>
5:18 pm - Friday June 15, 4863

አደራ ዶ/ር አብይ፥ ከዲያስፖራ (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

አደራ ዶ/ር አብይ፥ ከዲያስፖራ

ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

የሚወድዎትና እርስዎም የሚወዱት ዲያስፖራ ጋር ለመገናኘት፤ በመካከል ያለውን ፈተና አምላክ እንድንወጣ ያስችለናል ብዬ አምናለሁ። በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ባለው በኢትዮጵያ ቀን ላይ ተገኝተው ሊያዩን ቢፈልጉም አምላክ ስላልፈቀደ አልተሳካም። ሁላችንም እንደ አንድ ሆነን እርስዎን ለመቀበል እየፈለግን ሳለ፤ ግን ስለ መምጣትዎ በሚደረገው ዝግጅት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ መሰናክል እንዳይኖር ጥንቃቄ እናደርግ ዘንድ ይገባል። የእርስዎ መንገድ የተዋጣለት እንዲሆን ሁላችንም ለክቡርነትዎ ዘብ እንቁም።

የተዋደደ ሳይገናኝ እንዲሁ አይቀርም።

አሜሪካ የሚመጡት የአሜሪካንን መንግስት ለማናገር ሳይሆን ሕዝብዎን ለማናገር ስለሆነ፤ ዲያስፖራን ወክለው የእርስዎ እንግዳ ተቀባይ አስተባባሪ እንዲሆኑ ኤምባሲው ይህንን ሃላፊነት ሙሉ ለሙሉ ለሕዝቡ ቢለቅ ጥሩ ነው።  

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በመተባበር የእርስዎን ደህንነት መጠበቅ ብቸኛ ስራቸው ቢሆን መልካም ነው።

“አንድ ዶላር በቀን” ያሉትን ወርቅ አስተሳሰብዎት የተቀደሰ ነውና፤ አደራ፥ ሲመጡ እባክዎን አካውንቱን ከፍተው ይምጡ። እኛን አናግረው ሲመለሱ ባዶ እጅዎን አይመለሱም። የወደፊቱ እርዳታችን በኩር የሚሆንና ሀገር የሚያኮራ ልግስና አድርገን፤ ፍቅራችንን ለሕዝባችን በስራ የምንገልፅበት ዕድል ይፈጥርልናል። ለዚህም መብቃታችን መታደል ነው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አሰበ። ይጎበኛታልም።

አድራሻ፥ myEthiopia.com

Filed in: Amharic