይ ነዉ። ደም ከባዲራ ይበልጣል። መተባበር ለኛ የህልዉና ጉዳይ ነዉ። ይህን በተግባር አይተናል። በተከፋፈልን ጊዜ የጅቦች መጫወቻ ሆንን። በተባበርን ጊዜ ደግሞ ከራሳችን አልፈን የምስራቅ አፍሪካ ዋስትና ሆንን። የነፃነት እና የአንድነት አየር መንፈስ የጀመረዉ ከህብረታችን ባህር ነዉ። ህብረታችን ገና ለአፍሪካ እና ለዓለምም ብርሃን ይሆናል።

አይደለም እንዴ? ሠላም እደሩ!