>

በአዋጅ ያልታወጀ ያለመከሰስ መብትን የተጎናጸፈው ቄሮ ማን ነው?? (የሰሜኑ ቋያ)

በአዋጅ ያልታወጀ ያለመከሰስ መብትን የተጎናጸፈው ቄሮ ማን ነው??
የሰሜኑ ቋያ
በዶ/ሩ   ” ዘጠኝ  ድስት  ተጥዶ  እየፈላ ነው  የትኛውን  ድስት  አማስለው አጣፍጠው  ጥሩ ‘ወጥ’ ያደርጉት ይሆን ??”  ይህንን ከፈጣሪ በቀር እንኳን ሌላው እርሳቸውም አያውቁትም::
  
  ዶ/ር አብይ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም  ፖለቲከኛ  ማህበራዊ  መሰረቱን  ማስከፋትና  ማስቀየም  አይፈልግም  ከማህበራዊ  መሰረቱ  ጋር  የተጣላ  ፖለቲከኛ  በሁለት  ቢለዋ  ይወጋል
   1- የእራሱ ሃይል የነበረው
   2- ድሮውንም  ይቃወሙት  በነበሩት  ሃይሎች
ስለዚህ  በሁለት  ቢለዋ  ከመገዝገዝ  ችግሩን  እየደፋፈንክ  ማህበራዊ  መሰረትህን  መንከባከቡ  አዋጭ  ነው  ይላሉ  ፖለቲከኞች::
የዶ/ር አብይ  ማህበራዊ  መሰረት ደግሞ ቄሮና  ከሁሉም ቢሄሮች  የወጣው  ለውጥ ናፋቂ  ህዝብ ነው
 ዶ/ሩ  አምቦ  ከተማ  ላይ  ባደረጉት  ንግግርም  በቄሮ  መስዋዕትነት  እኛ  ወደ ፊት  መጥተናል  እኛ  የእናንተ  ወኪል ነን ብለዋል ስለዚህ  ይህ ሃይል  ምንም ቢያጠፋ  አሳልፈው  አይስጡትም  ምክንያት ማን ሞኝ አለ ማህበራዊ መሰረቱን  ንዶ  ብቻውን  የሚቆም ??
  ስለዚህ  ማጥፋቱን  ቄሮ  ያጠፋል !!! ቢሆንም ግን ማንነታቸው ያልታወቁ  ገንዘብ የተከፈላቸው ስዎች ናቸው ያጠፉት  ይህንንም አጣርተን ስንጨርስ  ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ተብሎ  እንድታለፍ  ጥረት ይደረጋል ::
ለመሆኑ እንዲህ የሰራው ወንጀል ሁሉ የሚድበሰበስለትን በአዋጅ ያልታወጀ ያለመከሰስ መብትን የተጎናጸፈው ቄሮ ማን ነው??
ከጀርባ ሆነው የሚዘውሩትስ እነማን ናቸው?
በአሁን ሰአት የዶ/ር አብይ መንግስት ለማንኛውም ኢትዮጲያዊ በሀገር ውስጥ በግልጽ እንዲደራጁ በሩን ብርግድ አድርጎ ከፍቷል። በዚህም መሰረት በስደት ያሉ ግለሰቦችም ፣ በግልጽም በህቡእ የተደራጁ ድርጅቶችም ፣ መሳሪያ አንግበው ለዘመናት የታገሉትም ጭምር በሰላማዊ መንገድና በግልጽ ተደራጅተው ዲሞክራሲያዊ ትግል ለማድረግ ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል።  ለምንድነው ታዲያ ቄሮ አሁንም ህቡእ ድርጅት የሆነው? አመራር የሚሰጥ አካል ከሌለው መንግስት ይህንን አደገኛ ቡድን መበተን አለበት።  ይሄ አሸባሪነት ነው። አመራር ካለው ደግሞ ሀላፊነት ሊወስድና ለጠየቅ ይገባል።
—-
ሌላው  የዶ/ሩ  ሶስት ፈተናዎችም  አሉባቸው
1- የአንድነት  ሃይሉ  -“እርስዎኮ  ከብዙ  መቶ አመታት  በኋላ  ከእግአአብሔር  ለኢትዮጵያውያን  የተላኩ  መሲህ ነዎት” የሚል  ማጀገን አለ
 እና ዶ/ሩ  ወደ ብሄር ጉዳይ  ገብተው ይህንን ማጀገንና  መካብ ቸለል ብሎ  የሚያልፍ  ልዕልና  ይናራቸው ይሆን ካልን  አይኖራቸውም ነው  መልሱ
2- የአማራ ብሄርተኝነት ጉዳይም ሶስት ነገሮችን እንደሚያስከትል  ጠርጥረው ነበር የአንድነት ሃይሉም ይህንን ፍራቻውን እየተርበተበተ  ሲያላዝን ነበር
  ሀ- አማራ  በብሄር  ከተራጀ  የአንድነት ጉዳይ  በቀጥታ  መቃብር ላይ አበባ ጉንጉን ከማስቀመጥ  የባስ  ጅልነት ነው
ለ- ሌሎች ብሄረሰቦችም  ይህንን ፈለግ ተከትለው ከሄዱ  ጭራሽ  አስቸጋሪ  ነው
ሐ- የአዲስ አበባ  ጉዳይ  ከጥቅም ጠያቂነት  በዘለለ  የህግ ጥስት ጥያቄን ወልዶ  ጉዳዩ  ከፍ ይልና አተርፍ ባይ  አጉዳይ ያደርገናል የሚሉ  ናቸው
3- ከመከላከያ  ከቴሌ  ከአዲስ አበባ አስተዳደርና  ከደህንነት  ተቋማት  የተባረሩ  የትግራይ  ተወላጆች  መቀሌ  መሽገዋል ይህንን ሃይል በህግ መጠየቅ የሚያስችል መረጃም ማስረጃም  በእጃቸው ቢኖርም  የግላቸውን ስብዕና  ለማሳመር በሚል
    1- ቀስ ብዬ  እርምጃ  እወስዳለሁ
    2- ቀስ በቀስ ጉዳዩ  ይረሳና በይቅርታና በመደመር  ቀመር ተረሳስቶ  ይቀራል
እኔም:– የአገሪቱ  የመቻቻልና የፍቅር እንድሁም የሁሉንም ህዝብ ስሜት የገዛ  መሪ ወይም ንጉስ እሆናለሁ የሚል  ህልም ነው
  በአጠቃላይ  በዶ/ሩ   ” ዘጠኝ  ድስት  ተጥዶ  እየፈላ ነው  የትኛውን  ድስት  አማስለው አጣፍጠው  ጥሩ ‘ወጥ’ ያደርጉት ይሆን ??”  ይህንን ከፈጣሪ በቀር እንኳን ሌላው እርሳቸውም አያውቁትም::
  እግዚአብሔር  ይህችን አገር በቃሽ ይበላት!!
 በመጨረሻም
-በየትኛውም ከየትኛውም ብሄር ያለምንም  ጥፋታችሁ  ለሞታችሁ ለተጎዳችሁ ፈጣሪ  በእቅፉ ውስጥ ያኑራችሁ አሜን!!
 -ከትግራይ ኦንላይን እስከ ስፈር ወረኞች  ለዚህ ግጭት መባባስ  ህወሃት ያስማራችሁ  የእኛዎቹ  ከይሲዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!
የደከማችሁበት  ስራ  ፍሬ አፍርቷል ሰይጣንም  እንቅልፍ የሚተኛውኮ  እናንተ እርሱን ተክታችሁ እንደምትስሩ በመተማመን አይደል??!!!
Filed in: Amharic