>
5:13 pm - Sunday April 18, 5480

"እናንት ጽንፈኞች ከአረጀ አስተሳሰብ ተላቃችሁ መደመሩ ነው የሚበጃችሁ!!!" (ወዲ ሻምበል ዘ ብሔረ ኢትዬጵያ) 

“እናንት ጽንፈኞች ከአረጀ አስተሳሰብ ተላቃችሁ መደመሩ ነው የሚበጃችሁ!!!”
በወዲ ሻምበል ዘ ብሔረ ኢትዬጵያ 
 
“መምህር አብርሃ ደስታ እንዳለው የባህር ዳር ሰልፍ ድርግን ለመመለስ  ቢሆን ኖሮ የመጀመሪያ ተቃዋሚ የምሆነው በደርግ ስርአት ውስጥ የኢትዮጵያ የቀድሞው ሰራዊት የነበርኩ እኔ እሆን ነበር ምክንያቱ ደርግ ጮቃኝ መሆኑ ማንም ያውቃል ሆኖም ጭቆና ከጭቆና ጋር አይወዳደርም እንጂ ብታወዳድረው በህወሓትና በደርግ መሀከል በደሉ የሰማይና የምድር ይራራቃል።ደርግ አባላት የነበሩ ከአንድ ብሔር ወይም ከአንድ መንደር እንደ ህወሃት የተሰባሰቡ አይደሉም ደርግ የመደብ ጠላት እንጂ አንድን ህዝብ ጠላቴ ነው ብሎ አልታገለም ህወሃት ግን አማራ ጠላቴ ነው ብሎ የሸፈተ ቡድን ነው።ደርግ በስርቆት በዘረፋ በፍጹም አይታማም ህወሃት ኢህአዴግ ግን ስርቆትና ዘረፋ መለያቸውና ከበረሃ ጀምሮ ያካበቱት ልምዳቸው ነው ደርግ በተወሰኑ አመታት ውስጥ የተቃወሙትን በመላ ኢትዬጵያ በቀይ ሽብር ስም ህይወት አጥፍቷል።ህወሃት ግን በ17 አመታት የበረሃ ትግሉ ጊዜ ብዙ የትግራይ አባቶቻችን እና ወጣቶች 06 በተባለው ምድራዊ ሲኦል ውስጥ አስገብቶ እያሰቃየ ገድላል። በ27 አመት የስልጣን ዘመኑ ደግሞ ያለ ማቋረጥ ብዙዎችን ገድሏል አስሮአል አሰቃይታል አገር ለቀው እንዲወጡ አስገድዳል ስለዚህ የህወሃት በደልን በደርግ እያሳበቡ ህወሃት ዳግመኛ ነብስ እንዲዘራ በተቃዋሚ ስም የሚደረገውን አሻጥር ማንም ኢትዬጵያዊ አይፈቅድም ሲጠቃለል ይህ ሰንደቅዓላማ በባህርዳር ከፍ ብሎ የተውለበለበው እኔና የትግል ጓዶቼ በረሃ  ለበረሃ ይዘን ከወራሪዎች ከገንጣይ አስገንጣይ ወንበዴዎች ጋር የተዋደቅነው የደርግ ስለነበረ ሳይሆን የቆየ የነፃነት ምልክታችን ስለሆነ ነው። ይህን ሰንደቅዓላማ ስትመለከቱ በብሔር ብሔረሰብ ስም እያሳበባችሁ ለኢትዮጵያውያን ያላችሁ ንቀትና ጥላቻ ነው የሚያመላክተው ባይሆን ከአረጀ የጅቦች አስተሳሰብ ተላቃችሁ ብትደመሩ እመክራለሁ።
Filed in: Amharic