>
1:43 am - Saturday December 10, 2022

የመንጋክራሲ( Mobocracy) ፖለቲካ አቀንቃኞች አላማ ምንድን ነው (ቾምቤ ተሾመ )

 የመንጋክራሲ( Mobocracy) ፖለቲካ አቀንቃኞች አላማ ምንድን ነው?

 

ቾምቤ ተሾመ       

የቄሮ፤ የፋኖ፤ የዘርማ መሰረታዊ የትግል መነሻው በጣም በሚያሰደንቅና በሚያኮራ መልኩ ፍትህን፤ እኩልነትን ፤ዲሞክራሲን ፤ የህግ በላይነትን በኢትዮጵያ እንዲስፍን ነው ፡፡ ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ ሰላማዊ ትግልን እንደ አውታሩ የተጠቀመ  በኢትዮጵያ ህዝቦች መአከል ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን እንዲጠናከር መሪ የሆኑ አቅጣጫዎችን የሚጠቁም ህዝባዎ ርእዮትን ያነገበ እንደነበር የቅርብ ግዜ ትውስታችን ነው፡፡

ይህን ህዝባዊነትን እንደመሰረቱ ተጠቅሞ የወያኔን አገዛዝ ጉልበቱን ሰልቦ በኢሀድግ ውስጥ የነበሩ የለውጥ መንፈስን ያነገቡ መሪዎች እንደ አማራጭ ወደፊት እንዲመጡ ያደረገ  እንቅስቃሴ ነው፡፡ ነገር ግን የዚህ እንቅስቃሴ ጉልበት እየጠነከረ የመጣውና ፍሬ ማፍራት የቻለው ለማ መገርሳ ቲምና የገዱ ቲም በወሰዱት የበሰለ አመራር ነው ፤ እነዚህ መሪዎች የኢትዮጵያ ህዝብን የወደፊት እጣ ፋንታ የሚወሰነው በአንድነቱ ላይ መሆኑን ስለተገነዘቡ እንቅስቃሴውን ተከላከለውና የእንቅስቃሴውን ጥያቄዎቹን አንግበው ከፊት በመቆማቸው ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዲመሰረት ተሰፋ ሲጪ መድረኮችን ማዘጋጀት ችለዋል፡፡

የቄሮ፤ የፋኖ፤ የዘርማ የወጣቶች እንቅስቃሴ ድርጅታዊ ሰንሰለቱ በጣም የላላ ፤ ያልተዋቀረ እንቅስቃሴ ስለነበር፤ የነለማና የገዱ  ቲም አብረዋቸው ቆመው እንቅስቃሴ ባይከላከሉትና ለወያኔ አጋልጠው ቢሰጡት ኖሮ፤ መዋቅራዊ ልእልናና ያለውና የሀገሪቷን የኢኮኖሚያ በበላይነት እየተቆጣጠር የነበረው ወያኔ ትግሉን አኮላሽቶ ፤ለውጡን ፈር ማሳት ብቻ ሳይሆን ፤አሁን ያየነውን እዲሞክራሲ ጭልጭልታ ሊያጨልመው ይችል ነበር ብለን በእርግጠኝነት ድምዳሜ ላይ መድረስ አንችላለን፡፡ ከቅርብ ታሪካችን እንደምንማረው 1966 የተማሪዎች እንቅስቃሴን በወቅቱ ተማሪው ያነገቧቸው ጥያቄአዎች የህዝብ ብሶት ያበቀላቸው የኢኮኖማዊና የፖለቲካ ጥያቄዎች ትክክለኛ እንደነበሩ ምንም ባይካደም፤ ነገር ግን በወጣቱ አክራሪነትና የቀሰቀሱትን አብዮት በተደራጀ መልኩ መምራት ባለመቻላቸው ፤ እንዲሁም በወቅቱም በነበረው በቢሮክራሲውና በትልልቅ ሃላፊነት ላይ የነበሩት ምሁር የመንግስት ባለስልጣናት፤ እንቅስቃሴው የሚፍስበትን ፖለቲካዊ የመስኖ መንገድ በበቃት ማዘጋጀት ባለመቻላቸው፤ በወቅቱ በብቃት ተደራጅቶ የነበረው ወታደሩ የተማሪውን ጥያቄዎች በመውረስ ሀገሪቱን በወታደራዊ አምባገነን ስር እንድትወድቅ አድርጓል፡፡

በወቅቱ በ84 አመቱ አዛውንት ግርማዊ ቀዳማዊ ኋይለስላሴ ስም ይመሩ የነበሩት በትምህርት የላቁ ነገር ግን እንደነለማ ቲም ቆራጥና ወቅታዊና አግባብ ያላቸው ውሳኔዎችን መውሰድ አቅም አንሷቸው ፤የለውጡን እርምጃ ፈር ማስያዝ ስላቃታቸው የራሳቸውንም ህይወት ያለ ፍርድ በግፍ አጥተው ሀገሪቱም በደርግ 17 አመት ከዚያ ደግሞ በጎጠጫው ወያኔ ደግሞ 27 አመታት አስከፊ አገዛዝ  ለእርስ በእርስ ጦርነትችና ኢ_ሰብአዊ ጭቆናዎች እንዲጋፈጥ ምክንያት ሆነው ታሪካዊ ስህተት በመስራት ጥለውት አልፈዋል፡፡

ስለዚህ የቄሮ፤ የፋኖ፤ የዘርማ እንቅስቃሴ ባልተቀናጀ ሁኔታ ቢመራም እንቅስቃሴው  በወያኔ ስርአት ላይ ትልቅ ተጽእኖ ማሳደር የቻሉት ምክንያት:-

ሀ) እንቅስቃሴው የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ በመረዳቱና ያነሳቸው ጥያቄዎች ህዝባዊ ስለሆኑ ከመለአው ኢትዮጵያን ድጋፊን አግኝቷል፡፡

ለ) እንቅስቃሴው ያነሳቸው ጥያቄዎቻችው የትብብር መሰረት እንጂ  የግጭቶች ማመንጫ እንዳይሆን ማድረግ ችለዋል ፡፡

ይህ የተቀነባበረ ዲሞክራሲን ያነገበ የትግል አካሄድ ታሪክ የሚመዘግበው አኩሪ የትግል ክንዋኔ ነው፡፡ በበለጠ ደረጃ ዳግሞ የነለማ ቲም ይህ የዲሞክራቲ እንቅስቃሴ ትክክለኛ የሆነ አመራር በመስጠት የራሳቸው ህይወት ለመሰዋአት አቅርበው አክታትለው  የወሰዱት የፖለቲካ ብስለት የተሞላበት እርምጃዎች የለውጡን መንገድ በመቀየስ ሀገራችን ከተደጋጋሚ የቀውስ አዙሪት እንድትወጣ አዲስ ፈር መቅደድ ችለዋል፤ ለዚህ ስራቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ባለውለታዎች ናቸው፡፡

ይህን እውነታዎች በደንብ ካስያዝን በኋላ ግን ልክ ደርግ የተማሪውን ጥያቄ ጠልፎና በውስጡ የነበሩትን በርእዮተ አለም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ የነበሩትን  የተማሪ እንቅስቃሴዎችን ትንሽ ልዮነቶችን እየበዘበዘ እርስ በእርሳቸው ካጫረሰ በኋላ መጨረሻ ሁሉንም ጠራርጎ አንዳጠፋቸው ሁሉ አሁን ደጎሞ በተለይ የቄሮን ዲሞክራሲያው እንቅስቃሴ ጠልፈው ለራሳቸው እኩይ ተግባር መሳሪያ አድርገው ለመጥቀም አሰፍስፍው አክቲቪስት በሚል ሻማ ተከናንበው ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደሩ የሚገኝ ግለሰቦች ትክክለኛ መልካቸው እየተገለጠ ከመጣ ትሽ ሰንብቷል፡፡ ይህንን እንቅስቃሴ ጠልፈው የፖለቲካ መሳሪያ ለመድረግ ከሚፈልጉት በቀንደኝነት  ጀዋር መሃመድና፤ ጸጋዬ አራርሳ ናቸው ፡፡

እነዚህ በተቀነባበረ መልክ የኦሮሞ ሚድያ ኔት-ወርክንና ፊስ-ቡክ በመጠቀም እየሰሩ ያሉትን ሴራ በበሰለና በተቀነባበረ መልኩ በጊዜ ገደብ እንዲይዙ መወስድ ያለባቸው እርምጃዎች አሉ፤ ነገር ግን መፍትሄው ጋር ከመሄዳችን በፊት ግን በምን መልኩ በሰላም ትግሉ ትልቅ ታሪካዊ አስዋጾ ያደረገ የቄሮ እንቅስቃሴ ወደ ኢ-ዲሞክራሲያው ወደ ግጭት እንዲያመራ እያደረጉት እንደሆነ አትኩረን እንመልከት ፤

ሀ) በጣም ቅጥ ያጣ ውደሳ ለቄሮ ማድረግ ፤ ሁሉንም ማድረግ የሚችል ፤ መንግስትን በፈለገ ጊዜ ማንበርከክ የሚችል ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጣው ነጻነት ቄሮ ብቻ ሃላፊ ነው ብሎ መዘመር ፤ ሌላው ደግሞ በቄሮ ስም የሚሰራ ጥዩፍ ስራዎችን መንቀፍ እንደማይቻል በድንፋታ ማስፈራራት፤ ለብዙ ጊዜ ሲነዙ የነበረውን ዘር አቀንቃኝ የበሬ ወለደ ታሪክ ጥያቄ ውስጥ ያሰገባ ግለሰብ ሲስሙ በተለያዩ  ሚዲያዎች ላይ ግለሰቡ ሰእብናን በሚነካ መልክ ማጥቃት ፤ የጣይቱን ሀውል ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያዊያንን በዛቻ አስፈራርቶ ለማስቀረት መሞክል ፤ ባጠቃላይ የኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሲያዊ ምብቶችን ቄሮን እንደማስፈራርያ ተጠቅመው ደፍጥጠው የራሳቸውን አክራሪ የኦሮሞ አንባገነናዊ ስርአት ሌላው እኢትዮጵያዊ ላይ ለምጫን እየተፍጨረጨሩ ይገኝሉ ፡፡ለምሳሌ ጀዎር መህመድ ልክ እንደ ጠገበ ዝንጀሮ ደረቱን እየደበደበ ያደረጋቸውን ኢንተርቪዎች ልብ ተብሎ ቢሰማ እራሱን እንደ ቄሮ መሪ በማስቀመጥ እኛኮ ብንፈልግ ኦሮሚያን መገንጠል እንችል ነበር፤ አሁንም ከፈለግን አሁንም መገንጠል እንችላለን ፡፡

ለ) በአሁኑ ወቅት ሁለት መንግስት ነው ያለው ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግስትና የቄሮ መንግስት ነው የሀገሪቱን እጣ የሚወስነው ግን ቄሮ ነው እያለ ዛቻውን ደርድሯል ፡፡ ይህ የፖለቲካ ድለላ አላማው ቄሮ በግልጽ ተደራጅቶ፤ እራሱን ወክሎ ለማቅርብና በፖለቲካ መድርክ ተሳትፎ ህዝብን ወክሎ፤ የፖለቲካ ፕሮግራሙን አሳውቆ በምርጫ ተወዳድሮ ስልጣን እንዲይዝ ሳይሆን የነ ጀዋር እና የነ ጸጋዬ አራርሳ ፍላጎት ቄሮ በተበታተነ መልኩ እንደተደራጀ የፖለቲካ ተጠያቂነት ሳይኖርበት ፤ ነገር ግን እነጀዋርና ጸጋዬ  በፈለጉ ጊዜ ቀውስን እንዲፈጠር በኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ልጓም የሚቆጣጠሩትና የነርሱን የአክራሪ ፖለቲካ አስፈጻሚ አድርገው መጠቀም የሚፈልጉት መሳሪያ ነው፡፡  ስለዚህ እነ ጀዋርና ጸጋዬ አራርሳ የሚፈልጉት ዲሞከራሲ ሳይሆን መንጋክራሲ (Mobocracy) ስለዚህ አሁን እያደረጉ ያሉት OMNና ፊስ ቡክ በመጠቀም አንደኛ እነ አብይንና እነ ለማን ያላቸውን ስልጣንና በኦሮሞ ኢትዮጵያን ያላቸውን ተቀባይነት ለመሸርሸር ኦሮሞን ፍላጎት የሚጻረሩ አድርጎ መሳል ፤ እነጀዋር የሚቃወሙት የእኢትዮጵያውነት ፖሊሲ ሲኖር ሚድያዎችን በመጠቀም ቅስቀሳ አድርጎ ፖሊሲውን ለማስቀየር ዘመቻ መፍጠር ፡፡ ኢትዮጵያዊነትን የሚደግፉ ሚዲያዎችን ለምሳሌ ኢሳትን ጸረ ኦሮሞ ነው እያሉ ዘምቻ ማካሄድ፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ግንቦት ሰብትን እንዲዚሁ ጸረ ኦሮሞ ነው እያሉ ዘመቻ ማካሄድ ምንም እንኮን ግንቦት ሰባት ለብዙ አመታት ሀገር ቤት እስከሚገቡ ድረስ ከነ ሌንጮ ለታ ጋር አብረው ህብረት መስርተው ሲሰሩን እንደነበር እያወቁ፤ ባጠቃላይ ዲሞክራሲ ሳይሆን በመንጋ ፖለቲካን እንደመሳርያ ተጠቅመው እነጀዋርና እነ ጽጋዬ አራርሳ ይህንን የዲሞክራሲያዊ ጭልጭልታ ሊያጨልሙ ቀን ከሌሊት እየሰሩ ነው፡፡

እስካሁ ድረስ ግን ይህ ጸረ ዲሞክራሲያዊ  ስራቸው ተገምግሞ ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ አልተሰጣቸውም ፡፡ ይህ ደግሞ ጊዜው በሄደ ቁጥር ይህንን የሚያቀናብሩት እነ ጀዋርና ጸጋዬን እንዲሁም የጭፊን ተከታዮቻችው ልብ እየደለበ ለበለጠ ጥፋት ሁላቸንን መዳረግ እንደሚችሉ ተገዝበን ኢትዮጵያው የዜግነት መብታችንን መጠበቅና መከላከል መብታቸን መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ ኢትዮጵያዊያን ማኛውም ቡድንም ይሁን ፖለቲካ ፓርቲ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የዲሞክራሲ መብታችንን ሊቀርፍ የሚሞክሩ ማንኛውንም ሃይል በተቀነባበረ ዲሞክራሲያዊ መንገድ መልስ መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ እጃችንን አጣጠፍን ተቀምጠን በበር የሸኘነውን አንገፊጋፊ የዘረኛች የጭቆና ዘመን በአዲስ የመድረክ ተጫዋቾች በጓዳ ሊያስገቡ ሲሞክሩ ዝም ብሎ ተመልካች መሆን ማክተም አለበት፡፡

Filed in: Amharic