>
5:33 pm - Sunday December 5, 0754

በረከት ስምኦን ያረፈበት ሆቴል መስታወቱ ተሰባበረ ቪ8 መኪናውም ጋየች!!!  (አምዶም ገ/ሥላሴ)

በረከት ስምኦን ያረፈበት ሆቴል መስታወቱ ተሰባበረ ቪ8 መኪናውም ጋየች!!!
 አምዶም ገ/ሥላሴ
የደብረማርቆስ ወጣቶች የበረከት ስምኦንን በሆቴሉ ማረፍ በመቃወም  “ጎዛመን” የተሰኘውን የከተማውን ትልቅ ሆቴል መስታወት በድንጋይ በመበሳሳት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።
በኣቶ በረከት ስምኦን  ቪ8 መኪና ውስጥ ሶስት ላፕቶፕ፣ በርካታ ሰነዶች ከሁለት የመኪና ታርጋ ጋር የተገኘ ሲሆን ሁሉም ንብረቶች በከባቢው ወጣቶች ተወስደዋል። መኪናቸውም በተለኮሰባት እሳት ለመጋየት በቅታለች።
አቶ በረከት በሆቴሉ ውስጥ መኖሩን ያረጋገጡት የአካባቢው ወጣቶች በአድማ በታኝ ፖሊሶች እየተተኮሰባቸው ያለውን አስለቃሽ ጭስ ከምንም ሳይቆጥሩ ሆቴሉን ዙሪያውን በመክበብ “በረከት ወንጀለኛ ነው አስወጡልን”  እያሉ ነው።
እነ ኣቦይ ስብሓት ነጋ የሚገኙበት ኣክሱም ሆቴልም ከጎዛምን ሆቴል ሊማር ይገባዋል።
“ጃ ያስተሰርያል”ን እየዘፈንክ ፡በለው ቁረጠው ፍለጠውን መጨመር የመደመርን መርህ ይጥሳል!!
ያሬድ አማረ
 በየአካባቢው የሚሰማው ነገር ጥሩ ነገር አይደለም ማንም ዜጋ የትም የመንቀሳቀስ መብቱ አይገደብ፥  ይከበር  እያልን የሌላውን መብት መጻረር አግባብ መስሎ አይሰማኝም።አስተውሎ የሚራመድ ረጅም ርቀት ይጓዛል አይደል የሚባለው።ማንንም ስለወደድን የምናቀርብ ማንንም ስለጠላን አይንህን ላፈር እዚህ ለምን መጣህብኝ ማለት ከኢትዮጵያዊ ስነ-ምግባር ውጪ ከመኑ በላይ ከየቦታው ስለሚፈናቀሉት ዜጎች መፈናቀላቸው አግባብነት ያለው ድርጊት ነው ወደሚል ድምዳሜም ይወስዳል።ማንም ስለወደደ የሚያኖርህ ማንም ስለጠላህ ከዚህ ሂድልኝ እያለ የሚያባርርህ ዜግነትህ ትርጉመቢስ ይሆንና  መዘዙም ብዙ ነው። እንዲህ አይነቱ ድርጊት ፍጹም አግባብም  አይደለም።ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በመላ ሃገሪቱ የመንቀሳቀስ መብቱ እንዲከበር ብዙዎች ዋጋ ከፍለው እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል።ይህን ለመቀልበስ የሚደረግ ማንናቸውንም አይነት ጫፍ የወጡ ተቃውሞዎችን መኮነን ያሻል።ይህ ግዜ ከስሜት በላይ በጣም አስተውሎት የሚጠይቅ ግዜ ነው።በረከት ማርቆስ ላይ ስለታየ ለምን መጣብኝ ማለት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላል።በረከት ወንጀል ሲሰራ ከተገኘ ወንጀልን ለመከላከል የተቋቋመ አካል አለ ፥ወዲያው ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ሲገባ መኪና እስከማቃጠል የሚደርስ ጫፍ የወጣ ድርጊት በእውነት ሊወገዝና እርምት ሊወሰድበት ይገባል።ጃ ያስተሰርያልን እየዘፈንክ ፡በለው ቁረጠውን መጨመር የመደመርን መርህ ይጥሳልና ታላላቆች ዛሬም ምከሩ
Filed in: Amharic