>

ከወደ ሰሜን የጦር ነጋሪት እየጎሰመ ነው! ......" (ጌታቸው ሽፈራው)

ከወደ ሰሜን የጦር ነጋሪት እየጎሰመ ነው!
ጦር አውርድ ባዩ በዝቷል!!!”
ጌታቸው ሽፈራው
ሰሞኑን የጦርነት ነጋሪት ሲመታ ሰንብቷል።  የነጋሪቱ መሰረት ደግሞ የጣና በለስ ፕሮጀክት ሰራተኛ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተገድለዋል ተብሎ ነው።
የመጀመርያው ነገር ሰዎቹ ተገደሉ የተባለበት መንገድ ማንነትን መሰረት  ያላደረገ  እንዳልነበር ነው። የኢንጅነር ስመኘው ቀብር ስነ ስርዓትን በቴሊቪዥን ሲመለከቱ መብራት አጠፉብን ያሏቸውን ጋር በተነሳ ጊዜያዊ ፀብ መሆኑ ተነግሯል። ይህ ጊዜያዊ ግጭት ነው የተባለው ወደ ማንነት አዙረው አገር ይያዝ አሉ።
ብአዴን የሚባል ታዛዥ ያሉትን ሳያጣራ ማንነት ላይ የደረሰ ጥቃት ነው ብሎ መግለጫ ሰጠ። ከዚህ ቀደም ኦሮሚያ ውስጥ ተመሰሳይ ነገር ተፈፅሟል ሲባል፣ እነ አዲሱ አረጋ ማብራሪያ ሲፅፉ እነ አቶ ንጉሱ ጥላሁም ተከትለው፣ “በግለሰብ ፀብ የተነሳ ነው” እያሉ  ሲያስተባብሉ አይተናል። ይህኛውንም የተባለውን ተከትለው በማንነት ነው ብለው መግለጫ አወጡ
የትህነግ አክቲቪስቶች “አንድ ኤርትራዊ ዝርያ ያለውም ተገድሏል፣ ስለዚህ በትግርኛ ተናጋሪው ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ነው”  የሚል ርካሽ ፕሮፒጋንዳን ሲያራምዱ የትግራይ ኮምኒኬሽን ቢሮም በተመሳሳይ “በትግርኛ ተናጋሪ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ነው” ብሎ የቅስቀሳ መግለጫ ሰጠ። በኤርትራዊያንም ጭምር ነው ማለታቸው ነው። ለመጀመርያ ጊዜ በብሄር ግጭት ተገደሉ ለተባሉ ሰዎች   ባለስልጣናት ቀብር ላይ ተገኝተው ጉዳዩን አጦዙት። በነጋታው ደግሞ ሴቶችን ሳይቀር መሳርያ አስይዘው ሰልፍ ወጡ። አማራ ነው የተባለን እየፈለጉ አሰሩ።
ዛሬ ሸገር  ሬድዮ የፕሮጀክቱን ኃላፊዎች አነጋግሮ አንድ ዜና ሰርቷል። የሀሰት ወሬ ነው ተብሏል።
ለዚህ የሀሰት ዜና ሲባል ናይጀሪያ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ፎቶ ተለጥፏል። የትህነግ አክቲቪስቶች ጦርነት ናፈቀን ያሉና ለዚህ ጉዳይ በተወጣ ሰልፍ መሳርያ ይዘው የወጡን ሰዎች ፎቶ መቀስቀሻ አድርገዋል። ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት መደረግ የለበትም ያለው የትግራይ መንግስት ጉዳዩን የማያውቁትን ምስኪኖች አስሯል። አስደብድቧል። የትህነግን ትዕዛዝ ተከትለው ሳያጣሩ መግለጫ ያወጡት እነ ንጉሱ ጥላሁን ለዚህኛው ጥቃት መልስ የላቸውም።
ይህ ሁሉ የሀሰት ወሬ እንግዲህ ከጦርነት ናፍቆት መሆኑ ነው፣ ጦርነት አታሳጣን ነው ፀሎታቸው። ፀሎታቸው ሳይሰምር ሲቀር ደግሞ በሀሰት ወሬ የጦርነት ነጋሪት ይጎስማሉ። ጉዳዩን የማያውቁት ምስኪኖች ላይ ጦርነት ተከፍቷል።
Filed in: Amharic