>
5:13 pm - Friday April 19, 5652

አዲስ አበባ ሆይ! የአማራና የኦሮሞ ብሔርተኞች ሊቀራመቱሽ አሰፍስፈዋል! አንቺ ግን ተኝተሻል! (ስዩም ተሾመ)

አዲስ አበባ ሆይ! የአማራና የኦሮሞ ብሔርተኞች ሊቀራመቱሽ አሰፍስፈዋል! አንቺ ግን ተኝተሻል!
ስዩም ተሾመ
የአዲስ አበባ #የነዋሪነት_መታወቂያ በአማካይ በ1200 ብር በገፍ እየተቸበቸበ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት #አዲስ_ከተማ ክ/ከተማ ዋና የሽያጭ ማዕከል ነበረ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ #ቦሌ_ሚካኤል ዋና የሽያጭ ማዕከል ሆኗል፡፡ የመታወቂያ ገዢዎቹ በአብዛኛው የኦሮሚያና አማራ ክልል ተወላጆች ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ መታወቂያ በገፍ የሚሸጥበት ዓላማ ለከተማዋ ነዋሪዎች ከሚዘጋጁ የመሰረተ ልማት አውታሮች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተጠቃሚ ከማድረግ ጀምሮ የራስን ብሔር ተወላጆች በከተማዋ በመሰግሰግ ቀጣዩን የአዲስ አበባ #ምክር_ቤት_ምርጫ በአብላጫ ድምፅ እስከ ማሸነፍ ይደርሳል፡፡ በእርግጥ ይህ ህወሓት ባለፉት 27 አመታት ውስጥ በተግባር ያደረገው ነገር ነው፡፡ ህወሓት ከአዲስ አበባ ተባርሮ መቀሌ ከመሸገ ወዲህ #አክራሪ #የኦሮሞና_አማራ ብሔርተኛ ቡድኖች የመታወቂያ ግዢውን በስውር እያበረታቱ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 5ሺህ የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች #ከባሌ_ጎባ በተፃፈ መልቀቂያ መታወቂያ ጠይቀዋል፡፡ በሌላ በኩል አክራሪ የአማራ ብሔርተኛ ቡድኖች በኢትዮጵያ ሆቴል ባደረጉት ስብሰባ ደጋፊዎቻቸው የአዲስ አበባን መታወቂያ በስፋት በመግዛት በከተማዋ አብላጫ ድምፅ መያዝ አለብን የሚል አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ አዲስ አበባ ሆይ! ህወሓት ግጦሻል፣ የአማራና እሮሞ ብሔርተኞች ሊቀራመቱሽ አሰፍስፈዋል፣ አንቺ ዛሬም ተኝተሻል?!
Filed in: Amharic