>

ለኦሮሞ ህዝብ ትናንት እውቀታቸውን ፤ ዛሬ አንገታቸውን ለመስጠት በጽናት የቆሙ ባለውለታ!!! (አፈንዲ ሙተቂ)

ለኦሮሞ ህዝብ ትናንት እውቀታቸውን ፤ ዛሬ አንገታቸውን ለመስጠት በጽናት የቆሙ ባለውለታ!!! 
አፈንዲ ሙተቂ
* “እሄን እርቅ ለማሳካት ከብት ማረድ ካስፈለገ ገዝተን እናርዳለን። ሰዉን ማረድ ካስፈለገ ደግሞ እኔን እረዱኝና በኔ ደም እርቅ አዉርዱ”

 

ይህን ማንንም ድንጋይ ልብ አለኝ የሚልን ሰብአዊ ፍጡር ልብ የሚሰብር ንግግር ያደረጉት አቶ ሀይሌ ገብሬ ይባላሉ ።
 አቶ ሀይሌ ገብሬ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ መስራችም ናቸዉ። የኦሮሞ ህዝብ ባንክ የመክፈት አቅም የለዉም ሲባል የኦሮሞ ህዝብ ብዛት 50 ሚሊዮን ነዉ እያንዳንዱ ሰዉ አንዳንድ (1ብር) ብር ብያዋጣ 50 ሚሊዮን ብር ይሆናል በማለት እንቅስቃሴ ይጀምራሉ። በወቅቱ ባንክ ለመክፈት የሚያስፈልገዉ ካፒታል 10 ሚሊዮን ብር ነበረ። ብር ማሰባሰብ ጀምረዉ እርሳቸዉ ሰብስበዉ አስር ሚሊዮን ሲሞሉ ካፒታሉ ወደ 35 ሚሊዮን አደገ አሁንም እንደምንም ተሯሩጠዉ 35 ሚሊዮን ሲሰበስቡ ካፒታሉ ወደ 75 ሚሊዮን አደገ።
እኚህ አባት ግን ተስፋ አልቆረጡም የኦሮሚያ ገበሬዎችንና የመንግስት ሰራተኞችን አሳምነዉ የዛሬዋን የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እዉን ማድረግ የቻሉ ጀግና አባታችን ናቸዉ። ይህ አባት ትናንት በተካሄደዉ የኦሮሞ ፓርቲዎች የእርቅና የሰላም ኮንፈረስ ላይ ልብ የሚነካ ንግግር አድርገዋል።
ኦቦ ሃይሌ ገብሬ ዕድሜ ልካቸውን ለደሃ የኢትዮጵያ ገበሬዎች መብትና ጥቅም ሲናገሩና ሲፋለሙ የኖሩ ጀግና ናቸው።
# የኦሮሚያ ቡና ላኪዎች ዩኒየን፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ዩኒየን እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የተመሠረቱት  በእርሳቸው ያላሰለሰ ጥረት ነው።
# በእርሳቸው አካሄድ ያልተደሰተው የወያኔ መንግስት እርሳቸውን ከኦሮሞ ገበሬ ለማራቅ የፌዴራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዳይሬክተር  አድርጎአቸው ሊያደነዝዛቸው ሞክሮአል። እርሳቸውም ይህ ስልጣን በቅንነት እና ለኦሮሞ ህዝብ በማሰብ የተሰጣቸው እንዳልሆነ በመረዳታቸው ጥቂት ብቻ ስርተው የጡረታ ፎርም ሞልተው በግል መስራት ጀመሩ። ኦቦ ሃይሌ የታዋቂው የማሳቹሴትስ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ናቸው።
ኦቦ ሀይሌ ገብሬ እንደ እርስዎ ያሉ አባቶች ይብዙልን!
Filed in: Amharic