>
5:18 pm - Tuesday June 15, 5154

አይ ሰሜን ተራራ እና የኢትዮጵያ ፓርኮች… (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

አይ ሰሜን ተራራ እና የኢትዮጵያ ፓርኮች…

መንገሻ ዘውዱ ተፈራ

የሰሜንን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፤በአፍሪካ በደረጃ የምንታወቅበት፤የራስ ደጀንን መቃጠል፤ለሚሰማ፤እንዴት ተብሎ ሊልና ሊገረም ይችላል። ይታያችሁ አነዚህ በልዩ ሙያ፤በፓርኮች ጥበቃና አንክብካቤ፤ በሰለጠኑ ባለሙያዎች፤ በእውቀት ተመስርተው የተቋቋሙ፤የዓለም ህዝብን፤እፁብ ድንቅ የሚላቸውና፤ ገብታችሁ አትውጡ የሚያሰኙት፤ፓርኮችና ጥብቅ ቦታዎች፤ነበሩ።

ፓርኮችና ጥብቅ ቦታዎች፤ መመራትና መተዳደር ያለባቸው፤በዚሁ ሙያ በሰለጠኑ ባለሙያዎችና፤ያለምንም ልዩነት ሁሉን የአካባቢውን ህብረተሰብ፤በውሳኔ ሰጭነትና፤ጥቅም ተጋሪነት ባሰተፈ ነው።ታዲያ ይህን እውነታ በመጣስ፤ እውቀትን አጥፍቶ በድንቁርና አገር አመራለሁ ብሎ ይዳክር የነበረው የወያኔ መንግሥት፤ ምንም ዝግጅት ሳይኖር፤ፓርኮችና ጥብቅ ቦታዎች በክልሎች መተዳደር አለባቸው ብሎ በ1987ዓ/ም ከመሰረታቸው አናጋቸው።አነ አቶ ተስፋየ ሁንዴሳን የመሰሉ ትልቅ ባለሙያዎቹም፤እረ ተው ይህ አደጋ ነው፤ብለው ቢመክሩ፤ በአደባባይ ሰድቦና አሳዶ፤ ከሐገር አንዲወጡ አደረጋቸው።ጀሮ ለባለቤቱ ባዳ ነውና፤አንጅ፤ሰሜንም ሆነ ሌሎቹ፤የኢትዮጵያ ፓርኮችና፤ ጥብቅ ቦታዎች፤ሆን ተብሎ በወያኔ መንግሥት ተወስኖ፤ከ1987ዓ/ም ጀምሮ እየተቃጠሉና እየጠፉ ነው ያሉት። ይኸው ዛሬ በኢትዮጵ፤አይደለም የድሮ ቁመናቸውንና ይዞታቸው የያዙ፤ሆነው መገኘት፤ፓርክ ነበሩ ብሎ ለመናገር አስከሚያጠራጥሩ? ሁሉም ፓርኮችና፤ጥበቅ ቦታዎች በኢትዮጵያ ምድር የሉም።

እነዚህን ፓርኮች ቀደምት ሁኔታ ለሚያወቅና፤ይህን እውነታና ስሜቱን ለመፃፍ ለሚነሳ፤የሚቀድመው የደም አንባ ነው።አነ አቶ ተሾመ አሸኔ፤አቶ ኪሩቤል ወዘተ፤እንኳን ቀብር መስኮት ኖሮት፤ቀና ብለው አላዩ፤የሚያዩ ቢሆን፤ሞት ደረጃ ቢኖረው፤የመጨረሻውን አሰከፊ ሞት የሚሞቱት ዛሬ ነበር።”ምነው አይኔ ሳላይ በሞትኩ ይላል”ኢትዮጵያዊ፤አንዲህ ያል የሐገር ወድ ሀብት፤ባለቤት አጥቶ እንዳልሆነ ሆኖ ከማየት።

በ1998ዓ/ም የ1987ዓ/ምን ውሳኔ ውጤት ለመገምገም፤በሁሉም ፓርኮች ለመድረስ ተሞክሮ ነበር።በዚህ ጉብኝት፤ከሁሉም የሐገራችን ፓርኮችና፤ጥብቅ ቦታዎች፤”ካሉት” ትንሽ የሚሻሉት የሰሜን ተራሮች በሔራዊ ፓርክና፤የሰንቀሌ ጥብቅ ቦታ ብቻ ነበሩ።

ይኸው፤ሰሜንንም፤በጥናት ተደግፎ የቀረቡ ሃሳቦችን፤ወደ ጎን በመተው፤በእኔ አውቅልሃለሁ፤ከእኔ ወዲያ ላሳር፤ውሳኔና ተግባር፤”ያለ አዋቂ ሳሚ– ይለቀልቃል” አንደሚባለው ያልሆነ ሥራ እየተሰራ፤ለአደጋ ተጋለጦ መቃጠሉን ሰማን።
አሁንም ተተኪዎቹ መስሚያ ጀሮ ካለቸው፤ለሰሜን፤ወደፊት ተሞክሮው ለሌሎቹ የኢትዮጵያ ፓርኮችም ሊያገለግል የሚችል

መፍትሔው፦

• በሐገሪቱ የሚገኙትንም ሆነ ከውጭ ካሉ፤በፓርክ ጥበቃና አንክብካቤ የሰለጠኑትን የጥንት ባለሙያዎችን፤አሰባስቦ፤ የአካባቢውን ማህበረሰብ፤ ያካተተና፤ሌሎችንም አስተዋፅኦ ሊያደርጉ የሚችሉትን ሁሉ በማሰባሰብ፤ እያንዳንዱን ፓርኮች፤ወደ ቀድሞ ቅርፃቸውና ይዞታቸው የሚመለሰ የፓርኮች ጥበቃና አንክብካቤ፤ሰልጠናና ትግበራ አቅድ በማዘጋጀት “ሀ” ብሎ መጀመር።

• በፓርክ ቁጥጥር፤አንክብካቤና፣አስተዳደር፤እና በቱሪዝም ልማትና ስራ አመራር፤መካከል ያለውን፤መስመር የለሽ፤የተምታታ፤የስራና የጥቅም ግጭት፤በጠራ ፖሊሲ፤ህግና፣ደንብ በማበጀት፤ፓርኮች ጽ/ቤት፤ፓርክን የመጠበቅ፤የመንከባከብና የማስተዳደር ሥራ፤ብቻ እንዲሰራ፤የቱሪዝም ልማትና ስራ አመራር፤ጽ/ቤት ደግሞ የቱሪዝሙን ስራዎች ብቻ እንዲሰሩ ማድረግ።

• የቱሪዝም ገቢው፤አንዱን በይ፤ሌላውን ተመልካች ሳያደርግ፤በፓርኮች ውስጥ፤ቱሪስቱ በሚተላለፍባቸው፤ለሚኖረው፤ ለሁሉም ህዝብ ተደራሽ እንዲሆንና፤ሁሉም በየአካባቢው ለፓርኩ ዘብ አንዲቆም ለማስቻል፤ የቱሪዝም ፍሰቱንና መስተንግዶውን፤ከቅብበሎሽ ጀምሮ ሌሎች አማራጮችን በመንደፍ መስራት።

• በተፈጠሮ የተገኘን፤የፓርክን ቅርፅና ይዞታ፤በአለው ተፈጠሮአዊ ሂደትና፤በእራሱ በህዝቡ ፍላጎት ከሚመጣ ፍልሰት ውጭ፤ያለ ህዝብ ፍላጎት በሰፈራ ማስወጣትን ማቆምና፤ከተፈጠሮው ጋር ሳይጋጩ የሚኖሩበትን ሌሎች አማራጮችን ብቻ በማሰብ መስራት ነው። ለምሳሌ፤ በሰሜን ተራሮች የሚገኙት፤የግጭ ኑዋሪዎች፤በተፈጥሮው ላይ ጉዳት በማያደርስ፤ የራሳቸውን ጥግ ይዘው ከተፈጠሮው ጋር ተስማምተው ለብዙ መቶ ምናልባት ሽህ ዓመታት የሚኖሩ ነበሩ።ከተፈጠሮው ጋር ግጭት የፈጠርነው እኛ ተማርን እናወቃለን፤እናውቅልሃለን የምንለው ዜጎቹና፤ እናውቅላችሁአለን በማለት ከውጭ የመጡ ነጮች ነን። ይህም የተፈጠሮ አቀማመጡንና፤የተፈጥሮ ሀብቶቹ፤ሰዎቹን ጨምሮ፤አንዴት ተከባብረውና ተሳስበው፤ አንደሚኖሩ ሳንረዳ፤ ዘለን ገብተን፤የዱር አራዊቶቹን መተላለፊያ መንገድ ዘግተን፤ቤት የሰራንበት፤የቱሪስት ማረፊያና፤የዱር አራዊት ጠባቂ ዘበኞች ቦታ ያደረግነው። ሰፈራ የሚያስፈልግንና፤ማባረር የሚቻል ቢሆን እኛን ነበር ማባረር።

• ግጭ መሐል ላይ ያለውን፤የዱር አራዊት መጠበቂያ ቤቶች፤የቱሪሰት ማረፊያ ቤቶች፤በአስቸኳይ በማፍረስ፤ጅን ባር ወንዝን ተሸግሮ፤ወደ አይና ሜዳ፤አምባራስ መንገድ ሰራተኞች ሰፍረውበት ወደ ነበረው መውሰድ።ከተቻለ ሁሉንም ከፓርኩ ውስጥ የሚገኘ የፓርክ መጠበቂያ ቦታዎችን ከፓርኮቹ መሀል እያወጡ፤ከፓርኩ ዳር ለጥበቃና ቁጥጥር በሚያመቹ በፓርኩ ዙሪያ ማድረግ ።

• ሆን ተብሎ የሰሜንን ብሔራዊ ፓርክ ለማጥፋት፤ከሚሊ ገብሳ ጀምሮ፤የተራራውን አናት፤የዱር አራዊቶቹ፤ከማደሪያቸው ወጥተው፤ወደ ግጦሽና ውሃ ፍለጋ የሚሄዱበትን መተላለፊያ አቋርጦ የሚሄደውን መንገድ በአስቸኳይ መዝጋትና ሀ. ለጃን አሞራና፤በየዳ፣በጎሚያ፣በለስ፣ ደንቆላኮ፣እየተሰራ ያለውን መንገድ፤በአስቸኳይ ማጠናቀቅና በዚያ እንዲጠቀሙ ማድረግ።ለ. ለፓርክ ስራና ለድንገተኛ ጉዳይ፤ለፓርከ መኪና ብቻ የድሮውን፤ከሚሊ ገብሳ፣በሚጭቢ፤ሣንቃበር፤የሚወስደውን መንገድ፤ ጠረግ ጠረግ አድርጎ መጠቀም።

• ከዚሁ እጥፊ መንገድ ጋር ተያይዞ፤በፓርኩ ውስጥ የተተከሉ የኤሌክትሪከ ምሰሶዎችና፤ገመድ፤የመገናኛ መሰመሮችና ግንባታዎች፤የሚፈጥሩት የሌሌት ብርሃን፤ ሁሉ፤የፓርኩን መልካም እይታ የሚበክሉና፤የተመልካቹን እይታ የሚያንሸዋርሩ በመሆናቸው።አብረው ከመንገዱ ጋር አንዲነሱ ማድረግ፤

• በሚቻለው መጠን፤ከደባርቅ ጀምሮ አስከ ራስ ደጀንም ድረስ የነበረው፤የቱሪሰት ጉብኝት ጉዞ፤ወደ ነበረበት በእግርና በፈረስ ላይ እንዲሆንና፤ማስገብኘቱም፤እንደተለመደው በትንሽ ቁጥር ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆን፤ገቢው ለሁሉም የሚደረስበት አዲስ የማስጎብኘትና ሌሌችንም አገልግሎቶች አሰጣጥ ስልት በመንደፍ መስራት። ከብዙዎቹ ወደ ውስጥ ሲገባ ከሚከሰቱት፤ብዙ ሥራዎችና እርምጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው።

 

ፈጣሪ፣አኒያን ውብ አፁብ ደንቅና እለባብ አልባብ ይሸቱ፤የነበሪ የተፈጠሮ ፀጋዎቻችን ወደ ነበሩበት ይመልስልን።

ኢትዮጵያ በከብር ለዘላለዓለም ትኑር

Filed in: Amharic