>

"የህወሀው ምስጢራዊ ዋሻ እና ስውር ወንጀሉ ሲጋለጥ!!!" (ጌታቸው ሽፈራው)

የህወሀው ምስጢራዊ ዋሻ እና ስውር ወንጀሉ ሲጋለጥ!!!”
ጌታቸው ሽፈራው
ከታማኝ ምንጭ የደረሰኝ መረጃ ነው!
“ሕወሐት ተከዜ ግድብ አጠገብ ማየ ዮርዳኖስ ከሚባል ቦታ ከተከዜ ሸለቆ ጀምሮ ወደአቢየአዲ እና መቀሌ የሚያደርስ እጅግ በጣም ትልቅ የሆነ የውስጥ ለውስጥ ዋሻ እና የመኖሪያ ዘመናዊ ቤቶች የእቃ መጋዚኖች ከ1993 ዓ/ም ጀምሮ ከ10 ዓመት በላይ የፈጀ በቻይናውያን ባለሙያዎች ተሰርቷል።
የሚያሳዝነው ግን ዋሻው ሲሠራ በቀን ሠራተኛነት ሲሠሩ የነበሩ ለጊዜው የታወቁ 38 አማራዎች (የበየዳ ልጆች) አፈር ተንዶ ተጫናቸው፣ ኤሌክትሪክ ያዛቸው እየተባለ ሞተዋል ተብሎ ለቤተሰቦቻቸው ተነገረ። ነገር ግን አንድም ሰው አስከሬናቸውን እንዳያይ የተቆለፈ ሣጥን እያሳዩ እንደቀበሯቸው ከሟች ቤተሰቦች አንዱ አውርቶኛል።
ከዋሻው ዳር ለዳር ሲሠሩ ከነበሩትም የተቆለፈውን ሣጥን ከማያታቸው ወጭ አማሟታቸውንም ሆነ አስከሬናቸውን አይተናል የሚል አልተገኘም።
ሌላው ገደሉ በሚደረሠስበት ጌዜ እና ዋሻው በሚሠረሠርበት ወቅት የሞተ ሰው አልነበረም ሞቱ የተባሉት ሥራው ማጠናቀቂያ ወቅት ነው ። አስከሬናቸው አልተገኘም ተብሎ የተነገራቸውም አሉ። ከሟቾች መካከል እጅግ ጠንካራ ሠራተኞች የነበሩ እና ዋሻው ውስጥ ገብተው ለረጅም አመት ሲሠሩ ቆይተው በመጨረሻ ሞቱ የተባሉት :-
1ኛ ከፍያለው ውብስራ ንጋቱ
2ኛ መሠለ የሚባሉ እና ሌሎችም አሉ። የቀሩትን ሟቾች ዝርዝር እያጣራሁ ነው። በአሁኑ ወቅት የመብራት የውኃ እና ሌሎችም አግልግሎቶች ተሟልተው ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን እንዲሁም የመካናይዝድ የጦር መሣሪያዎች ገብተው እንደተከማቹ የዓይን እማኞች ይናገራሉ።”
Filed in: Amharic