>
5:13 pm - Sunday April 19, 4336

ብሄር የማያውቁት ወጣቶች (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

 

ሰፈር እንጅ ብሄር የማያውቁት ወጣቶች ይፈቱ

 

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ /ኮተቤ ሜትሮፖሊን ዩኒቨርስቲ

 

መከራ ተረግዞ ተወልዳ ችግር

ስቃይ ተሞሽራ ሲዘራ ባገር

ኃዘን ስትዘፍን አታሞ ስትመታ

ድህነት ሲሸልል እየነፉ እንቢልታ

መጡ ከኔ ዘንድ አብረውኝ ሊኖሩ

ተስማምተው ደረሱ እየተባበሩ

(ዮሀንስ አድማሱ፡ እስኪ ተጠየቁ ቁ. 3)

ኢትዩጵያውያን ለዘመናት ቢያንስ ለሰማኒያ እና ለዘጠና አመታት መሪዎች በሚፈጥሩት የአገዛዝ ስርዓት መከራ እንደ ሰው ተረግዞ፣ ስቃይ እንደ ጎረምሳ ተሞሽሮ፣ ሀዘን እንደ ደስታ ሲዘፈን፣ ድህነት እንደ ጀግና ሲሸልልብን የኖርን ህዝቦች ነን፡፡ በተለይ ላለፉት ለሀያ ሰባት ዓመታት ተንሰራፍቶ በቆየው የህወኃት አገዛዝ ያሳለፍነው ጊዜ እጅግ ዘግናኝ ነበር፡፡

ይህ ለዘመናት ተንሰራፍቶ  የቆየው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የጭቆና አገዛዝ  በዶ/ር አብይ አስተዳደር መስመር ይይዛል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር፤ ዳሩ ግን የተሰጠን የተስፋ ቃል ዜጎች ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ እንደማይታሰሩ በሚዲያ የተነገረን ትርክት ረጅም ጉዞ ሳይዝ ለምን መሰናክል ገጠመው?

የአዲስ አበባ ወጣቶችን ያለ ምንም ጥፋት ለደህንነታቸው አስጊ በሆኑ አስር ቤቶች ማጎር እና ሕይወታቸው እንዲያልፍ ምክንያት ለመሆን መብቃት ከዶ/ር አብይ አስተዳደር የሚጠበቅ ተግባር አይደለም፡፡ ያለ ወንጀላቸው ለምን ወጣቶች ይታሰራሉ? ፍትህ ለአዲስ አበባ ወጣቶች!!!!!!

አስካሁን ባሳለፍናቸው ጊዜዓቶች ኢትዪጲያ የችግር አገር ነች፡፡ መከራ፣ ስቃይ፣ ሀዘን፣ ድህነት፣ ስራ አጥነትን ችለው እየኖሩ ያሉ ወጣቶች ቢያንስ  ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊታሰሩ እና ሊሞቱ ግን አይገባም፡፡ አሁንም ፍትህ ለአዲስ አበባ ወጣቶች!!!!!!

Filed in: Amharic