>
5:18 pm - Tuesday June 15, 2190

"በስብሠናል ካላችሁ የበሠበሠ ነገር ከህዝብ ጋር አብሮ ከኖረ በሽታ ነውና ለምን ዞር አትሉልንም ...? (ዶ/ር አረጋዊና ኢር ግደይ ዘርኣጽዮን)

“… በስብሠናል ካላችሁ የበሠበሠ ነገር ከህዝብ ጋር አብሮ ከኖረ በሽታ ነውና ለምን ዞር አትሉልንም …?
 ዶር አረጋዊ በርሄ፣ ኢ/ር ግደይ ዘረአጽዩን እና አቶ መኮንን ዘላለም – በ LTV
በከድር እንድሪስ
እነ ዶር #አረጋዊ_በርሄን እንግዳ አድርጋ ያቀረበችው ቤተልሄም በኮርኩዋሪ ጥያቄዎችዋ ዛሬም እልፍ ጉዳዬችን ከህወሓት መስራቾች አሠምታናለች።
እነዶክተር አረጋዊ በርሄ፣ኢ.ር #ግደይ_ዘረአጽዩን እና አቶ #መኮንን_ዘላለም (አቶ መኮንን በበርካታ የሕወሓት ደጋፊ የሆንኑ የትግራይ ተወላጆች ዘንድ ትግራይን እና ሕወሓትን ለማዳከም ሰርጎ የገባ ሰላይ የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቷቸዋል)።
 የህወሓት አመራርን የ #ድብቅ የ #መገንጠል ማኒፌስቶን ጨምሮ የተለያየ ነገር ተናግረዋል።
አንዳንድ አመራሮች #አማራን ብቻ ሳይሆን #ቤተክርስቲያንንም ጠላታችን ሲሉ እንደከረሙ፣ብሄር ከብሄር ለማጋጨት እንደሚሞክሩ፣በተጠና ሁኔታ ኢትዮጵያዊ አቅዋም የነበራቸውን ታጋዬች እንዴት እንደሚያገሉ፣የአንቀጽ 39ኝን ጉዳይ እዴት እንዳስወጡት በሚገባ ተንትነውታል።
 #ህወሓቶች ለምን የ #አኖሌን #ሀውልት እንዳሠሩት የ #ጉራፈርዳን ግፍ ለምን እንዳስፈጸሙት በብሄረሠቦች መካከል ለምን ልዩነትን እንደሚፈጥሩ ኢህዴንን አፍርሠው ብአዴን እንዳደረጉት ሁሉ ተንትነዋል።
አስተዋዩ ምሁር ፕሮፌሠር #አስራት_ወልደየስን ከመቃብር በላይ የሚኖር ስራ የሠሩ ብለው ሲያሞካሹ አቶ #መለስ_ዜናዊን ደግሞ #ዴቭላዊ (ሠይጣናዊ):ታክቲክ የሚጠቀሙ ብለዋቸዋል።
 የዶ.ር አብይን የፍቅር መንገድ ሲያሞካሹ፣የህወሓት አመራሮች በስብሠናል ካላችሁ የበሠበሠ ነገር ከህዝብ ጋር አብሮ ከኖረ በሽታ ነውና ለምን ዞር አትሉልንም ብለዋችሁዋል።
በዚህ ፍጹም ኢትዮጵያዊ መንፈስ በረበበት የምሁራኑ ውይይት እልፍ ጉዳዬች ተነስተዋል።ከምንም ከምንም በላይ ብዙ አስተማሪና መሳጭ ታሪኮች ቀርበውበታል።የቻላችሁ ሁሉ እንደምንም እንድታዩት እመክራለው።
በዚሁ አጋጣሚ እነ ዶክተር አረጋዊ ለሠጣችሁት እጅግ መሳጭ ኢንተርቪው ላመሠግናችሁ እወዳለው።
የተለመደ አድናቆቴ ለጋዜጠኛ ቤተልሄም ይድረስ።እንዲህ አይነት ኣፍ ቁምነገር ተጠናክሮ ይቀጥል።
Filed in: Amharic