>
5:14 pm - Friday April 20, 9303

በጋምቤላ ምድር የተዳፈነው ረመጥ ወደ አስፈሪ ሰደድ እሳትነት ተቀይሯል!!! (ኡጁሉ ሌሮ)

በጋምቤላ ምድር የተዳፈነው ረመጥ ወደ አስፈሪ ሰደድ እሳትነት ተቀይሯል!!!
ኡጁሉ ሌሮ

ይህ የታላቋ ትግራይ ካርታ ነው እንግዲ ከየት ተነስቶ የት ድረስ እንደተሰመረ እያያችሁ ነው፣ ይህን ካርታ ያሰመሩ ሰዎች ግን የትግራይን ህዝብ ይወክላሉ ብዬ አላምንም ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ይገነጠላሉ ብዬ አላምንም። የዛሬ የጽሑፈ መነሻ ግን ስለትግራይ ለማውራት ሳይሆን ስለደቡብ ሱዳን ነው፣ ዱሮ ሱዳን እንዳሁኑ ለሁለት ሳይከፈሉ አንድ የጋራ አቋም ነበራቸው ይኸውም ጋምቤላ የሱዳን አካል ነች ብሎ ያምኑ እንደነበረ የተደበቀ ሚስቲር አይደለም።

አሁን ለሁለት ከተከፈሉ በኃላ ጋምቤላ የምታዋስነው ደቡብ ሱዳን ነች። እናም ደቡብ ሱዳን ነፃ ወጣ እንደ አንድ ሀገር ራሷን ችላ መኖር ከጀመረች ወዲህ ከአራት አመታት በላይ ሆኗታል ግን ውስጥ ባለው ችግሮች ተረጋግተው መኖር አልቻሉም። እናም ከዱሮ ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቷ ረብሻ ሲፈጠር መደበቂያቸው ጋምቤላ ነው፣ ምክንያቱም በባህልም ሆነ በቋንቋ ቅርበት ጋምቤላ ይቀናቸዋል፣ እናም እነኚህ ደቡብ ሱዳኖች በውናቸውም ሆነ በህልማቸው ጋምቤላ የደቡብ ሱዳን አካል ነች ብሎ ያምናሉ እንዲያውም ጋምቤላ የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ እናራጋታለን ብሎም ያምናሉ፣ ይህ አላማቸው የኢትዮጵያ መንግሥታት ያወቁት እንደሆን አላቅም ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ የማሳወቅ ግደታ ስላለብኝ ነው ይህን የማካፈላችው።
 አሁን ባለው ሁኔታ በኔ እይታ ጋምቤላን እንዴት አርገው ይወስዱቷል ብላችው ቢጠይቁ በሁለት ዓይነት መንገዶች ናቸው።
1) ጋምቤላ ክልል የራሷ አንቀስ 39 ስላላት በዚሁ አንቀጽ መገንጠል ትችላለች ማለት ነው ምክንያቱም ዛሬ የጋምቤላ የህዝብ ቁጠራ ቢደረግ ከ400 መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን  ስደተኞች የኢትዮጵያ ዜግነት ተሰጧቸው ይኖራሉ ይህ ቁጥር ከጋምቤላ ህዝብ ቁጥር በላይ ነው፣
2) በጦርነት ከሆነ ደግሞ ሊያሸነፉም ላያሸንፉም ይችላሉ፣ ሊያሸንፉ ይችላሉ የሚልበት ምክንያት አንዱ እነኚህ ከ400 መቶ ሺህ ስደተኞች በላይ በሙሉ መሣሪያ አላቸው ያኔ የርስ በርስ ጦርነት ሲነሣ ወደ ኢትዮጵያ ሸሽተው ሲገቡ ብዙዎቹ መሣሪያቸው ይዞ ነው የገቡት ይኸ ደግሞ ስደተኛ ወደ ጎሬቤት ሸሽተው ከነመሣሪያ ሲገባ ኢትዮጵያ/ጋምቤላ ከዓለም የመጀመሪያ መሆን አለባት፣ አሁን ባለንበት ስዓት ላይ ጋምቤላ የሚመራው በደቡብ ሱዳን ስደተኛ የነበረ ሰው ነው።
እነኚ የደቡብ ሱዳን የኑዌር ጎሣዎች ድንበሩን እንደተሻገሩ በሳምንታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዜግነት ይሰጣቸዋል እናም ሁለት መታወቂያ ወረቀት ነው ይዞ የሚዞሩት ይኸም ድርጊት በጋምቤላ ክልል ብቻ ነው የሚደረገው ይኸን እያየሁ ያስፈራኛል ። ሌሎቻችሁ ልያስፈራችሁ ይገባል ምክንያቱም በኃላ ችግሩ የሁላችን ነውና፣ ከዚህ በላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች በሙሉ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ቢሮ ማወቅ ያለበት ጉዳይ ስለሆነ የኢትዮጵያ መንግሥትም ችግሮች ሳይከሰቱ ትኩረት ቢሰት ጥሩ ነው የሚል እምነት አለኝ።
 እዚያ ጋምቤላ ያለው እሳት ከነደደ በኃላ ከመሯሯጥ ካሁኑኑ ሳይነድ ማስቆም ተገቢ ነው። ብዙዎቻችው ምነው አንተ ብቻህን ነው ስለጋምቤላ የምትቆረቆረው ትሉኝ ይሆናል እኔ ግን በኃላ ከመፀፀት የሚችለውንና የማውቆውን ለራሴ ብቻ ከማስቀረት ሌላም ማሳወቅ ስላለብኝ ነው በኃላ ከሚቆጨኝ!!!!
Filed in: Amharic