>

ለውጡን እንዴት እንርዳ? (ቾምቤ ተሾመ)

ለውጡን እንዴት እንርዳ?

ቾምቤ ተሾመ


ለብዙ ጊዜ በውሃ እጦት ደርቆ የቆየና የተሰነጣጠቀ መሬት ምን ያህል ውሃ ቢፈስበት ከመሬቱ በላይ በቃኝ የሚል መልክ እንደማያሳይ ሁሉ እኛ ኢትዮጵያንም ለብዙ ዘመናት ስንመኝው የቆየነው የዲሞክራሲ ጭልጭልታ እጃችን ላይ ሲወድቅ እንዴት እንደምንይዘው ግራ የገባን እንመስላለን፡፡

ዲሞክራሲ የሚሰጣቸውን መብቶች ከሞላ ጎደል በንድፈ ሃሳብ ደረጃ እናውቃቸዋለን ፤ ለምሳሌ የራስን ወኪል ታእማኔነት ባለው የምርጫ ቦርድ አማካይነት መምረጥ፤ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ፤ እራሳቸውን ለፓለቲካ ጫና የማያቀረቡ  ነጻ ብያኔን መስጠት በሚችሉ የፍርድ አቋማትን ማቋቋም ፤ ገለልተኛ የሆነ የህዝብ ደህነት ተቋም መመስረት፤ የመከላከያ ሰራዊትም ፤ህዝቡ በነጻ ምርጫ በወከላቸው ተወካዮቹ የጸደቀውን ኮንስቲቲውሽን መከላከልና፤ የሀገርን ልእልናን  ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ከመከላከል ውጭ ሌላ ምንም ተልኮ የሌላው አቋም መሆኑን ማረጋገጥ ውዘተ፡፡ እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው መዋቀራዊና ግለሰባዊ መብቶች በእርግጥ መመስረት አለባቸው፤ ከተመሰረቱም መጠናከር አለባቸው፡፡

ነገር ግን ሀላፊነትን ግንዛቤ ደረገ መልኩ ህዝባዊ ተሳታፊነት ካልተጨመረበት ፤  ላቆጠቆጡት ዲሞክራሲያዊ ጭላንጭሎችን በትግስት ነገር ግን ባላቋረጠ መልኩ እንዲጎለምቱ ማድረግ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡
ደግሞም ይህንን የለውጥ ሂደት ግንባራቸውን ሳያጥፉ እየገፉ ያሉትን አብይን፤ ለማን ፤ገዱንና ፤ ደመቀን እርምጃቸው እንዳያወላዳ እየመከርንና እየገሰጥን የለውጡን እርምጃ አብረን ማፋጠን አለብን፤ነገር ግን በዚህ ሽግግር ወቅት የነዚህን መሪዎች ደህንነታቸውን በተመለከተ ብቃት ባለው መዋቅራዊ አደረጃጀት ባለው የህዝብ ደህንነት እየተደገፍን ህዝባዊ የብረት አጥር ሁነን መከላከል ያለብን ግለሰቦች መሆናቸው ተረድተን ወሰነን መጓዝ አለብን፡፡  ለፈላጭ ቆራጭ መሪዎቻቸን የሰጠነውን መረን ያጣ የደህንነት ጥበቃ
ሊያገለግሉን  ደፋ ቀና ለሚሉ መሪዎቻችንን አግባብ ያለው ጥበቃ መንፈግና በንዝህላልነት ለአደጋ ማጋለጥ እራሳቸን ላይ እንደማሴር የሚቆጠር ነው ፡፡በቅርቡ መረን ያጣው ወደቤተመንግስ የዘመመው የወታደሮች ጉዞ ንዲሁም ባለፈው ጥቅምት ላይ አብይ ላይ ያነጣጠረው የፈንጂ ሙከራ ቢሳካ ምን ያህል ማጥ ውስጥ ልንገባ እንደምንችል መገንዘብ ስለማያዳግት፡፡ይህ ክፍተት እንዳይደገም ተደርጎ በጭራሽ መወገድ  አለበት፡፡


ይህንን ከተጠቆመ በኋላ፤ ህዝቡ እንዴት ነው ይህንን ለውጥ ስር እንዲሰድ  ማድረግ የሚቻለው የሚለው ጥያቄ ለመዳደስ እንሞክር፡፡ አሁን የደረስንበትና ግንዛቤ ያደረግነው ነገር ቢኖር ለውጡን በመሪነት የያዘው አብይ ወይም በቡድን  ስሙ ቲም ለማ ዲሞክራሲን እንዲገነባ ፍላጎት እንዳላቸው፤ ብሄራዊ አንድነት እንዲጠናከር እንደሚጥሩ ፤ለዚህም እስካሁን የወሰዱትን እርምጃዎች እንደ ማስረጃ በማቅረብ፤ የወደፊት ርአያቸውን ለህዝብ በማሳወቅ ህዝቡ እንዲደግፋቸው እየጠየቁ ነው፡፡ ይህንን ጥሪያቸውን የተለያዩ ተፎካካሪ
ፓርቲዎች እንደሚደግፉ በተለያየ መድረክ ሲምሉ ሲገዝቱ ይታያሉ ፤ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውጡን እንደግፋለን እያሉ ለውጡን የሚያደናቅፍ እንቅስቃሴ ውጥስ እራሳቸውን ዘፍቀው ይገኛሉ ፡፡

ይህ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ በሁለት መልኩ ሊታይ ይችላል አንደኛው ጀዋር በግልጽ እንደነገረን በየደረጃ የፖለቲካ እውነታን መሬት ላይ ለመፊጠር የሚደረግ እንቅስቃሴዎች ሊሁኑ ሲችሉ ሁለተኛው  ደግሞ የአጭር ግዜ የፖለቲካ ትርፍ ለማኝት የሚወሰዱ የፖለቲካ እርምጃዎች ሆነው ነገር ግን ህብረተሰቡ ላይ በጣም አጥፊ ክስተቶች እንደሚያመጡ በቅርቡ በቡራዩ የደረሰውን በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል፡፡ ይህንን ፕላን ተገባራዊ ለማድረግ  በብሄር የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች በዜግነት ፖለቲካ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱትን ድርጅቶች ላይ ከወያኔ መፅሃፊ ገጾቸን በመውሰድ ሞአ አንበሳቸ ሊመጡባችሁ ነው እያሉ በይፋ በአጥራቸው ውስጥ ገድበው  በያዙት ህዝብ ላይ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ እያካሄዱ ነው፤ በዜግነት ፖለቲካ የሚንቀሳቀሱ ፓለቲከኝች ደግሞ የያዙትን አለም አቀፋዊ እንዲህም በኢትዮጵያዊ ዜግነት የተመስረተ ርእዮት የበላይነት በመመካት ለብሄር ፓለቲከኝችን ከበሬታ ባለመስጠት አብረው ተከባብረው መስራት የሚቻልበትን መድረክ መፍጠ አለመሞከራቸው ያለውን ልዮነት እያሰፋ ፤ በአንድ ሀገር እንደሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይሆን በተለያየ ፕላኔት ላይ እየኖሩ የሚጯጯሁ ጎረቤቶች እንዲመስሉ አድርጓቸዋል፡፡  ይህ ደግሞ ህዝቡን ከማቀራረብ ፋንታ እንዲራራቅ ወደ አንድ መድረሻ የሚጓዝ ህዝብ ሳይሆን አንዱ ወደ ሰላሌ ሌላው ወደ ሞያሌ የሚጓዝ የሚመስል ስእል በህዝቡ አእምሮ ውስጥ እንዲሳል አድርጓል፡፡


ይህ ደግሞ አሁን ሀገር እየመራ ያለውን አስተዳደር የቱን ይዞ የቱን እንደሚጥል ግራ እንዲጋባ አድርጎታል፤ ለምን ቢባል እንደ ጽንፈኛው ጸጋዬ አራርሳ አይነቶቹ አክራሪዎች አብይ የሚኒልክን ስጋ የለበሰ ኦሮሞ ነው ብሎ ኢላማቸው ውስጥ አስገብተው እየቀሰቀሱበት ይገኛሉ ፤ ሌላች ደግሞ አብይ ይህንን አዘር ፖለቲካ በጓዳ ጀምሮ አሁን ደግሞ በፊት በር እያስገባ ነው፤ እውነተኛ ቀለሙ ፏዋ ብሎ እየታየ ነው ብሎ ይከሱታል ( በዚህ እረጋድ
የአብይ አስተዳደር መስራት ያለባቸው ስራዎች አሉ በኋላ ላይ እመለስበታለሁ) ይህን ስከን ባለ መልክ ስናየው በአግድሞሽ የሚካሄድ ዲሞክራሲያዊ የግኑኝት ድልድዮች እየተገነቡ እንዳልሁነና ነገር  በሽቅባዊ አቅጣጫ
የሚገሰግሱ የዲሞክራሲያዊ ጥያቂዎችና ግን እየጨመሩ መምጣታቸውን ነው የሚያሳየው ፤ማለትም በህብረተሰብ ውስጥ ያሉት የፖለቲካዊ ወይም ህብረሰባዊ ጥያቄዎች መፊትሄ እዲገኝላቸው ህዝባዊ መድረኮች ተዘጋጅቶላቸው እየተወያየንባቸው ሳይሆን አድራሻ ተጽፎባቸው የሚላኩት ወደ አብይ ደጅ ነው ፡፡ አብይ
የሚሰጣቸው መፍትሄዎች ደግሞ ሁሉም በተሰለፈበትና ካለበት ጎራ አንጻር ትርጓሜ ስለሚሰጠው አንዱ የአድላዊ ውሳኔ ተጠቃሚ ሌላው ደግሞ የአድላዊ ውሳኔ ተበዳይ እንደሆነ አይነት ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

እነዚህ የተለያዩ የአብይን የለውጥ መስመር እንዲሳካ እንጥራለን የሚሉትና በየሚድያው የሚምሉት
“ደጋፊዎች” እርስ በእርስ ሲጠላለፉ ፤ ይህንን ለውጥ ተቀልብሶ የድሮ ኮርቻቸው ላይ ፊጢጥ ለማለት የሚያልሙ፤ ይህንን የተፍጠረ ክፍተት ተጠቅመው ትልቅ ጥፋት  ለመስራት እደማይመለሱ ከላይ የተጠቀሱት አደገኛ ሁኔታዎች ግልጽ ያደረገው ጉዳይ ነው፡፡


ወደተነሳንበት ዋና ሃሳብ ከመመለሳቸን በፊት መረገጥና መሰመር ያለበት ጉዳይ ቢሆኖ አክራሪ ወያኔዎችና ፤ጽንፈኛ የኦሮሞ አክራሪዎች፤ ደግሞም የወያኔ ፍርፋሬ የቀረባቸው የጥፋት ሃይሎች ለጥፋት ሊሄዱ የሚችሉበትን እርቀት አለመረዳት እጅግ በጣም አደገኛ ነው፡የዚህ አጥፊ ሴራቸው ምን ያህል ለመሳካት
እንደቀረበና ከተሳካ ደግሞ ለኛ የሚያስከፍለን የጥፋት ክፍያ ከፍ ያለ መሆኑን መረዳት በመሃከላቸን ካለው እሰጣ ገባ ጫወታ ተመንጭቀን እንድንወጣ ያስገድደናል፡  ለውጡን ወደፊት ተጠናክሮ እንዲቀጥል
የሚከተሉት እርምጃዎች በሁሉም የፖለቲ ድርጅቶች ሳይውል ሳያድር መውሰድ አለባቸው፤


1) የድርጅት ፖሊሲዎቻቸው ተግባራዊ መሆን ህብረተሰቡ ለገንጠመውን ችግር እንዴት መፍትሄ
እንደሚሆን በህዝብ ፊት ቀርቦ ማስድረዳትና ፤ ከህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች አግባብ ያለው መልስ መስጠት

2) የፊደራላዊና የአካባቢ አሰትዳደሮች እንዴት በፖሊሲና በህግ ደረጃ ተዋቅረው የህዝቡን የራስ በራስ ማስተዳደር መብትና በፊደራሊዝም የሀገራዊ አስተዳደሮች መዋቀር ተስማምተው መካሄድ የሚችሉበት መንግድ ላይ ህዝብ ፍት በግልጽ ቀርቦ ማስረዳት

3) እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ የትኛውም የአሰተዳር ውስጥ ሲኖር በማንኛውም አሰትዳደር የማይጣት ግለሰባዊ መብቱን ጥርት ባለ መልኩ ማስቀመጥ  እያንዳንዱ ድርጅቶች መድረክ ቀርቦላቸው መወያየት ይገባቸዋል፤

በዚህ ውይይት ላይ  የተፎካካሪ ድርጅቶች ሆኑ መንግስትንም ጨምሮ መከባበር በሞላበት መልኩ
ለህዝቡ ያላቸው ርአይ የሚያስቀምጡበት ይሆንል ፤ይህም 2020 ምርጫ ሰው ስለሀገሩ የወደፊት ጉዞ
ግልጽ እይታ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ጥያቂያችንን ተመልሰን ከአርስቱ  ለውጡን እንዴት እንርዳ? ብለን እንጀምር። ምንም እንኳን አሁን ያሉት ዋና ተብለው የሚጠሩት ብሄራዊ ማነነት ላይ  ያጠነጠነ የፖለቲካ
አሰላለፍና በዜግነት ላይ ያተኮረ ፖለቲካ ከሩቅ ሲታዩ የማይታረቁ ቢመስሉም ቀረብ ብለው ሲያይዎችው በብዙ መልኩ መገናኝት አብረው ተከባብረው መሄድ የሚችሉ ናቸው፡፡ ሁለቱም ዲሞክራሲ ስርአት እዲመሰረት አቀንቃኞች ናቸው፡፡

የግለሰብ መብት እንዲከበረ ሁለቱም ድጋፋቸውን ይሰጣሉ ፤ ሁለቱም የህግ በላይነት እንዲኖር የፍርድ ተቋማትም ነጻ ከፖለቲካ ዉጭ አቃም እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፤ ሁለቱም ወገኖች የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች እየተንሸራሽሩ ህዝቡ በድምጹን በነጻ እንዲሰጥ ይደግፋሉ፤ ነጻ የመናገርና የመጻፍ ህዝቡ እንዲኖሩ ይደግፋኡ  ከብዙ በጥቂቱ እነኝን የተወስኑ ስምምነቶች እንኳን እንደ ድልድይ  ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ጽንሰ ህሳቦች ናቸው፡፡ ስለዚህ ብዙ የሚያስማሙን ነገር ግን በማንስማማቸው ላይ ደግሞ እውቀትን መሰረት ያደረገ ውይይቶችን በህዝብ ፊት ከበሬታ በሞላበት መንገድ ውይይት ማድረግ እንቻላለን፡፡

በዚህ መንፈስ የሚካሄዱ ውይይቶች አንደኛ ፓለቲካን ስሜትን ጎትጉተው የህዝብ ጀሞላ ተከታይነት ለማግኘት የሚደረጉ የፖለቲካ አካሄዶች እየከሰሙ እንዲሄዱ ያደርጋሉ፡፡ በውሸት ላይ ተመስርተው ፖለቲካ ለማራመድ የሚነዙ የበሬ ወለደ ታሪኮችን ሃሰት ከሆኑ ህዝቡ በሙሁራን እየተረዳ ገምግሞ አክስሮ እንዲተዋቸው እድል ይሰጣሉ፤ እውነትነት ያላቸውን ምንም እንኳን ለመቀበል የሚያስቸግሩ እውነታዎች ካሉ ሁላችንም ከታሪኮች ተምረን እንዳይደገሙ ቆርጠን ተደጋግፈን አብረን እንድንቀጥል ይረዳናል፤ በይበልጥ ደግሞ አብረን በመከባባር እውነትን   ለማግኘት በምናደርጋቸው ውይይቶች አንዳቸን ከሌላችን የሚያስተሳስረን የሰው ተፈጥሯችንን የጎላ መሆኑን እየተረዳን እንድንመጣ ይረዳናል፤  እነኝህ ተንከባክበን የምንመሰርታቸው ግለሰባዊ ደግሞም መሃበራዊ ግኑኝቶች ናቸው የምንሻቸውን የምንመስርተውን የዲሞክራቲክ ተቋማትን ለሰው ፍላጎት መልስ የሚሰጡ  ህይወት ያላቸው ተቋሞች የሚያደርጓቸው፡፡

ይህንን ጎንዮሽ ግኑኙነት እንዲመሰረቱና እንዲዳብሩ ፤ የተለያዩ ህሳቦችም ወደላይ የሚላኩ ሳይሆኑ ደጎን  እንዲሸራሽሩ የተቃውሞ የፖለቲካ ድርጅቶች መንግስት እንዲሁም ብሄር ተኮር የሆነ  የፖለቲካ አደረጃጀት ያላችው ሁሉ በሃሳብ ልዩነት ምክንያት ሳይፈራሩ፤ አብረው በውይይት መድረክ ላይ የያዙትን ሃሳብ ይዘው ከራክር መደራደር አንዳንዴ ደግሞ እንደማይስማሙ ተስማምተው በመከባበር መለያየት  ሚችሉበትም መንገዶችን ይከፍታል፡፡

ይህ አይነት ህዝባዊ የሆነ ተሳትፎ በመሪነት ላይ የተቀመጡ ሰዎች የሚወስዱትን አቋም ክፖለቲካ አመለካከት እንጁ አንዱን ወገን ለመጥቀም እንዳላደረጉት በሙሉ ልብ መግለጽ እንዲችሉ ሰፋ ያል መድረክ ይሰጣቸውል፤ ስለዚህ አሁን በሀገራችን ላይ ያለውን ይህንን ወግኖ ይህንን  ለመበደል ነው ከሚል መላምት ያወጣናል;፤ እንዲህ አይነት ውይይቶች የሚያሰፉት የፖለቲካውን መድረክ ብቻ ሳይሆን   የአስተሳስባችንን  መድረኮ ችንም ያሰፉልናል፡፡ ያ ደግሞ ፖለቲካችንን እንደ ጣውላ ቀጥ ያለና ደረቅ ከመሆን አውጥቶ መፍትሄ ለማግኝት ተጣጣፍና እንደአስፈላጊነቱ ተስተካካይ እንዲሆን ያደርገዋል፤ ዲሞክራሲ የሚገነባው የዲሞክራሲያዊ መዋቅሮች በመኖራቸው ብቻ ሳይሆን ህዝቦች ያላቸውን ሀሳቦች በአደባባይ እየፈተሹ ሀሰት የሆኑትን ቀርፈው በመጣል እውነት የሆኑት ላይ ደግሞ በመስጠትና በመቀበል ላይ በተመሰረተ ፖለቲካ መፊትሄ ፍለጋ ላይ ሲሰማሩ ነው ፡፡ 

 እንደማጠቃለያ ቀደም ብዬ የአብይ አስተዳደር ያለማቋረጥ በማያሻማ ሁኔታ ለመላው ኢትዮጵያዊ እያስረገጠ የተናገረው ነገር ቢኖር እንደሃገር ካለንበት የፖለቲካዊ ፤ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ ማጥ ለመውጣት የምንችለው አብረን እንደ ኢትዮጵያውያን እየተደጋገፍን ስንሄድ ብቻ ነው ብሎ በተደጋጋሚ ተናግሯል ፤ ይህ ደግሞ እንኳን 83 የተለያዩ ብሄረሰቦች በሚኖርባት አገር ቀርቶ አንድ ብሄረሰብ የሚኖርበት ሀገር እንኳን ቢሆን ከእውንታዊነት ፍቀቅ የሚያደርገው ነገር የለም ፡፡

ነገር ግን አብይ የሚሾማቸው ወይንም ሀላፊነት የሚያስቀምጣቸው ሰዎች እርሱ ከሚያራምደው የፖለቲካ እይታ ተስፈንጥረው በተግባርም ይሆን በእይታ የቆሙ ከሆኑ ፊየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ የሚሉት
ሁኔታ ነው የሚፈጠረው፡፡ ይህንን  ለማስተካከል በይሉኝታ ወይም ደግሞ ይሄ የኔ ድርጅት አባል ነው ብሎ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም አብይን ተቃርነው ከቆሙት የበለጠ ጉዳት ማድረስ ስለሚችሉ ነው ፡፡
እነደነ ፕሮፌሰር እስካአልና እንደ ኦቦ ሌንጮ ባቲ   የሶስት ሺህ አመት የታሪክ ሂሳብ  እናወራርዳልን ብለው የሚንቀሳቀሱ የህዝብ አስተዳዳሪዎች ወይንም የመንግስት ባለስልጣናት ካሉ ምንም እንኳን ጊዚያዊ 
የፖለቲካ  ግም ግም ቢያስከትሉም የለውጡን መንገድ ፈር ለማስያዝ ወሳኝና አስፈላጊ እርምጃዎች በጊዜ ወስዶ ማስወገዱ ፈረንጆቹ እንደሚሉት “An Ounce of Prevention Is Worth a Pound of Cure “

Filed in: Amharic