>
5:18 pm - Sunday June 15, 0431

ልብ ይሰብራል!!! (ሀብታሙ አያሌው)

ልብ ይሰብራል!!!
ሀብታሙ አያሌው
ስለ ጠበቃ ሄኖክና ስለ ማይክ የእስር ሁኔታ ምንም ማለት እስከማልችል ድረስ ግራ ገብቶኛል:: ማይክን ባለፈው ሳምንት አግኝቼዋለሁ:: ማይክ ሙሉ ሰው የምንለው አይነት ምርጥ ሰው ነው:: ደግነቱ…. የሚገለፀው በመስጠቱ ሳይሆን ከልቡ በመስጠቱ ነው:: መስጠቱ…. በአይን የሚታይንና የእለት ችግርን በሚያቃልል መልኩ ብቻ አይደለም:: ቅን..ሩህሩህ… አዛኝ… የመሆኑ ቀመር የመጣው ከመኖር እና ከማንበብ ነው:: ከማይክ ጋ በተቀመጥንባቸው 2 ሰአታት ብዙ ቁምነገሮችን አውርተናል:: ታሪክ… አስተዳደር… ሂሳብ… ፖለቲካ….. ብዙዙዙዙዙዙ ነገር! ማይክ ስለ ብዙዎቹ አዲስአበቤዎች ብቻ ሳይሆን ስለ ሰማይ አእዋፋት እንኳን አብዝቶ የሚጨነቅ ደግ ሰው ነው::
ስለወቅቱ የአዲሳባ የባለቤትነት ጥያቄ እና ነዋሪው ስላለበት ሁኔታ ብዙ ተነጋግረናል:: ለዚህም እንደ መፍትሄ ከወጣቶች ጋ ለመነጋገር ብሎም መልካምን ነገር በቀጣይ አዲስአበባዊ ጉዳይ ላይ ለመመካከር ማህበር እንደሚቋቋም ለዛም ተግቶ እየሰራ መሆኑን ተመልክቻለሁ:: እስረኛ ጠያቂውን ማይክ….. ለችግረኞች ደራሽ የሆነውን ማይክ… እንግዳ ተቀባዩን ማይክ… አንድ ለናቱ የሆነውን ማይክ…ምን ስላጠፋ አሰራችሁት!!??  መች ይሆን በሃገራችን ምክንያታዊነት እና ሰብአዊነትን አጣምሮ የያዘ መንግስት የሚመጣው??
ትላንት የኔን ስቃይ አብሮኝ የተሰቃየ፤ ያሁሉ ደህንነት እየዛተ በራሱ ላይ ጨክኖ ለወራት በማደንዘዣ የመቆየቴን ስቃይ በመኖርያ ቤቱ እንዳሳልፍ የረዳኝ፤ ሚካኤል መልአክ ዛሬ “አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ነዋሪ የዜጋው ናት።  ከክልል እያመጣችሁ አትሹሙብን”  አለ።  ከዚያም የአዲስ አበባን ወጣት ለማደራጀት ሞከረ በሚል በዶ/ር አብይ አስተዳደር እጁ ላይ ካቴና ገብቶ ማየት ለዚህ አሳፋሪ ተግባር ሽፋን ደግሞ ከፍልስጤም ስልጠና መውሰድ የሚል ነውረኛ የተለመደ ቅጥፈት መጨመር በእጅጉ ያሳዝናል።
 ፌንፊኔን እናስመልስ የሚል ማህበር መመስረት እና አዲስ አበባ የኛ ናት የሚል መግለጫ ማውጣት ለዚህም የመንግስት ስልጣን ከያዙት ጋር በመመሳጠር በተግባር የሚደረግ አደገኛ ሴራን ለማክሸፍ ኢትዬጵያዊነት ማለት እንደ ትላንቱ ለሰቆቃ የሚዳርግ ሁኖ ቁጭ አለ።
የጉድ አገር !!
Filed in: Amharic