>
5:18 pm - Tuesday June 15, 9294

"የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት እንድ አይደለም!" (የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ)

“የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት እንድ አይደለም!” የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ
 ትናንት ከወደ መቀሌ የተሰራጨው የ6 ደቂቃ ቪዲዮ
– አቶ በረከት እርስዎ  ከስብሐት ነጋና ከአቶ መለስ ጋር ሆነው ጽንፈኝነት አምጥተውብናል፡፡
– ኢህአዴግ ተመርጦ ያውቃል እንዴ? ኮረጆ ሲዘርፍ እኮ ነው የኖረው!!
– እንኳን ሕገ-መንግስት፣ ህወሃት የራሱን ህገ ደንብ አክብሮ አያውቅም፡፡
– በዚህ 27 ዓመት ሕገ-መንግስት አልተከበረም፤ ዴሞክራሲ አልነበረም፡፡
– የትግራይ ሕዝብ እና ሕዋሃት እንዴት ሆነው ነው አንድ የሚሆኑት?
– አሁንም በስደትና በጉስቁልና ላይ ነው ያለው፡፡…”
– እኔ እኮ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኮንፈረንስ መስሎኝ ነበር፤ የህዋሃት ወሬ እንዳለው አልገባኝም፡፡
• ኢህአዴግ ተመርጦ ያውቃል እንዴ? ኮረጆ ሲዘርፍ እኮ ነው የኖረው!! በኃይል ነው እስካሁን የቆየው፡፡ አሁን ከፌደራል ስልጣን ስለተባረረ ነው፤ በራሱ ሲደርስ ነው ይሄ ሁሉ ጫጫታ የበረታው፡፡
•እርስዎ (አቶ በረከትን) ከስብሐት ነጋና ከአቶ መለስ ጋር ሆነው ‘ትግራይ ብቻዋን እየለማች ነው!’ ብለው ጽንፈኝነት አምጥተውብናል፡፡ የትግራይ ወጣት ቁጭት አለበት፡፡
•ዛሬ ላይ ህወሃት ከፌደራል /ከአዲስ አበባ/ ሲባረር ነው፣ ትግራይ እንደሚጠፋ፣ የትግራይ ህዝብ እንዳለቀለት፣ በጠላት እደተከበበ በኃይለኛው እየተቀሰቀሰ ያለው፡፡ ነገር ግን በአንጻሩ ከኤርትራ ጋር ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጀምሯል፡፡
• ምርጫ ሲጭበረበር ነው የኖረው፤ በዳኝነት ላይ ጣልቃ ሲገባ ነበር፡፡
•እንኳን  ህገ መንግስት፣ ህወሃት የራሱን ህገ ደንብ አክብሮ አያውቅም፡፡
 • ልዩነቱ፣ አሁን በትግራይ ያለው የህዋሃት አመራር ከፌደራል ስልጣን ስለተባረረ፣ እንደ አዲስ ነገር ተደርጓል፡፡ እዚህ ያለው አመራር፣ ‘#_አንጃ! #_አሸባሪ!” ሲል የነበረ ነው፡፡ እንጂ በዚህ 27 ዓመት ህገ-መንግስት አልተከበረም፤ ዴሞክራሲ አልነበረም፡፡
• የትግራ ሕዝብ እና ሕዋሃት አንድ እንደሆኑ ይገለጻል፡፡ እንዴት ሆነው ነው አንድ የሚሆኑት? ደሃ ህብረተሰብ፣ የሚበላ የሚጠጣ የሌለው ሕዝብ እና በትግራይ ህዝብ ስም በቢሊየን ብር የሚያንቀሳቅስ ባለስልጣኖች እየተጠቀሙበት እንዴት ብሎ ነው አንድ የሚሆኑ? አሁንም ትግራይ ሕዝብ በድህነት ላይ ነው ያለው፤ አሁንም በስደትና በጉስቁልና ላይ ነው ያለው፡፡…”
ጨብጭበጭ…ብብብ…
•አቶ በረከት ስምኦን አንዴ! አንዴ! ቆይ ይጨርስ….አንዴ ይጨርስ….
ሃሳቤን ላጠቃልል….አስጨርሱኝ….
ጨብጨብጨብብብብ….
 እኔ እኮ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኮንፈረንስ መስሎኝ ነበር፤ የህዋሃት ወሬ እንዳለው አልገባኝም፡፡
ተቋረጠ
ቪዲዮውን ይመልከቱ
Filed in: Amharic