>
5:18 pm - Tuesday June 16, 7767

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ለታማኝ በየነ ከሁለት በላይ መድረክ ሊያዘጋጁለት ይገባል!!! (ኣስገደ ገብረስላሴ-መቀለ)

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ለታማኝ በየነ ከሁለት በላይ መድረክ ሊያዘጋጁለት ይገባል!!!
ከኣስገደ ገብረስላሴ –  መቀለ  
የመንግስትና የተፎካካሪ ፓርቲ ፖለቲኮኞች የታማኝ አይነት ኣመለካከትና ቅንነት  10%  እንኳን ቢኖሯቸው ሀገራችን ምንኛ ባደገች ነበር ? 
እኔ ለኣርቲስት ታማኝ በየነ ኣሜሪካ ለህክምና ሄጀ ሶስት ጊዜ ኢህኣዴግ እንዳያውቅና “ኣሸባሪ ታማኝ በየነ ጋር ተገናኜ” ተብዬ ቅሊንጦ ወስደው ወደ እነ ኣብርሃ ደስታ እንዳይቀላቁሉኝ  ፈርቼ  በድብቅ ኣግኝቼው  ስለሃገራዊ ጉዳይ ተወያይተን ነበር ።
ታማኝ ስለ ኢትዮጵያዊነት ሲተነትን በሆነ መንገድ የኢህኣደግ ኣማራርና የተፎካካሪ ፓርቲዎች የማይተነትኑት ሃሳብ ኣግንቼለት ነበር ።
እንደታማኝ በዬነ ቅን ኢትዮጵያዊ ኣስተሳሰብ ያለው ዜጋ ወይ ሙሁር እንደሌለ ለጥቂት የቅርብ ጓዶኞቼ የተወሰነ ተናግሬ ነበር በተረፈ ግን ተንፈስ ብዬ ኣላውቅም ።
ዛሬ ግን ሰሞኑን በጎንደርና በባህርዳር በኣደባባዮች በኣዳራሾች ፣ ከመላው የክልሉ ህዝብ ፣ ወጣቶች በቆራጥነት ያለኣንዳች ስጋት በኢህደን ኢህኣደግ ሚዲያ   ሲናገረውና ሲያስተላልፈው የሰነበት ስለ ስለኢትየጵያዊነት ፣ ስለኣንድነት በተናገረው ከገመትኩት ካሰብኩት በላይ  ረካሁበት ።
 በተጨማሪ የታማኝ በዬነ ኣነጋገር በመላው ሀገራችን  ላሉት ሙሁራን ተማሪዎች ፣ ወጣቶች ፣ ለእድሜ ባለጸጋዎች ፣ ለኣክቲቪስቶች ያስተማረ ፣ እሩቅ  ሄደው ማንነታቸው እንዲመለከቱ ያደረገ እጅግ ቅን ሊሂቅ ዜጋ ኣድርጌ ተቀብዬው ኣለሁ ።
በእኔ እምነት የትግራይ ክልል ባለስልጣናት እንዲፈቀዱለት  በትግራይ ክልል ከሁለት በላይ መድረክ ተሰጥቶ  መግለጫ ቢሰጥ ለትግራይ ህዝብ ልክ እንደጎንደር መልእክት ቢያስተላልፍ የክልላችን መሪዎች ያለኣንዳች ተጽእኖ ሁኔታው እንዲያማቻቹለት ጥሬን ኣቀርባለሁ ።
ኣርቲስት ታማኝ በየነም ወደ ትግራይ እንድትመጣ ራስህም ግፊት ብታደርግ ።  ታማኝ በየነ ሃሳብህን እጅጉን ተመችቶኛል ሁለችንም ከጎንህ ነን ።
Filed in: Amharic