>
5:18 pm - Sunday June 15, 3158

አቡነ ጴጥሮስ በዚህ ወቅት ቢኖሩ  ዘመነኞቹ ምን ያደርጓቸዉ ነበር?  (ሸንቁጥ አየለ)

አቡነ ጴጥሮስ በዚህ ወቅት ቢኖሩ  ዘመነኞቹ ምን ያደርጓቸዉ ነበር? 
ሸንቁጥ አየለ
* ሁሉም ኦሮሞ ክርስቲያን ሊያሰላስላቸዉ የሚገቡ ቁልፍ ህሳቤዎች
ጣሊያን በከፍተኛ ገንዘብ ስልጣን እና ጥቅማ ጥቅም ሊደልላቸዉ ታላቁን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ እና የነጻነት ቀንዲሉን አቡነ ጴጥሮስን አግባባቸዉ::
“ኢትዮጵያን ለሮማ ካስገዛህልኝ….” ብሎ ሀሳቡን ሳይጨርስ አቡነ ጴጥሮስ እንዲህ አሉት:: “ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ሀገር ነች:: እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱ የኢትዮጵያ ምድር አይገዛልህ ! ብዬ እገዝታለሁ”  ብለዉ በአደባባይ ህዝብ ሰብስበዉ ግዝት አደረጉ::
ጥያቄዉ ግን አቡነ ጴጥሮስ ጣሊያን ሊገላቸዉ እንደሚችል እያወቁ ለምን እንዲህ አሉ? አቡነ ጴጥሮስ ለምን እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱ የኢትዮጵያ ምድር አይገዛልህ አሉ?
ይሄን የአቡነ ጴጥሮስን የነጻነት አስተምህሮት አሁን ካለዉ ሁኔታ ጋር እያስተሳሰራችሁ ለማንሰላሰል ሞክሩ?
አቡነ ጴጥሮስን የኔ ጎሳ ናቸዉ ብሎ ሲያበቃ የአቡነ ጴጥሮስን እምነት ለማጥፋት ደፋ ቀና የሚሉ ሰዎችን ሀሳብ እያንሰላሰላችሁ ቆዩ::
አቡነ ጴጥሮስን የኔ ጎሳ ናቸዉ ብሎ ሲያበቃ አቡነ ጴጥሮስ የእግዚአብሄር ምድር ያሏትን ኢትዮጵያን የካዱ ሰዎችን አጀንዳ እያንሰላሰላችሁ ቆዩ::
ጀዋርም ባንድ ወቅት አቡነ ጴጥሮስ ኦሮሞ ናቸዉ::”የአቡነ ጴጥሮስን ስም ነፍጠኞች ሆን ብለዉ የኦሮሞ ስም እንዳይሆን አቅደዉ ቀይረዉት ነዉ” ሲልም የአቡነ ጴጥሮስ ተቆርቋሪ ሆኖ  ተደምጧል::
ለመሆኑስ የአቡነ ጴጥሮስን “ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ሀገር ነች” የሚል አስተምህሮት ጀዋር መሃመድ ሲሰማ አቡነ ጴጥሮስን ምን ያደርጋቸዉ ነበር ብላችሁ ተመራመሩበት::
በሜንጫ አንገታቸዉን በሏቸዉ ይል ነበር ወይስ በአቡነ ጴጥሮስ አስተምህሮት ይስማማ ነበር?
ነዉ ወይስ “አይ እስላም ያልሆነ ኦሮሞ አይደለም” ይላቸዉ ነበር?
ነዉ ወይስ አንተ የምትላት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች መቶ አመት አይሞላትም::አንተ ያልተማርህ ስለሆንክ ነዉ ኢትዮጵያ የ እግዚአብሄር ሀገር የምትለዉ ይላቸዉ ነበር::
አቡነ ጴጥሮስ አሁን ቢኖሩ ኖሮ ጀዋር መሃመድ ምን ያደርጋቸዉ ነበር እያላችሁ ተደመሙ::
እናም አስከትላችሁ የአቡነ ጴጥሮስን ሚስጥራዊ የመንፈስ ቅዱስ አስተምህሮት የተላበሱትን ኦሮሞ ክርስቲያኖች ጀዋር መሃመድ በቀጣይ ምን ሊያደርጋቸዉ ይችላል ብላችሁ አስቡ::
በተለይም አቡነ ጴጥሮስ ከቀዱበት የ እዉቀት እና ጥበብ ምንጭ ደርሰዉ ኢትዮጵያ የ እግዛብሄር ሀገር መሆኗን የተማሩ: የተረዱ: የተመራመሩ ኢትዮጵያዉያን የተከበሩ ክርስቲያን ኦሮሞዎች ጀዋር መሃመድ ኢትዮጵያን ሲሳደብ እና ሲያዋርድ እንደ አባታቸዉ አቡነ ጴጥሮስ ” የለም ልክ አይደለህም:: ኢትዮጵያ እኮ የ እግዚአብሄር ሀገር ነች” ቢሉት ምን ያደርጋቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁ::
 የመጨረሻዉ ጥያቄ ለመሆኑ አቡነ ጴጥሮስ “ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ሀገር ነች” የሚለዉን አስተምህሮት ከዬት አገኙት? ይሄስ “ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ሀገር ነች” የሚለዉ ሀሳብ ምን ማለት ነዉ? እነዚህ እና ተዛማጅ ጥያቄዎችን ዛሬ ላይ ቆሞ ሁሉም ኦሮሞ ክርስቲያን ሊያንሰላስላቸዉ ይገባል::
ማጠቃለያ
————
እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አቡነ ጴጥሮስ በደም ኦሮሞ ናቸዉ ወይም አይደሉም የሚለዉ ነጥብ አይደለም::የሰዉ የደም ምንጩ አንድ አዳም ነዉ::የሆኖ ሆኖ ጀዋር መሃመድ አቡነ ጴጥሮስን ኦሮሞ ናቸዉ ብሎ ሲናገር አቡነ ጴጥሮስን ከእነ እምነታቸዉ እና ኢትዮጵያዊ የነጻነት እሴታቸዉ ነዉ የተቀበላቸዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ጭብጥ ነዉ::
 ይቆዬን ! እንመለስበታልን !
Filed in: Amharic