>
10:29 am - Monday August 15, 2022

ለካቴና የተፈጠረ እጅ!! (እየሩሳሌም ተስፋው)

ለካቴና የተፈጠረ እጅ!!
እየሩሳሌም ተስፋው
ይሄ እጅ ለካቴና የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ ምናልባት ለአስራ አምስተኛ ግዜ ዛሬም ካቴና ገብቶበታል።
ክሶቹም ከያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ጀምሮ ህዝብን ማነሳሳት ፣ ህገመንግስቱን በሃይል ለመጣል (በተደጋጋሚ ግዜ) እና ዋናው ክስ ሽብር ናቸው ያሁኑ ገና አልተለየም።
በተደጋጋሚ ግዜ አብረን ብንታሰርም አብዛኛውን ግዜ የመጀመሪያ ታሳሪ ግን ከመሃላችን ብርሃኑ ነው።
እስካሁን ከግራውድ አልወጡም ጨለማ እና ቀዝቃዛ ክፍል ከተቆለፈባቸው ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸው።
ብርሃኑን ሁለት ግዜ በመርማሪው በኩል አግኝቼዋለሁ  እጁ ላይ የተያዘው ገንዘብ በተመለከተ ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ ሄደን ”ለእራት ልትከፍል እንደነበር አጣርተናል ግጭቱ የተፈጠረ ግዜም አዲስአበባ እንዳልነበርክ አረጋግጠናል አሉኝ” አለኝ
”እና ምን ቀራቸው? መኩንስ ምንድነው የሚሉት” አልኩት?
አንድ አይነት ነው ምርመራችን የስልክ ማስረጃ አለን ይላሉ ፈገግ እያለ አስቂኞች ናቸው ልጆች ደውለው ይሄን ያህል ሰው ሞቷል ለሚዲያ አሳውቁልን ሲሏችሁ እሺ ብላችኋል ይሉናል።
የአርበኞች  ግንቦት 7 አመራሮችና አባላት የስልክ ንግግር  በደሕንነት ሰዎች እንደሚጠለፍና የስልክ ምልልሱንም ለክሱ ማጠናከሪያነት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አንዳችም ለዛ የሚያበቃ ነገር ባለመገኝቱ ክሱን ወደ ተራ የሌብነት ወንጀል እና ህዝቡን ለአመጽ ማነሳሳት ወደሚል ለማዞር ተገደዋል።
ሌላ ለምን አባል ሆናችሁ ?  ስለአቀባበሉ መግለጫ ለምን ሰጣችሁ?  አርፎ የተቀመጠውን ህዝብ እናንተ ናችሁ ቀስቅሳችሁ አርፎ እንዳይቀመጥ ያረጋችሁት የኮሚቴውን አባላት ስም ዝርዝር ያመጡና ከነዚህ ውጭ ማን አለ? ይሉናል ብቻ ይሄን መሰል አስቂኝ ጥያቄ ነው የሚጠይቁን በር በተከፈተ ቁጥር ማንን አመጡ ብለን ከመሳቀቅ በቀር ከመኮንን ጋር አንድ ላይ ስላደረጉን ከሱ ጋር ስናወራ እንውላለን ከበፊቱ ይሻላል እያለኝ ፖሊሱ ሰዓት እንዳለቀ ነገረን ሰላም ተባብለን ተለያየን።
Filed in: Amharic