>
5:18 pm - Thursday June 15, 5797

ኢንጂነር ስመኘዉ በቀለን በመግደል የከተማ ሽብር ምዕራፍ ተከፍቷል!!! (በፍቃዱ ሞረዳ)

ኢንጂነር ስመኘዉ በቀለን በመግደል የከተማ ሽብር ምዕራፍ ተከፍቷል!!!
በፍቃዱ ሞረዳ
 
በማንኛዉም ምክንያት ይህን ሰዉ በመግደል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚያስብ ካለ እንስሳ ነዉ፡፡ ሽብሩ በዚህ ላይቆም ይችላል፡፡ነገ ተረኛዉ ማን እንደሆነ አይታወቅም
፡፡ አፀፋዉ ከጦር ግንባር ዉጊያ በበለጠ ጥንቃቄን ይጠይቃል፡፡ ወደከተማ ዉጊያ ሊያድግ የመቻሉ ጉዳይም ታሳቢ ተደርጎ ብቃት ያለዉ የሰዉ ኃይልና አስፈላጊ መሣሪያንም መጠቀም የግድ ይላል፡፡
  ዋናዉ መሣሪያ ግን  ሕዝብ ነዉ፡፡ አመፅን በአመፅ ፣ ሽብርን በሽብር ለመመለስ መሞከር ለጊዜዉ የሚጠቅመዉ የሽብሩን ጠንሳሾች ነዉ፡፡ የማታ ማታ በሰፈሩት ቁና መሰፈራቸዉ ባይቀርም፡፡
  እናም በተረጋጋና በተደራጀ መንገድ የሽብሩን ምንጭ ለማድረቅ መተባበር እንጂ ‹‹እነርሱ›› በቀደዱት ቦይ መፍሰስ በቀላሉ ወደማንወጣዉ ቀዉስ ዉስጥ ሊከተን ስለሚችል ሁላችንም የዜግነት ግዴታችንን ከስሜታዊነት ወጥተን በጥንቃቄና በስክነት  እንድንወጣ ጊዜዉ የግድ ይላል፡፡ የሚዲያ ሰዎች፣ አክቲቪስቶችና ፖለቲከኞች ድርብ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 በተለይ በዘር ላይ የተመሰረተ ጣት ቅሰራና ጥቃት ትዉልድን ዋጋ ሊያስከፍል ስለሚችል በሰለጠነ አስተዉሎት ይህን አስቸጋሪ ምዕራፍ ማለፍ ጥሩ ነዉ፡፡
   ያለፈዉን ታሪካችንንም ሆነ የሌሎች ሀገሮችን መራራ ተመክሮ ልናስብ ይገባል፡፡
Filed in: Amharic