>
5:18 pm - Sunday June 16, 8537

የብድር ነገር!!! (ቅዱስ ማህሉ)

የብድር ነገር!!!
ቅዱስ ማህሉ
ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር እዳ ያለበት ሃገር 40ቢሊዮን ብር አውጥታ ችግኝ መትከሏን የሚናገሩ ደፋር እና ነውር የማይፈሩ ባለስልጣናት የነገሱባት ሃገር ናት። 
* ከ 50 ሀገሮች ይህን ያህል እዳ ያለባት አገር የሚመሩት ሰዎች ለወንዝ ዳር ፕሮጀክት እና ከተማ ማስዋቢያ 30ቢሊዮን ብር በጀት የሚመድቡ የምኞት ባሪያዎች ሆነው እየታዩ ነው!!!
—-
ንብረትነቱ የታንዛኒያ መንግስት የሆነው የታንዛንያ አየርመንገድ አውሮፕላን በደቡብ አፍሪካ ተይዞ እንደነበር ታውቋል። ይሄው አውሮፕላን ኤርባስ 220-300  አርብ ዕለት ከጆሃንስበርግ ወደ ዳሬሰላም በረራ ለማድረግ በተዘጋጀበት ወቅት የደቡብ አፍሪካ የጸጥታ ሃይሎች አውሮፕላኑ እንዳይንቀሳቀስ ማድረጋቸው ታውቋል። ምክንያቱ ደግሞ የታንዛኒያ መንግስት ከአንድ ደቡብ አፍሪካዊ ገበሬ ላይ መሬት ነጥቆ ተገቢውን ካሳ ባላመክፈሉ ምክንያት የተከሰተ ነበር። የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ለገበሬው የታንዛኒያ መንግስት 33ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ቢፈርድበትም እምቢ ብሎ በመቆየቱ ፍርድቤቱ ባለዕዳው የታንዛኒያ መንግስት ንብረት የሆነው አውሮፕላን እንዲያዝ ወስኗል። የታንዛኒያ መንግስት የተያዘበትን አውሮፕላን አስመልክቶ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለመመካከር ቃል አቀባዩን ወደ ደቡብ አፍሪካ መላኩን ገልጿል። እዳ ተገኘ ተብሎ ዝም ብሎ እጅ መስደድ መዘዝ ያመጣል። ከሶስት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ዕዳ ጫና መፍትሄ ካልተገኘለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ባለእዳዎቹ በያረፉበት እየያዙ ሊወስዷቸው ይችላሉ። ከዚህ በፊት የአርጀንቲና አበዳሪዎች በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የአርጀንቲና መንግስት ከሰው የአርጀንቲናን መንግስት ንብረት እየይዙ ያበደሩትን ገንዘብ እየሽጡ እንዲወስዱ በፈረደላቸው መሰረት ይህንኑ አድርገዋል። የአርጀቲና መንግስት የንግድ መርከብ ምዕራብ አፍሪካ ጋና ይዘው የመርከቡን ሰራተኞች እና ጭነት አራግፈው መርከቡን ወስደዋል። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ውሳኔን የጋና መንግስት አስፈጽሟል። የአርጀንቲና አውሮፕላን በርሊን እንዳረፈም የፍርድ ቤት ውሳኔያቸውን ለጀርመን መንግስት አቅርበው አውሮፕላኑ በቁጥጥር ስር እኒውል ማድረግ ችለው ነበር። ይሁን እንጅ አውሮፕላኑ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት መንቀሳቀሻ የነበረ በመሆኑ እና በቬና ስምምነት መሰረት ፕሬዝዳንቱ ባለው የዲፕሎማቲክ መብት አውሮፕላኑ ለጥቂት ከአበዳሪዎቹ እጅ ማምለጥ ችሏል።
አርጀንቲናን ያቃወሳት የኢኮኖሚ ስርዓቷ በምኞት ላይ የቆመ መሆኑ እና ያንንም በብድር ገንዘብ ለማስፈጸም መሞከሯ ነበር። የኢትዮጵያን ብናየው ፕሮጀክቶቹ ከምኞትም በላይ ተምኔታዊ ናቸው። ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር እዳ ያለበት ሃገር 40ቢሊዮን ብር አውጥታ ችግኝ መትከሏን የሚናገሩ ደፋር እና ነውር የማይፈሩ ባለስልጣናት የነገሱባት ሃገር ናት። ይህን ያህል እዳ ያለባትን ኢትዮጵያ የሚመሩት ሰዎች ለወንዝ ዳር ፕሮጀክት እና ከተማ ማስወቢያ 30ቢሊዮን ብር በጀት የሚመድቡ የምኞት ባሪያዎች ሆነው እየታዩ የሃገሪቱን እዳ ያቃልላሉ ማለት እንዴት ይቻላል? አርጀንቲናን በኢኮኖሚ ቀውስ  ብቻ መቋቋም ያቃታትን የእዳ ጫና ኢትዮጵያ ከዚያም በላይ ስርዓት አልበኝነት ነግሶባት እንዴት ልትወጣው ትችላለች? ይህን በምጽፍ ሰዓት እንኳ ኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ ብድር ማግኘቷ ገና ትኩስ ዜና ነው። ይህ እንግዲህ ካልተከፈለው 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር እዳ ላይ የተጨመረ አዲስ ብድር ነው። ይህ ያለው ትውልድ እና የልጅ ልጁ የሚከፍለው እዳ! ብድር በመጭው ትውልድ መቀለድ ነው።
Filed in: Amharic