>
5:18 pm - Monday June 16, 7580

እስክንድር ነጋ ለሶስተኛ ጊዜ የታገደበት  መግለጫ በደህንነት ትዕዛዝ መሆኑ ታውቋል!!!

እስክንድር ነጋ ለሶስተኛ ጊዜ የታገደበት  መግለጫ በደህንነት ትዕዛዝ መሆኑ ታውቋል!!!
* በዛሬው ዕለት የሰናይ መልቲ ሚዲያ ምስረታና የአክሲዮን ሽያጭ፤ ይፋዊ መግለጫ መንግስታዊ አፈና በድጋሚ ተካሂዶበታል!!!
* ” ከደህንነት ተደውሎ ስለተነገረን አሁን መግለጫ መስጠት አትችሉም “
 
በድጋሚ ለሁልም ሚዲያ የተላለፈ ጥሪ “
“አፈር ልሰንም ቢሆን የህዝብ ሚዲያ እንቋቁማለን!!!
እስክንድር ነጋ”
///
አዲስ የሳተላይት ቴሊቪዥን ጣቢያ ምስረታ ጋዜጣዊ መግለጫ
ቦታ ፦ አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል
ቀን፦ አርብ ግንቦት 30/2011 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
ሰናይ መልቲ ሚዲያ ፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ ፣ እንዲሁም እየታሰሩ እየተፈቱ ለህዝብ መሰዋዕትነት ሲከፍሉ በኖሩ አንጋፋ እና ወጣት የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች አስተባባሪነት (ፕሮሞተርነት) የ24 ሰዓት ቲቪ ለመክፈት ህጋዊ የሆኑ ሂደቱ ተጠናቋል ።
ትላንትና ፣ዛሬ እና ነገን እንደ-ድልድይ የሚያስተሳስር ፣ መረጃ ፣ ቁምነገር እና መዝናኛ ፕሮግራሞችን በላቀ ሁኔታ የሚያቀርብ ቲቪ፤ ህዝብ እንዴት የራሱ ማድረግ እንዳለበት በተመለከተ በሂልተን ሆቴል
ጋዜጣዊ መግለጫ ይስጣል።
ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁሉም የሚዲያ ተቋማት ክፍት ነው !
ለበለጠ መረጃ
በዚህ መልኩ የተዘጋጀ መጥሪያ የደረሳቸው ጋዜጠኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰአቱ ስፍራው ቢደርሱም የጠበቃቸው አሳፋሪ መንግስታዊ የመብት ጥሰት ነበር።
    ለአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በቀን 27/ግንቦት/2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፤ “ጌት አማካሪዎች” የንግድና ኢንቨስትመንት ማማከር ድርጅት፤ የሰናይ ቲቪ ምስረታ እና አክሲዮን ድርሻ ሽያጭን በተመለከተ ፤ለግንቦት 30/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት ለሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ የአዳራሽ ኪራይ የተጠየቀ ሲሆን ፤
      ሂልተን ሆቴል በደብዳቤ ለቀረበለት ጥያቄ ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም አወንታዊ ምላሽ በደብዳቤ በመግለጽ፣ ክፍያ እንዲፈጸም በጠየቀው መሰረት በዚው ዕለት 12995 ብር (አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አምስት ብር ) ክፍያ ተፈጽሟል ።
    ይሁን እንጂ በተገባው ህጋዊ ውል መሰረት፣ በዛሬው ዕለት ጥሪ የተደረገላቸው ጋዜጠኞች እና ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የተገኙ የሰናይ መልቲ ሚዲያ መስራቾች ፣በቦታው ቢገኙም የተሳበው መግለጫ መስጠት አልተቻለም ።
        ይህን ጉዳይ በተመለከተ የሆቴሉ የሽያጭ ክፍል እረዳት ስራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ሰርጸወልድ ” ከሚመለከተው ክፍል ፍቃድ ካላመጡ መግለጫ እንዳይሰጡ” በማለት ከደህንነት ተደውሎ ስለተነገረን አሁን መግለጫ መስጠት አትችሉም ብሏል ። ለእኚህ ስራ አስኪያጅ የሰናይ መልቲ ሚዲያ መስራቾች “የሚመለከተው” አካል ማነው ?ይህን ማድረግ ከእኛ አይጠበቅም !ዝግጅታችን አጠናቀናል፣ ህጋዊ ውል ፈጽመናል ፣ መግለጫ እንድንሰጥ ወደ አዳራሹ እንድንገባ በሩ ይከፈትልን ፤ በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፤ አቶ አንተነህ የሆቴሉን ጥበቃዎችን በመጥራት የአዳራሹ በር በማዘጋት ፣” ይሄ ከእኔ አቅም በላይ ስለሆነ ፤ ጊቢውን ለቃችሁ ውጡልኝ ” ብለዋል ።
      የሰናይ መልቲ ሚዲያ መስራቾች ይህ’ን መንግስታዊ የሚዲያ አፈና ፣እዛው በመረጃና በማስረጃ በሆቴሉ ቅጥር ግቢ ለተገኙ የሚዲያ ተቋማት በመግለጽ ፣ ግቢውን ለቀው ወጥተዋል ።
     ከላይ ለተዘረዘሩት የውል ስምምነት ማስረጃ ከዚህ ጽሁፍ ጋር ተያይዟል ፣እኔ’ም በቦታው ስለነበርኩ እማኝነቴን እገልፃለው።
ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ !!!
Filed in: Amharic