>
5:13 pm - Thursday April 18, 6937

እረ የሃላፍነት ስሜት ይሰማን!!!  (ገረሱ ቱፋ)

እረ የሃላፍነት ስሜት ይሰማን!!! 
ገረሱ ቱፋ
ላለፉት ዓመታት ስልጣን ላይ የነበረው የፖለቲካም የኢኮኖሚ የበላይነት የነበረው ሃይልስ ለምን እንደሚበጠብጥ ግልጽ ነው። ለዛው ሃይል ተግባራዊ አጋርነት( practical partnership) እየሰጡ ያሉ የፖለቲካ ጆከሮቻችን ግን ይገርማሉ!
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የሚታየው ችግር እጅግ የተወሳሰበ እና ብዙ ተገዳዳሪ ፍላጎቶችን አቻችሎ መሄድን የሚጠይቅ እና ፈታኝ ነው። ብዙ ጥንቃቄ የሚጠይቁ አዳዲስ እና የቆዩ ችግሮች ስላሉ ተገዳዳሪ ፍላጎቶቻችን እያቻቻሉ ታክቲካዊ እና ስትራቴጃዊ ችግሮችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና የሃላፊነት ስሜት እየለዩ እና እየፈቱ መሄድ ያስፈልጋል።
በተቃራኒው፣ በአሁኑ ሰዓት የትኛውም አሁን ስልጣን ላይ ያለውን ሃይል እተካለሁ የሚሉ ቡድኖች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩትን ውስብስብ ችግሮች በተሻለ ሁኔታ እና ፍጥነት ለመፍታት የሚያስችላቸው የአደረጃጀት ብቃት እና ተግባራዊ ራእይ ሲያመጡ አይታይም።ከዚያ ይልቅ እነሱ የሚያደርጉት ህዝባችን ገና ያልተፈቱ ችግሮች ስላሉት እነሱኑ በአጭር ጊዜ የሚፈቱትንም የማይፈቱንም ማራገብ እና የለውጥ ሃይሉ በዕለት ዕለት የማረጋጋት ስራ ላይ ብቻ እንዲጠመድ ማድረግ ነው። ይሄ ደግሞ እራሱን ወደሚያሳካ ትንብት(self fulfilling prophecy) ልያመራ እና “ብለን ነበረ” ልያስብል ይችላል። ላለፉት ዓመታት ስልጣን ላይ የነበረው የፖለቲካም የኢኮኖሚ የበላይነት የነበረው ሃይልስ ለምን እንደሚበጠብጥ ግልጽ ነው። ለዛው ሃይል ተግባራዊ አጋርነት( practical partnership) እየሰጡ ያሉ የፖለቲካ ጆከሮቻችን ግን ይገርማሉ። በለውጡ እጅግ ከፍተኛ ተፅእኖውን ያጣው አካል የትኛውም ሃይል ለፈለገው ኣላማ ህዝብን ካነሳሳ ለጊዜው ለነሱ ተገባራዊ ወዳጅ(practical partner) ነው። “የፖለቲካ ጆከሮች” ደግሞ ለዚህ በጣም ይጠቅሙታል። እኛ ሃገር ውስጥ ብዙ የፖለቲካ ጆከሮች አሉ። የፖለቲካ ጆከሮች የምላቸው ሃይሎች ምንም አይነት ወጥነት ያለው ስትራቴጃዊ የፖለቲካ ግብ፣ ራዕይ አና ወዳጅ የሌላቸው እና ምንም ዓይነት ህዝብን ያንቅሳቅሳል የሚሉ ነገሮችን የሚያስተጋቡ እና ከየተኛውም ሃይል ጋር በየትኛውም ጊዜ ታክትካል(ጊዘያዊ) ወዳጅነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው።
ችግሩ አሁን ያለው አንጻራዊ ለውጥ በሚደረግበት ግፊት ከመስመር ከወጣ እና ሀገራችን ሙሉ በሙሉ ትርምስ ውስጥ ከገባች እነዚህ የፖለቲካ ጆከሮች “ብለን ነበረ” ከማለት ውጭ ግልፅ የሆነ የመፍተሔ ሀሳብ የላቸውም።
እንዲያውም ወደትርምስ የማምራት እድላችንን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጨምር ተግባር ላይ ሁሉ በግልፅ ይሳተፋሉ። ስለዚህ ህዝባችን የጉዳዮን ውስብስብነት ተረድቶ በጆከሮችም በለውጡ ከከሰሩትም ፣ ተገባራዊ ወዳጅነታቸውም (practical partnership) የሚመጣውን መዘዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያየው ይገባል።
Filed in: Amharic