>

የሰዉ ደም ያክለፈልፋል፤ ያቅበዘብዛል፤  አዙሮ አዙሮ ወልቃይት ላይ ይጥልሃል!!! (ውብሸት ሙላት)

የሰዉ ደም ያክለፈልፋል፤ ያቅበዘብዛል፤  አዙሮ አዙሮ ወልቃይት ላይ ይጥልሃል!!!
ውብሸት ሙላት
 * የወልቃይት አማራ ላይ የደረሰዉ ግፍ እንደማግኔት ስቦ ክንፈ ዳኛውን እና ተክለብርሃንን ከመቐሌ ጎትቶ በማምጣት ማይካድራ የተባለች የድንበር ከተማ ግፍ የዋሉበት ህዝብ እጅ ላይ ጥሏቸዋል።  ከንስሮቹ ዓይን ማምለጥ የለም!!!
 
የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መግለጫ የሰማ ሰዉ ሁሉ እንደ አገር በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን ሲያስብ ምን ያህል ዉስጡ እንደሚደማ መገመት ቀላል ነዉ፡፡ በብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት (NISS) ተቋም ኃላፊዉ አጋፋሪነት የተፈጸሙት እጅግ ሰቅጣጭ በደሎች ማንነትን መሠረት ያደረጉ እንደነበሩም ተነግሯል፡፡
እኛ ለአመታት ብንጮህበትም ሰሚ አጥተን የነበረው አሰቃቂው የስቃይና የሰቆቃ ታሪክ ዛሬ በኦፊሴል ተዘረገፈ። የወንጀል ድርጊት ተሳታፊ የነበሩትም ተጠያቂም የሚሆኑት ሥፍር ቁጥር አይኖራቸውም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዛሬ ከተዘረገፈው የወንጀል ዶሴ መረዳት ይቻላል፡፡
እንግዲህ ለዚህ ሁሉ ሰቅጣጭ የበደልና የጭቃኔ ድርጊት ፊት አዉራሪ በመሆን የጋፈሩት ጌታቸዉ አሠፋ (የNISS ኃላፊ ናቸው፡፡ የሰኔ 16ቱንም ጭምር፡፡ በሜቴክ በኩል የተደረገው አገራዊ ዝርፊያ ኢትዮጵያ ላይ የዝርፊያ ጦርነት አዉጀዉ ያዋጉት ጀኔራል፣ክንፈ ዳኘዉ ናቸዉ፡፡
ሥራቸዉን የሚያዉቁት እነዚህ ቡድኖች ከአዲስ አበባ ኮብልለዉ መቀሌ መሽገው ከርመዋል፡፡
 የሰዉ ደም ያክለፈልፋል፤ ያቅበዘብዛል፤ አዙሮ አዙሮ ወልቃይት ላይ ይጥልሃል።
 የወልቃይት አማራ ላይ የደረሰዉ ግፍ እንደማግኔት ስቦ ክንፈ ዳኛውን እና ተክለብርሃንን ከመቐሌ ጎትቶ በማምጣት ማይካድራ የተባለች የድንበር ከተማ ግፍ የዋሉበት ህዝብ እጅ ላይ ጥሏቸዋል።  ከንስሮቹ ዓይን ማምለጥ የለም።
ጌታቸዉ አሰፋን እዚያ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን የተቻለ አይመስልም፡፡ በእርግጥ በቅርቡ ወንድሙ (ዶ/ር ደረጀ አሰፋ) ሲሞት ኃዘን ላይ የነበሩ ሰዎች በሦስት ቀን ሦስት ዓይነት የተለያየ መልክ ነበረዉ ብለዉኛል፡፡ እናም ጌታቸዉ ghost (ቅዱስ ስለማይሆን እርኩስ መንፈስ) ነዉ አሉኝ፡፡ እርግጥ የፊትን መልክ (ቀለም) መቀያየር ቀላል ነዉ፡፡  ይሁንና ፊቱንም ድምጹን ስሙንም ቀያይሮ በተለያየ ፓስፖርት በመጠቀም ወይም እዚሁ አገር ዉስጥ ሆኖም እምጥ ይግባ እስምጥ ላይታወቅ ይችላል፡፡
የሆነዉ ሆኖ እነዚህን ወንጀለኛ የሚለዉ ቃል የማይገልጻቸዉን ሰዎች የእዉነት የትግራይ ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ለፖሊስ  አሳልፎ መስጠት አለበት፡፡  ሕወሓትም አሳልፋ መስጠት አለባት፡፡ እንደዉም በትግራይ ክልል ፖሊስ በኩል እያደነች አንቃ መስጠት አለባት፡፡
አሁን ሕወሃት አጣብቂኝ ላይ ናት፡፡ እነ ጌታቸዉ አሰፋን አሳልፋ የመስጠትና ያለመስጠት አጣብቂኝ፡፡ በተለይ ጌታቸዉን በሚመለከት በፍጥነትም ከሕወሓት ሥራ አስፈጻሚነት ማንሳት፣ ከደብረፂዮን የጸጥታ አማካሪነት ማገድ ይጠበቅባልታ፡፡
ዶ/ር ደብረፂዮን የሐዋሳዉ ጉባኤ ላይ ባለፉት 27 ዓመታት የተፈጸሙትን አሰቃቂ ወንጀሎች (ዛሬ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የገለጿቸውን) ይፈጸማሉ ብለዉ ገምተዉ እንደማያዉቁ በመግልጽ በጣም በተደጋጋሚ የደረሰዉን ስቃይ እየገለጹ “ያማል! ያማል!” ሲሉ እንደነበር ከተሳታፊዎች ሰምተናል፡፡ ከዚሕ ባለፈም እንዲህ ዓይነት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን “ይሰቀሉ ቢባል እንኳን እተባበራለሁ፡፡ ለሕግ እንዲቀርቡ ያቻልኩትን ያህል አድርጋለሁ ብለዋል” አሉ-እዚያዉ የሐዋሳዉ ጉባኤ ላይ፡፡ ይህንን ቃላቸዉን ያከብራሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይህንን ቃላቸዉን ማክበር አለማክበራቸዉንም የምናዉቅበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ያዉ ሜዳዉም ያዉ ፈረሱም ያዉ!
ይሁን እንጂ ደብረፂዮን ሕዝቡንም ሕወሓትንም አስተባብረዉ የመቀሌ ከተማን የደደቢት ዋሻ ያደረገዉን የወንጀለኛ ቡድን በመስጠት እና ባለመስጠት መካከል የሚኖርባቸዉን አጣብቂኝ ቀላል እንደማይሆን ማንም የሚስተዉ አይደለም፡፡ እንኳንስ ለደብረፂዮን ለአገሪቱም የሚመለስ ቀላል ቡድን አይደለም፡፡
 የሆነ ሆኖ የደብሪፂዮን አጠባቂኝ የዳኒሹን ፈላስፋ የሶረን ኬርኬጋርድን ጽሑፍ (ሐሳብ) ያስታውሰናል፡፡ እ.አ.አ. በ1843 የተጻፈ ነዉ፡፡ እንዲህ ይላል ርእሱ- “Either/Or: A Fragment of Life” በሕይወት አጋጣሚ የሰዉ ልጅ በቃ ከሁለት አማራጮች አንዱን ብቻ እንዲመርጥ የሚገደድበት ወቅት አለ፡፡ ወደዚያ ወደዚህ የማያፈናፍኑ አምባገነን አማራጮች፡፡ ሌላ ምሳሌ መስጠት ሳያስፈልግ አሁን በደብረፂዮን ፊት የተደቀነዉ ወይ አልሰጥም ብሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቆራረጥ፣ከሕግ የበላይነትና ፍትሕ መጣላት፣ ወይም ደግሞ እነዚህን ወንጀለኞች አሳልፎ በመስጠት የትግራይንም ሆነ መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ መቆም፣ለሕግ የበላይነትና ለፍትሕ መከበር ማገዝ የሚሉት አማራጮች ናቸዉ ያሏቸዉ፡፡
 Now is the time when Debretsion’s fragment of life is facing with two tyrannical choices but only one of them will transcend him the trap of double regret!
በአንድ በኩል ያለዉ ያለመስጠት አማራጭ የሚመጣዉና አስጨናቂ ሁኔታ ዉስጥ የሚከተዉ አብረዉ ለዘመናት በዝምድና በጓደኝት በአንድ ብሔርነት የተጠፈረ ግንኙነት እና ተፈላጊዎቹ እጅግ አደገኛ የወንበደና ማፊያ ቡድን ስለሆኑ እንኳንስ ደብረፂዮንን አገሪቱንም የሚያሰጉ ስለሆኑ ደብረፂዮንን ሊያስገድዱትም ጭምር ስለሚችሉ ነዉ፡፡
ደብረፂዮን አሳልፎ ለመስጠት ካልተባበሩ፣ብሎም ለእነ ጌታቸዉ ካገዙ ያዉ ሁለተኛ ጥፋት መሆኑ ነዉ፡፡ መያዛቸዉ ላይቀር ትርፉ ሕዝባዊ ቅያሜን ማምጣት ነዉ፡፡  እስከዛሬ ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈጸም ማጣራት፣መከታትል፣መስማት ባለመቻላቸዉ እንደሌሎቹ ደብረፂዮንም ጥፋት አለባቸዉ፡፡
አሳልፈዉ ካልሰጡ ደግሞ የበለጠ ሌላ ጥፋት መሆኑ ነዉ፡፡ ኋላ የተያዙ ጊዜ ከሌላዉ ሕዝብ ጋር በሚኖርዎት ግንኙነት እንዳይጸጸቱ አሳልፈዉ ይስጡ፡፡
ሁለተኛ አያጥፉ፡፡ የኬርኬጋርድ “የወይ ይኼ፣ ወይም ያ” ብቻ አማራጭ ለደብረፂዮን መዳኛ፣መታረቂያ መፍትሔን ይዟል፡፡ ተቃራኒ አማራጮች፡፡ ነገር ግን አንዱ መጥፊያ ሌላዉ መዳኛ ነዉ፡፡ መዳኛዉ አሳልፎ መስጠት ስለሆነ ለዚሁ ተግባር መተባበር ነዉ፡፡ ከዚያም ከሁለተኛ ጥፋት መዳን፡፡
Filed in: Amharic