>

የትግራይ ሰልፍ ፖለቲካዊ አንድምታዉ (non-partisan) 

የትግራይ ሰልፍ ፖለቲካዊ አንድምታዉ (non-partisan)
 
ሚኪ አምሀራ
የትናንትናዉን የትግራይን ሰልፍ ተከታትያለዉ፡፡ ብዙዉ ሰዉ ያዉ ሙድ ሲይዝበት ነበር፡፡ እነሱ ግን ያሰቡት ጉዳዩ ወዲህ ነዉ፡፡ ማለቴ ፖለቲካዉ ሌላ ነዉ፡፡ አሁን ላይ ህወሃት እየተከበበ መሆኑ ገብቶታል፡፡ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ እየተወገደ መሆኑም እንዲሁ፡፡ የኤርትራ በፈለገዉ መንገድ ቀና አለመሆን አሳስቦታል፡፡በአለም አቀፍ ደረጃ ስሙ መጉደፉ አበሳጭቶታል፡፡ የትናንነትናዉ መልክት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካ፤ ለአዉሮፓ እንዲሁም ለሌሎች የቀጠናዉ ሰላም ለሚያሳስባቸዉ ነዉ፡፡ በሰልፉ ማስተላለፍ የፈለጉት መልክት ህወሃትን ማራወጥ ላይ የማታርፉ ከሆነ እና በዚህ የምትቀጥሉ ከሆነ አገሪቱ ለሁላችንም እንዳትሆን እናደርጋለን ማለታቸዉ ነዉ፡፡ It is all about themselves refusing not to go away.  አሜሪካ እና አዉሮፕያዉያን የተረጋጋ አካባቢ ፈጥረዉ እነሱም የሚበዘብዙትን መበዝበዝ ነዉ ፍላጎታቸዉ፡፡100 ሚሊየን ህዝብ የያዘ ሀገር ያልተረጋጋ እንዲሆን አይፈልጉም፡፡ አዉሮፓን እያፈራረሳት ያለዉ ስደተኛ ነዉ፡፡ ለዚህም ነዉ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚፈሩት፡፡
 ህወሃት አሁን ብሎ የሚያስበዉ ኢትዮጵያን hostage አድርጊያታለዉ ነዉ፡፡ እናም ሰልፉ ለመደራደሪያ አቅም መፍጠሪያ ነዉ፡፡ አምባገነኖች ህዝባዊ አመጽ እየተቀጣጠለባቸዉ ሊበላቸዉ ጫፍ ሲደርስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ፡፡ ደጋፊወችን ሰልፍ ማስወጣት፤ ብጥብጥ በሌላ አካባቢ መፍጠር እና የመሳሰሉት፡፡ ይሄን በሳዳም አይተነዋል፤ በጋዳፊ አይተነዋል፤ በሆስኒ ሙባረክ አይተነዋል፡፡ በመሆኑም አሁን ካለቻቸዉ ፓወር በታች ከወረዱ የበሉትን ገንዘብ ሊመልሱ ነዉ፤ የዘረፉትን መሬት ሊመልሱ ነዉ፤ በአዉሮፓ ያከማችቱን ገንዘብ ሊመልሱ ነዉ፤ ሊታሰሩ ነዉ፡፡ እነዲያዉም ተጀምሯል፡፡ ስለዚህም የሚያወጣቸዉ here and there chaos መፍጠር ደጋፊን በማሰለፍ ህዝብ ከጎናችን አለ በማለት የመደራደር አቅምን ማግኘት ነዉ፡፡ የአሜሪካዉ አምባሳደር ለማሸማገል በሚመስል ጉዳይ ሰሞኑን መቀሌ ነበር፡፡ ነገር ግን ግትር ብለዉበታል፡፡ መቀሌ ጉዳዩን ጠይቆ ወደ ባህርዳር የተጓዘብት ምክንያትም ከአዴፓ ጋር ለማሸማገል ነዉ፡፡ ይህች ሽምግልና ስለተጀመረች ሰልፏ ማስፈራሪያ ናት፡፡ይተርፋሉ ወይ ነዉ ጥያቄዉ፡፡ እነ ጋዳፊ እነ ሆስኒ ሙባረክ ተርፈዉ ከሆነ እንሱም ይተርፋሉ፡፡ ዋናዉ የሰልፉ ጭብጥ እና ፖለቲካዉ ይሄዉ ነዉ፡
Filed in: Amharic