>

የላሊበላ በርካታ አደጋዎችና የታሰበው ነጠላ የማዳን እርምጃ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ“ እንዳይሆን። (መንገሻ ዘውዲ ተፈራ)

የላሊበላ በርካታ አደጋዎችና የታሰበው ነጠላ የማዳን እርምጃ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ“ እንዳይሆን።

መንገሻ ዘውዲ ተፈራ
የኢትዮጵያ መንግስት በመጨራሻ 12ኛ ጉባኤው ቱሪዝምን አንደ አንድ የሐበት አመንጭ ማየቱ አጅግ ትክክለኛ ሐሳብ ነው። ቱሪዝም በተለይ ለአማራ ክልል ከትልቁ ግብርና አኩል ዋጋ ያለው ነው። ሰለአጠቃላይ የኢትዮጵያ ቱሪዝም በየቱሪዝም ሐብቶቹ ዓይነት፤ አሁን የሚገኙበት ሁኔታና ስለ ተደቀነባቸውን ፈተና ወደፊት በዝርዝር እመለስበታለሁ።
አሁን ግን መነሻየ ሰለሆነው በመፍረስ አደጋ ላይ ሰለሚገኘው የቅዱስ ላሊበላ ስሪቶች “የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት“ በአቅሜና በተረዳሁት መጠን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያውቃቸው የሚገቡ ናቸው ብየ ያመንኩባቸውን ለማድረስ ነው።
የላሊበላ ወቅር አብያተ ክርስቲያናት በዓለም ቅርስ ሐብትንት ከመመዝገብ በተጨማሪ በዓለም ካሉ አሰደናቂና አስደማሚ ክሰተቶች አንዱ ነው።
ቱሪስቶች ወደ ሐገራችን ኢትዮጵያ ለመምጣት የመጀመሪያ የሀሳብና ፍላጎታቸው መነሻ ምናልባትም ብቸኛ ምክንያት የላሊበላ ወቅር አብያተ ክርስቲያናት መገኘት ነው። ከዚህ የምናገኛቸውን ቱሪስቶችም ሆነ በየትኛውም ዓለም ስንንቀሳቀስ ሰለ ኢትጵያ በዓለም ካርታ ላይ መኖር መረጃ ያላቸው ከሆኑ የመጀምሪያ የሚጠየቁት ስለ አስደናቂውና አስደማሚው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ሲገልፁትም (you have a miracle art work result, rock hewn church which I want visit) ነው።
ከአፈ ታሪከ ከሚነገረውና ቅዲስ ላሊበላ አልፎ አልፎ ጀምሮአቸው ነበር ከሚባሉት በመላው ኢትዮጵያ በተለይ በአማራ ክልል ላስታ ላሊበላ ዙሪያ፦ በጌምደርና ሰሜን ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ክምር ድንጋይ ወቅሮ ላሊበላ ጃንአሞራ ሰረባል መድሐኒ ዓለም፤ ወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሰቆጣ  መስቀለ ክረሰቶስ እና በተለይ ወደ ላሊበላ እየተጠጋን ሰንሄድ አጅግ ብዙ ጅምሮች እንደተረዳሁት ቅዱስ ላሊበላ አሁን የምንነጋገርበትን የላሊበላን ውቅር አብያተ ክርሰቲያናት ለመገንባት ምቹ የሆነ ሰፍራን ሲመርጥ አንደነበርና መጨረሻም ይህንን ትክክለኛ ቦታ ሲያገኝ ስራዎቹን አንደከወነ ነው።
አሁን በአደጋ ላይ የሚገኘው “የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት“ የተሰሩበትን የመሬት አቀማመጥና ተፈጠሮ ስናይ፦ በደቡብ ኩል መስክን ሙጃን ተጠግቶ የተከዜ ወንዝ መነሻ ደልብ በሎም አሰከ ላይኛው አቡየ ተራራ፤ በምዕራብ ከውሮፕላን ማረፊያው በመነሳት ሹም ሽሃ ሲመኖ ሰኞ ገበያ ረባዳ መሬቱን ተከትሎ፤ በሰሜን ከሰኞ ገበያ በመራባርባ ከላይ መጫራሻው አፋፍ፤ በምስራቅ  ከዚሁ አፋፍ በመነሳት አሰከ አቡየ ተራራ ሰነሰለተማው ድልብ የተደላደለውን የተራራ ሽፋን እንደጣራ በመጠቀም በመካካል ያለውን አሰተማማኝ ቦታ መምረጡንና መጠቀሙን ነው።
በዚህ በተመረጠው ቦታ ውስጥ 11ዱን በቅርርብ በዙሪያ የሚገኙትን አሸተን ማረያም፣ ቅዱስ ናአኩ ተልአብና ገነተ ማሪያም ተገንብተዋል። በዚያ ዘመን አሰከ 1969 ዓ/ም አገልጋዮቹም ሆነ ኑዋሪዎቹ በዚህ ደንቅ የተቀደሰ ታአምራዊ ስፍራ ላይ ተፅእኖ የማይፈጠር በአካባቢው በሚሰበሰቡ ትንንሽ ድንጋዮች በጭቃ ልቁጥ ክብና የሳር ክዳን ቤቶች እየሰሩ ይኖሩ ነበር።
የላሊበላ መዳረሻነት በዓለም ሲታወቅና ጎብኘዎች ወደ ላሊበላ መምጣት ሲጀምሩ የተሰሩት የአንግዳ መቀበያ ሰባት ወይራና አሸተን ሆቴሎችም ትንሽ ለየት ያለ ቅረፅ ቢኖራቸውም አሰራራቸው ግን ምንም አይነት ጫና በማይፈጥሩ ሁኔታ ነበር። አሁንም አሩቅ ሳይሆን በ1968/69 የእንግዳው መብዛትና የአገልግሎት መስጫው መስፋፈት አስፈላጊነት ተከሰተሰ። በዚያ ዘመን የነበሩት ኃላፊዎችና የሀገር ባላባቶች ቀዳሚ ነው በለው ያሰቡት የአገልግሎት መስጫውን ከቤተ ክርስቲያኑ ማራቅ ነው። የዛሬን አያድረገውና ሩሃ ሆቴልና አሁን ቀደምት ሆቴል የተሰሩበት ለከተማው ሩቅ ቦታ ነበር። የሆቴሎቹ አሰራራም ሩሃ አሁንም የሚታይ ሲሆን በአሁኑ ቀደምት ላይ በቀ/ች ብርሃነ መስቀል የተሰራው ምንም አሻራ እንኳ የሌለው ተሰርቶ የነበረው በላሊበላዎቹ የጥንት ቤት አሰራር ይዘት በአካባቢው በሚሰበሰቡ ተንንሽ ድንጋዮች ክብና የሳር ክዳን ሆኖ ውስጣቸው ግን አጅግ ፊት በሚየሳይ አብነ በርድና ከወተት በነፃ ኮረኒስ ነበር። እጅግ የሚያሳዝነው ግን ቀደምት አባቶቻችን በራሳችን የቤተ ክርሰቲያን ትምህርት ብቻ በተገኝ ጥበብ እውቀትና የኃላፊነት ሰሜት ቅብብሎሽ ቅርሱ አሰከ አሁን ተጠብቆ የማንነታችን ትልቅ ምስክርና የኑሮአችን መሰረት እንዲሆነ አደድገዋል። እኛ ግን ዘመናዊ ትምህርት ተምረናል በተወሰነም የወጭውን ዓለም አይተናል  ከእኛ በላይ አዋቂነት ላሳር ብልን የምንደሰኩረው ያቆዩንን መጠቀም ቀርቶ በማጥፋት ላይ መገኛታችን ነው።
ብዙ አስረጅዎች ማቅረብ የሚቻል መሆኑ አንደተጠበቅ ሆን ከነዚህ መንደርደሪያ ሃሳቦች በመነሳት ጥቂቶቹን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ችግሮች በኃሳብ በመለዋወጥ ቢቻል ለማፅዳት አለበለዚያ ባለበት ለማቆየት የድርሻ ኃሳብን ለማበርከት ነው።
ለአብያተ ክርስቲናቱ መከላካያ የተሰራውን ክብደት ያለው ጣራ ማሰወግድና በሌላ ቀላል ለመተካት መወሰድ የሚገባው እረምጃ አንደተጠበቀ ሆኖ ከዚያ በፊትና ጎን ለጎንና በኃላም መወሰድ የሚገባቸውንም እርምጃዎች አያጠኑ መወሰድ ቢቻል።
ሰሚ በመጥፋት አንጅ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሰንጮኸበት የነበረውና ምናልባት አሁን ለተከሰተው መሰንጠቅም አስተዋፅኦ ሊኖረው የቻለው ከሙከጡሪ በዓለም ከተማ ጋሻና ላሊበላ ሰቆጣ ተንቤን የሚያልፈው ዋና መንገድ በአሽተንና በ11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያን መካከል የሚያልፍና ከፍተኛ የመሬት ንዝረት ያለው የመሰንጠቅ ብቻ ሳይሆን የላይኛው ከታችኛው በመገናኘት ምናልባት የመሬቱንም ይዘትና ቅረፅ ሊቀይር የሚችል ስጋት በመሆኑ በመጠርጠር ነገ ዛሬ ሳይባል በባለሙያ ተደግፎ እርምጃ ቢወሰድ።
ይህ በማህበረ ሰቡ መከፋት ይፈጥራል የሚል ስጋት አንደላው መገመት ይቻላል። ነግር ግን የላሊበላን በአጠቃላይ የላስታን ህዝብ ይህ መንገድ ወደ ፊት የሚፈጥርውን ጥፋትና ስጋቱን በትክክል ማስረዳት የሚችሉ ባለሙያዎችን በመጠቀም ማስረዳት አሰከተቻለ ድረስ የለላሊበላ ህዝብ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት በላይ ምንም ቅድሚያ የሚሰጡት አንደለለና በዚህም የማይደራደሩ ማንኛውንም መስዋዕትነት የሚከፍሉ ናቸው። ለዚህ ደግሞ እንደ ጊዜአዊ መፍትሄ ሊወሰድ የሚችለው፦ አሁን መስፋፈት ወደ አለበት አየር ማረፊያ አካባቢ ላይ ዕቃን ከከባድ ጭነትን ወደ ትንሽ ክብደት ጭነት በማቀያየር እና የህዝብ ማመላለሻም በድሮው ወደ ላሊበላ መግቢያ በሮሃ ሆቴል የሚያልፈው መንገድ አሰከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቱ ብቻ እንዲደርስ ማድረግ ይቻላል።
የላሊበላ የአሁኑ ግን የጥንት ከተማ ከአሁን በኃላ የተሸከመው ከብደት በቂው ሆኖ አነዚህም ወደፊት አቅም ሲገኝ ትክ በመክፈል የሚፈርሱ መሆናቸው ታሰባ ተደርጎ አይደለም ትልቅ ሕንፃ ትንንሽ ግንባታን ማቆምና አዲሱን የከተማ ማስፋፋትና ግንባታ የአየር ማረፊያውን ቀጭን አቫንና ተከዜን ተከትሎ በሹም ሸሃና ሲመኖ ወደ ሰኞ ገበያ ረባዳ መሬቱን ተከትሎ ማስፋፋት።
ሁሉንም ባለ ድርሻ አካለትን በማገናኘት ሰፊ ውይይት አድረጎ ቀደም ሲል በተገለፀው ክልል ውስጥ የሚገኘውን የቅዱስ ላሊበላ ክልል በፍፀም ገዳምነት መከለልና ከበካይ ዘመናዊነት ንክኪ በመከላከል ከመጭው ቁጥሩን ከማናወቀው ቢሊዮን ትውልድ የተበደርነውን የአደራ ሀብት ኃላፊነት በተሞላበት የድርሻችን ተጠቅመን ጠብቅን የማቆየትና የማስተላለፍ አደራችን ለመወጣት መስራት።
ወደፊት ከሚመሰረተው አዲስ የከተማ መስፋፈት ወደ ጥንቱ በገዳም የምንከልለው የላሊበላ ገዳም የሚደረግን እንቅስቃሴ ከተሸከረካሪ መጠቀም ወደ ባህላዊ በፈረስ በበቅሎ በሚድረግ ለመቀየር መስራት። ይህም የአካባቢውን የተፈጥሮ ማህበራዊ ባህላዊና አገልግሎት አሰጣጥ ተፈጥሮዊ ማህበራዊ ባህላዊ ይዘትና ቅርፅ ማስጠበቅ ሲያስችለን አሁን ያለውን የቱሪሰት ቆይታ በእጥፍ በማሰደግ ጥሩ ተከፋይ እንድንሆን ያስችለናል።
በመሆኑም የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ባህላዊ ቅርስ ሐብት የተወሰነ ሰው ወይም ቡድን ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያዊ አፈሪካዊ በሎም የዓለም በመሆኑ ይህን ሐብት ከተደቀነበት አጣዳፊ አደጋ ለመታደግ ያለምንም ፍረሃትና ስጋት ሁሉንም ባለድረሻ አካላት በማገናኘት አስቸኳይ መፍትሔ አንፍጠር።
ኢትዮጵያ ለዘላዓላም በክብር ትኑር። 

 

Filed in: Amharic