ሀብታሙ አያሌው
ይህ መልዕክቴ እንዲደርስዎ በቀና መንፈስ እንዲያዩትም በትህትና እጠይቃለሁ።
አራት ኪሎ እሪ በከንቱ መጠጊያ የሌላቸው እናቶች ህፃናቶቻቸውን ይዘው ጎዳና ላይ ወድቀዋል። ህፃናቱን እና የእናቶችን እንባ በዚህ ሁኔታ ማየት ልብ ያደማል እረፍት ይነሳል።
በእርስዎ አስተዳደር ስር ያሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እነዚህን ምስኪን መጠጊያ የሌላቸው ድሆች ህገወጥ ናችሁ በማለት መጠለያቸውን ድምጥማጡን አጥፍተው በዚህ ሁኔታ ለስቃይና ልእንግልት ዳርገዋቸዋል።
እርስዎ በዶክተር አብይ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ከመሾምዎ በፊት ኪራይ ቤቶች አስተዳደር በሰጠዎት ቤት ይኖሩ እንደነበረ አውቃለሁ። ስልጣን በተሰጥዎ ማግስት ግን ያ ባለ ሶስት መኝታ አፓርታማ ለክብርዎ አይመጥንም በማለት ከመንግስት ካዝና ከነዚሁ ዛሬ እያነቡ ጎዳና ከወደቁ እናቶች በታክስ ከተሰበሰበ ገንዘብ በወር 140 ሺህ ብር ገደማ ኪራይ ወደሚከፈልበት ክብርዎን ይመጥናል ወደተባለ ቤት መዘዋወርዎም ይታወቃል።
በቅርቡ በእርስዎ አስተዳደር እጅግ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ሶስት መስጊዶች እንዲፈርሱ ተደርጎ በቁጣ ስንነድ እቦታው ድረስ በመሄድ ስህተቱን ለማረም ያሳዩት የወሰዱትን እርምጃ እያደነቅሁ እነዚህን ዜጎች ፈጥነው ከጎዳና እንዲያነሱ። ንብረታቸውን ያቃጠሉ ጭነው የወሰዱና እነዚህን አይዞሆ ባይ የሌላቸው ድሃ አደጎች በግፍ የደበደቡ ፖሊሶች በህግ እንዲጠየቁ እንዲያደርጉ እንደ አንድ ዜጋ እማፀንዎታለሁ።