>

ጭቆናን ማስወገድ ሆነ ዴሞክራሲን መገንባት የሚቻለው የፍርሃትን ግንብ በማፍረስ ነው! (ስዩም ተሾመ)

From Authoritarian to Democratic Order” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ “The Role of Intellectuals in Political Transition” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ በእርግጥ ውይይቱ በተለያዩ በሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ በመድረኩ ላይ ከተናገርኩት በተጨማሪ በፅሁፍ ያዘጋጀሁት “Slide” አለ፡፡ ይህ ስላይድ ሁለት የቪዲዮ ምስሎችን ያካተተ ነው፡፡ የፅሁፉን ይዘትና አቀራረብ ለማየትና ለማንበብ የምትሹ ይሄን ሊንክ በመጫን ማውረድ ትችላላችሁ፡፡ አቀራረቡ እንደ ስላይድ ባይሆንም ፅሁፉን ከቪዲዮ ምስሎቹ ጋር አጣምሮ ማየት ለምትሹ ደግሞ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

Presenter: Seyoum Teshome, Ambo University

1. “ምሁር” እና “ሙር”

  • “ምሁር” ማለት “በትምህርትና ዕውቀት የበሰለ አዕምሮ ያለው ሰው።”
  • ለውጥና መሻሻል ለማምጣት የማያስችል ትምህርት ሆነ ዕውቀት ፋይዳ-ቢስ ነው።
  • ምሁርነት ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት ጋር የተቆራኘ ነው፤

“The intellectual is the individual endowed with a faculty for representing, embodying, articulating a message of you, attitude, philosophy or opinion to as well as for a public in public. This role has an edge to it, and cannot be played without the sense of being someone whose place it is, publicly, to raise embarrassing questions, to confront orthodoxy and dogma rather than to produce them, to be someone who cannot easily co-opted by governments and corporations.” Edward Said (1993): Representations of an Intellectual – Reith Lectures 1993.

  • የሕዝብን ጥያቄና አመለካከት የሚወክሉና የሚገልፁ፣ አሣፋሪ ጥያቄዎችን በአደባባይ የሚያነሱ፣ ኋላቀር አመለካከቶችን የሚጋፈጡ፣ ለመንግስትና ድርጅቶች ፍላጎት ተገዢ ያልሆኑ ሰዎች “ሙር” ይባላሉ።
  • “ሙር” ማለት “የተማረና ዕውቀት ያለው ሆኖ ወፈፍ ስለሚያደርገው ብዙ የሚለፈልፍና የሚናገር፥ ንግግሩ ግን ፍሬ ነገር ያዘለ ሰው”

2. ምሁራን እና መንግስት

  • መንግስት ሀገር የሚያስተዳድረው በብዙሃን አመለካከት አማካኝነት ነው።

“Rule is the normal exercise of authority, and is always based on public opinion. Never has anyone ruled on this earth by basing his rule essentially on any other thing than public opinion.” The Revolt of the Masses, Ch. XIV, Page 73.

  • ምሁራን ለውጥና መሻሻል ለማምጣት የብዙሃኑን አመለካከት መቀየር አለባቸው።

“Every intellectual has an audience and a constituency. The issue is whether that audience is there to be satisfied or challenged. But in either case, there is no getting around authority and power, and no getting around the intellectual’s relationship to them.” Edward Said (1993): Representations of an Intellectual, Reith Lectures 1993.

  • የብዙሃኑን አመለካከት ለመቆጣጠር በሚደረግ ጥረት በምሁራን እና መንግስት መካከል ግጭት ይፈጠራል።

2.1 ዴሞክራሲያዊ ስርዓት

  • መንግስት ሀገርና ሕዝብ ያስተዳድራል፣
  • ምሁራን የብዙሃኑን አመለካከት እና የመንግስትን ሥራና አሰራር ይቆጣጥራሉ።

“….Their part is to indicate wants, to be an organ for popular demands, and a place of adverse discussion for all opinions relating to public matters and, along with this, to check by criticism, and eventually by withdrawing their support, those high public officers who really conduct the public business. …There are no means of combining these benefits except by separating the functions which guarantee the one from those which essentially require the other; by disjoining the office of control and criticism from the actual conduct of affairs…” Representative Government, Ch.5: P.59

2.2 ጨቋኝ/አምባገነናዊ ስርዓት

  • ጨቋኝና አምባገነናዊ መንግስት የብዙሃኑን አመለካከት በበላይነት ለመቆጣጠር ይሻል።
  • የምሁራኑን ሃሳብና እንቅስቃሴ ካልገደበ የብዙሃኑን አመለካከት መቆጣጠር አይችልም።
  • የምሁራን ሃሳብና እንቅስቃሴ ከተገደበ ለውጥና መሻሻል ማምጣት አይችሉም።
  • በመሆኑም ምሁራን እና ጨቋኝ መንግስት ዓይንና ናጫ ይሆናሉ።
  • የተወሰኑ ምሁራን መንግስታዊ ስርዓቱን ለመቀየር በፖለቲካዊ ንቅናቄ ውስጥ ይሳተፋሉ።
  • መንግስት ምሁራኑን ለእስር፥ ስደትና ሞት ይዳርጋል።
  • እውነትን ማወቅና መጠየቅ ጥፋት፣ መናገርና መፃፍ ወንጀል ይሆናል፤
  • “እብደት” ነፃነት ይሆንና ምሁራን “ሙር” ይባላሉ!
  • ዕውቀት ፍርሃት ሆኖ ፍርሃት ዕውቀት ይሆናል!

“እያዩ ፈንገስ” – ደራሲ:-በረከት በላይነህ፣
ተዋናይ:- ግሩም ኤርሚያስ

3. ፖለቲካዊ ሽግግር እና የምሁራን ሚና

3.1 ፍርሃትን ማሸነፍ

  • እንደ ፖለቲካዊ እንስሳ “እኩልነት” የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው።
  • ዴሞክራሲ ደግሞ በእኩልነት መርህ ላይ የተመሰረተ ስርዓት ነው።
  • ጨቋኝ ስርዓት የአንድ ወገን የበላይነትን በማስቀጠል ላይ የተመሰረተ ነው።
  • ፍርሃት የእኩልነት ጥያቄ እንዳይነሳ፣ የአንድ ወገን የበላይነት እንዲቀጥል ያደርጋል።
  • ለውጥና መሻሻል ለማምጣት ምሁራን ከፍርሃት ነፃ መውጣት አለባቸው።
  • ጨቋኝ መንግስት ደግሞ ሁልግዜም ምሁራንን ይፈራል፥ ያስፈራራል።
  • ስለዚህ የምሁራን ቀዳሚ ተግባር ጨቋኝ ስርዓትን ለማስወገድ መታገል ነው!
  • ይህን ለማድረግ በቅድሚያ ፍርሃት ማሸነፍ ይጠይቃል!

3.2 ብሔርተኝነትን መግራት

  • ለትግሉ የሚያስፈልገውን ሕዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር በሚደረገው ቅስቀሳ በማህብረሰቡ ዘንድ የወገንተኝነት ስሜት፣ በጨቋኞችና ጭቆና ላይ ጥላቻ ይሰርፃል።
  • ብሔርተኝነት በወገንተኝነትና ጥላቻ ስሜት ላይ የተመሰረተ የትግል ስልት ነው።
  • በዘር፥ ሀገር ወይም ብሔር ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል።
  • ህዝባዊ ንቅናቄውን ከመፍጠር የዘለለ ፋይዳ የለውም።
  • ከትግሉ ዓላማ – እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጋር ይቃረናል
  • ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት አያስችልም
  • ጨቋኙ ስርዓት ከተወገደ በኋላ አመለካከቱ መቀየር አለበት።
  • የብሔርተኝነት ስሜቱን መግራት ካልተቻለ ጭቁኖች ተመልሰው ጨቋኝ ይሆናሉ።

3.3 የፍርሃትን ግንብ ማፍረስ

  • ፍርሃት በዜጎች መካከል የእርስ-በእርስ ግንኙነት እና የህግ ዋስትና እንዳይኖር ያደርጋል።

“Terror substitutes for the boundaries and channels of communication between individual men… The stability of laws, erecting the boundaries and the channels of communication between men who live together and act in concert, hedges in this new beginning and assures its freedom.” Hanna Arendt (_), On the Nature of Totalitarianism: An Essay in Understanding: 329-360

  • ጨቋኝ ስርዓት ለማስወገድ ሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት “የፍርሃትን ግንብ ማፍረስ” ያስፈልጋል።
  • በዜጎች መካከል የተቋረጠውን የግንኙነት መስመር መልሶ መቀጠል
  • የዜጎች መብት ዋስትና እንዲኖረው የሕግ የበላይነትና ፍትህን ማረጋገጥ
Filed in: Amharic