>
5:13 pm - Saturday April 19, 6577

የመንደር አምባገነነኖችን ማስታመምና ማስተናገዱ እስከመቼ?!? (ነአምን ዘለቀ)

የመንደር አምባገነነኖችን ማስታመምና ማስተናገዱ እስከመቼ?!?
ነአምን ዘለቀ
 ህግና ስርአት  መከበር አለበት፡ የፌደራል መንግስታና የክልል አስተዳደሮች ስረአተ አልበኞችን ብቻ ሳይሆን በታችኛው እርከን ላይ የሚገኙ የአስተዳደርና የደንነት ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።  እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ የመኖር፡ የመንቀስቀስ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ የማደረጀት፣ የመስብሰብ ፓለቲካዊና  የሲቪል መብቶች ሙሉ በሙሉ መከበር አለበት። በዚህ ላይ ድርድር መኖር የለበትም፡ ዜጎች በማናቸውም ቦታ ለሚያደርጉት ስላማዊ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ሙሉ ደህነትና ዋስትና መንግስት መስጠት ሃላፊነት አለበት። የመንደር አምባገነነኖችን ማስታመምና ማስተናገድ ለወደፊቱ ጠንቅ ነው።
በአነ ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው ለውጥ አራማጅ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት አየወሰደ በሚገኘው ልዩ ልዩ እርምጃዎች የተገኙና  በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች በእጅጉ የሚደነቁና የሚበረታታ ሂደት ቢሆንም፡ ሰረአት አልበኝነት አሁንም እንደነገሰ ነው፣ በስረአተ አልበኞች ብቻ ሳይሆን በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የዞን፡ የከተማ፡ የወረዳ የአስተዳድርና የደህንነት አካላት ከስረአት አልበኞች ጋር በመተባብር ዜጎች ላይ ድብደባ መፈጸም፣ መዘርፍ፣ ወይንም ወከባ፣ ድብደባና ዝርፊያ ሲፈጸም እርምጃ አለመውሰድ ብቻ ሳይሆን ተባባሪ የመሆንም ሁኔታዎች በልዩ ልዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መከሰታቸው ቀጥለዋል። ሰሞኑን በጅማና በአሰላ በአካባቢዎች የአስተዳደርና የደህንነት አባላት እውቅና አልፎም ትብብር ጭምር በኢትዮጵያውያን ዚጎች  ላይ የተደረጉ ህገ ወጥ ድርጊቶች የመበት ረገጣ፣ እስር ፣ ወከባ፣ ዘረፋና ድብደባዎች የዚህ  የስረአተ አልበኝነትና የክልልና የፌደራል መንግስትና አስተዳድሮች  የዜጎችን ደህነት ለመጠበቅ፣ መብቶቻቸውን  ለማስከበር አቅም በእጅጉ ማነስ    የሚያሳዩ መገለጫዎች ናቸው።
የዜጎችን ደህንነትና መብት የሚረግጡና የሚያስረግጡ የታችኛው የመንግስት እርከን ባለስልጣኖች ተጠያቂ ማደግ የክልልና የፌደራል መንግስት ሃላፊነት በመሆኑ አነዚህ ድርጊቶች በፈጸሙና ባስፈጸሙት የመንግስት ባለስልጣኖችና ተመራጮች  ለህገ ወጥ ተግባሮቻቸው ተጠያቂ ማድረግ፣ ብሎም  ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፣ ወደ ህግ ፊት ማቅረብ ካልተቻለ አሁንም እንደቀድሞው ዜጎች የሚደርስባቸው የመብት ገፈፋና ረገጣ ይቀጥላል ማለት ነው።
የፌደራል መንግስታና የሚመለከታቸው የክልል አስተዳደሮች ይህን የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋት፡ የዜጎች ደህነትና መብቶች መጠበቅ እነደ ወሳኝና ቅድሚያ  ትኩረት የሚሻ ጉዳት አድርገው በመውሰድ እግር በእግር እርምጃ ካልወሰዱ ተመሳሳይ ድርጊቶች እየቀጠሉ ይሄዳሉ፡ እነዚህን ህግና ስርአትን የማሰጠበቅ እርምጃዎች መውሰድ ካለተቻለ ህዝብ ለውጡን እንዳያጣጥም፡ ብሎም  ሰላም ፣ መረጋጋት እንዳይሰፍን  አልፎም የለውጡን ሂደት ወደ ወደ ሰከነ፡ የተረጋጋና፣  ሰላማዊ ሀገራዊ ከባቢ  ለማሸጋገር አዳጋች አየሆነ ይመጣል።
Filed in: Amharic