>

ኦነግ ከቀደመ ስህተቱ ተምሮ ሰራዊቱን ከነ ትጥቁ አስገብቷል!!! (ጌታቸው ሽፈራው) 

ኦነግ ከቀደመ ስህተቱ ተምሮ ሰራዊቱን ከነ ትጥቁ አስገብቷል!!!
ጌታቸው ሽፈራው 
የሽግግር መንግስቱ ወቅት ትህነግ የቀለደበት ኦነግ በዚህኛው ወቅት መሳርያውን ይዞ እየገባ ነው። ከታጣቂዎቹ መካከል ድርድር የተዋጣለት ኦነግ ይመስላል። አብዲ ኤሊ የኦሮሞን ሕዝብ እየጨፈጨፈ ነው።  የትህነግ አጋዚ አሁንም አለ። ነገ ኦነግ ሰራዊቱ ይጠቃለልኝ ብሎ ይደራደር ይሆናል።  ይህ  ባይሆን ከእነ ሙሉ ትጥቁ ያሰፍረዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 እና አዲኃን ሰራዊት መሆን የነበረበት/ያለበት እንደዚህ ነበር። ብአዴን ወደ አስመራ ሄዷል። ብአዴን ይህን ጥያቄ ማንሳት አይችልም እንጅ ኤርትራ ያለው የሁለቱ ድርጅቶች ሰራዊት ከእነ መሳርያው ገብቶ ደለሎ አካባቢ መስፈር ነበረበት። ይህ ሰራዊት  ኑሮውን ለመግፋት የሚያስችል አጋጣሚ ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን  የትህነግ/ህወሓት ሰራዊት  ለማይቆምለት የአማራ ገበሬ ደጀን መሆን በቻሉ ነበር።
አሁንም መደራደር ከተቻለ መሆን የሚገባው ይኸው ነው። የአርበኞች ግንቦት 7 እና የአዴኃን ሰራዊት አብዛኛው ገበሬ ነው። ወጣቶች ናቸው።  መሳርያ ፈትተው ሌላ አማራጭ የላቸውም። የሱዳን ጦር በቅርቡ የለቀቀው ደለሎ አካባቢ ከእነ መሳርያቸው ቢሰፍሩና ሰላማዊ ህይወታቸውን ቢገፉ ለአማራ ገበሬ ብቻ ሳይሆን ሉአላዊነቱን በማስከበርም ቀላል የማይባል ሚና በተወጡ ነበር።
ችግሩ ብአዴንም አይጠይቅም፣ ድርጅቶቹም የተደራደሩ አይመስልም። ትህነግም አይፈልገውም። ነገ በወልቃይት ጉዳይም በርረው የሚደርሱ ይመስለዋል።
Filed in: Amharic