>
5:13 pm - Thursday April 19, 6362

በአባይ ጸሃዬ ምክንያት የታሰረው ኢንጂነር በእስር ቤት ህይወቱ አለፈ (ሪፖርተር)

በአባይ ጸሃዬ ምክንያት የታሰረው ኢንጂነር በእስር ቤት ህይወቱ አለፈ
 
* ሪፖርተር ክሱ ተቋርጦ ነበር ያለው ሃሰት ነው (ቤተሰቦቹ)
ኢንጂነር አበበ ይባላል፣ የሃገራችን በትልልቅ ፕሮጀክት ላይ ተሳትፏል፤፡ ጊቤ፣ ተንዳሆ፣ ተከዜ እና ሌሎችም በፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነት ሰርቷል፡፡ ከመታሰሩ በፊት በስኳር ኮርፖሬሽን በኮንትራት አስተዳደርነት እያገለገለ ነበር፡፡
የስኳር ፋብሪካዎችን ሜቴክ ሲጨማለቅባቸው የነበሩትን በትልቅ ካምፓኒ እንዲሰራ ጥረት አድርጎ ኦሞ 5 ፋብሪካን በውጪ ካምፓኒ እንዲሰራ አድርጎ በፓርላማ ጭምር ፕሮጀክቱ የተመሰገነ ሆኗል፡፡ ነገር ግን በሃምሌ 2009 መንግስት(የቀድሞው ህዋሃት፣ የአሁኑ የድሮ ስርት ናፋቂው) ለፖለቲካው ሲል ሰዎችን ማሰር በጀመረበት ሰአት፣ እሱን እና ሌሎች ባለሙያዎች ማእከላዊ ተጠርተው አባይ ጸሃዬን ልናስረው ስለሆነ ለምስክርነት ተዘጋጁ ይሏቸዋል፡፡
ከአባይ ጋር የሚታሰሩ ሰዎችም ቀድመው መታሰር ቀጥለው ምስክር ማሰብሰቡ ወደማለቁ ሲደርስ፣ ህውሃት አባይን አላሳስርም ይላል፡፡ በዚህ ሰአት ኢንጂነሩን ጠርተው አባይን አናሳስርም እያሉ ስለሆነ ሌላ የማያውቀውን እና አባይን የሚከስ የሃሰት ምስክርነት እንዲሰጥ ይጠይቁታል፣ አሱ ግን የማውቀውን ብቻ ልምስክር ብሏቸዋል፡፡ ይህ ጥያቄ ለሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ቀርቦ እቢ በማለታቸው ታስረዋል፡፡ መጨረሻ ላይ ለምስክረንት ያሰቡትን ሰውዬ አሰሩት፡፡ ሃሳቡ ሲቀየር ሌላ ሽመልስ የተባለውን ደግሞ ጥፋ ተብሎ ቢከሰስም በሌለበት ጉዳዩ እየታየ ነው፡፡ ይህንንም ያደረገው በዋነኛነት መዝሙር ያሬድ የተባለው በጠቅላይ አቃቤ ህግ የሙስና ዳሬክቶሬት የነበረው ሲሆን፣ በቀኝ እጁ እስኪሪቢቶ በግራ እጁ ዱላ ይዞ ለሊት ለሊት ይመረምር እንደነበር ሰምተናል፡፡ ከመዝሙር ጋር አብረው የሚመረምሩት ደግሞ ምስክር ሆነው የቀረቡት ጄነራሎች ነበሩ፡፡ መጀመርያ ቃል የተሰበሰበው ለአባይ ጸሃዬ ስለነበረ፣ በችሎት ላይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት መሃል ዳኛ አቶ ከበደ፣ አባይ ፀሃዬ በሌለበት ስለሱ በመስማት ሲቸገሩ እና ከጠበቆች ጋር ክርክር እንደነበር ተስተውለዋል፡፡
 አሁን አባይ መቀሌ ተደብቋል፣ ከነ ኮሚሽነር ረታ (የማእከላዊ የቀድሞ አዛዥ) ጋር ተነግሯቸው መዝሙር ጠፍቷል፣ ይህንን እያወቀ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሌሎች ሙሰኞችን፣ እነ ገብረዋህድን፣ ዛይድ ወ/ገብርኤልን ለሃገር መግባባት በሚል ፈቶ እነ ኢንጂነሩን ግን ለሃገር መግባባት አትጠቅሙም ብሎ ሳይፈታቸው ይቀራል፡፡ በዚህ የተበሳጨው ኢንጂነሩ ቂሊንጦ እያለ በብስጭት ሃገሬን ማገልገሌ ይህ ነው ወይ በሚል አንደበቱ መናገር ያቅተዋል፣ ህመሙም ጸንቶበት ለህክምና ብዙ በህመም በእስር ቆይቶ በአስራ አንደናው ሰአት ሆስፒታል ቢገባም ህይወቱ አልፏል፡፡
አሁንም ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወንጀለኛና ንጹሃንን ቢለይ ከሌላ ጸጸት ሊታደግ ይችላል፡፡
በምድር ያጣኸውን ፍትህ በሰማይ እንደምታገኘው እናምናለን በግፍ አብረውህ ከታሰሩ ወድሞችህ የሚል በመቃብሩ ላይ አበባ ጉንጉን ወዳጆቹ አስቀምጠውለታል፡፡
ነፍስ ይማር
Filed in: Amharic