>
4:03 pm - Tuesday July 5, 2022

አድራጊ ፈጣሪው የህወሀት ረጅም እጅ እየተቆረጠ - አከርካሪዋም እየተሰበረ ነው!!! (መስከረም አበራ)

አድራጊ ፈጣሪው የህወሀት ረጅም እጅ እየተቆረጠ – አከርካሪዋም እየተሰበረ ነው!!!
መስከረም አበራ
ህወሃት ዋና ዋና ኦርጋኖቿ “Fail” እያደረጉ ነው፨ ዛሬ አስመላሽ ወ/ስላሴ የተባለ የተባለ መዥገር ተነቅሏል፨ ኢትዮጵያ ውስጥ “ህወሃት” የሚባል ፖርቲ “Ban” ተደርጎ እንደማየት የሚናፍቀኝ ነገር የለም፨
ህዎሃት  ሌብነትን በዘረኝነት የለወሱ ሰዎች የመሰረቱት፤ በመታረሙ ተስፋ የማይደረግበት የዘቀጠ መሞት ብቻ ያለበት ፓርቲ ነው፨ የነአስመላሽ አይነት ሰዎች ከማይገባቸው  ወንበር ላይ መነሳት ወደሞት የማዝገሙ ምልክት ነው፨
የግፈኛውን የተወልደን፣ ሰብዐዊነት በዞረበት ያልዞረው የውሸት ጎተራ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር እና ሌሎችን መዥገሮች መነቀል እንጠብቃለን፨ አንቸኩልም ሆኖም ፍላጎታችን የፍትህን ደጃፍ እንዲያንኳኩ እንጅ መቀሌ በየሆቴሉ በስተርጅና ዓለም አስር እንዲሉ አይደለም።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የመከላከያ አባላት
የጌታቸው አስፋ ምክትል ዶ/ር ሀሺም ይገኝበታል
በወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት መስሪያ ቤት ሰዎች መካካል የሦስት ዳይሬክተሮች ዳይሬክተር የነበረውና የጌታቸው አስፋ #ምክትል ዶ/ር ሀሺም ይገኝበታል። ዶ/ር ሀሺም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ ዋና እና ቁልፍ ሰው ሲሆን የሰው ኃይል ምልመላ፣ መረጣ፣ ስምሪት፣ ስልጠና፣ የመስሪያ ቤቱ አጠቃላይ አደረጃጀት፣ መዋቅርና የውጭ ግንኙነት በበላይነት የሚመራ እና ጌታቸው አሰፋ የሚተማመንበት ዋነኛ ሰው ነበር።
እስካሁን በቁጥጥር ስር ከዋሉት #የመከላከያ_አባላት! 
1. ብ/ጀ/ ጥጋቡ ፈትሌ የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ
2. ኮ/ል ሙዕዝ የሎጂስቲክስ ክፍል ኃላፊ
3. ኮ/ል በረሃ የሜጋ ፕሮጅክቶች ኃላፊ
3. ኮ/ል ሙሉ የሰው ሃይል አስተዳደር ኃላፊ
4. ኮ/ል ተክላይ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍል ኃላፊ
5. ኮ/ል በረሃ የሕግ ክፍል ኃላፊ
6. ኮ/ል መሃመድ የስነምግባር ክፍል ኃላፊ
7. ኮ/ል ህሉፍ የኮንትራት አስተዳዳር ኃላፊ
8. ሌ/ኮ አክብረት የእቅድ ዝግጅት ኃላፊ
9. ሌ/ኮ ተከስተ የአቅም ግንባታ ማእከል ኃላፊ
10.ሺ አለቃ ገብረስላሴ የልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ
11. ሺ አለቃ ክፍሌ የቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ
12. ሺ አለቃ መኮንን
13.  ጀኔራል ሀድጉ ገ/ስላሴ
14. ጀነራል ጠና ቁርንዲን
Via Brook Abegaz Aba Bona
Filed in: Amharic