>
5:18 pm - Monday June 15, 1401

ይድረስ ለአማራ ክልል ህዝብ፤ (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

ይድረስ ለአማራ ክልል ህዝብ፤

ከመንገሻ ዘውዱ ተፈራ
ልክ ነው አዴፖ ምን ለውጥ አመጣ ብለን አንድ እጣት ቀስረን ስንጠይቅ፤ወደ እኛ ለተቀሰሩት  ሦስት እጣቶች፤ አንተ ምን ሰራህ? ምን እየሰራህ ነው? ምንስ ለመስራት አቀድክ? መልስ ሰጥተን ከተነሳን ጥያቄአችን ትክክል ይሆናል። በዚህ አስተሳስብም አሁንም አማራን ጠብቀን ከኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር የሚገባውን እያገኘ እንደጥንቱ እንዲኖር ማድረግ እንችላለን። ነገር ግን ይህን መሰረት ባላደረገ አዴፓን መጥላቱ ግን ለችግር እንዳያጋልጠን፤ከእነ አሰስ ገሰሱም ቢሆን ለጊዜው እውቅና ያለው፤ በሐገሪቱ ሐብት ለመስራት መብት ያለውን ድርጅት እያጠናከሩ መስራት የግድ ነው። ይህም የሚሆንበት የተሻለ ስለለ እና አዲስም በመፍጠር ጊዜ ማጥፋት ስለማይገባን ነው።
እውነት እነዚህ ለአማራ ህዝብ ቁሙናል የሚሉ ድርጅቶች ሁሉ በስተጀርባ የተቋጠረ የግል ፍላጎት ምሳሌ ስልጣን ጥመኝነት ከሌላቸው፤ ለህዝብ ለሐገር የሚያስቡ ከሆነ፤ከአዴፖም ሆነ ከሌሎቹ ውስጥ ያሉ ሁላችንም የአማራ ክልል ህዝቦች ነን፤ ከዚያ ዝቅ ሲባል ደግሞ የደምና አጥንት ዝምድናም ይገኘናል ታዲያ ለመነጋገር ለምን ተቸገርን?
ስለዚህ የሚሻለው የስው፤የቁስ፣የአስተሳሰብ ሀብትን፤በእየፊናው እየተቧደን ከምናባክንና፤ ኃይላችን ከምናሳሳ፤ ለምንድን ነው ቢያንስ ተሰባስበን በአማራና ኢትዮጵያዊ አንድነታችን አብሮ በመስራት ለውጤት ለመብቃት ማሰብ የሚሳነን? አውሬ እንስሳን ለመብላት የመጀመሪያው እርምጃው፤ መበታተን ነው። ይህ ብትትንም ነው፤ ግማሹ ተራው እስኪደርስ ባደባባይ አ ድንፉታ፤ የተወሰኑት እስር ቤት፤የተወሰኑትም በለለ ጫካ ዱር ቤቴ ብለው፤ግንባሩን እያሳሳን አማራን ወደ ተጠቂ አጣብቂኝ ውስጥ እየከተትነው ያለን።
እባካችሁ በ2012 ዓ/ም ከዚህ መበታተንና የተበታተነ ትግል እንውጣ፤ነገሮችን ስናይና ስንመዝን፤ከአካባቢያዊ፣ክልላዊ፣ሐገራዊና፣ዓለም አቀፋዊ እውነቶችና፤አስገዳጅ ሁኔታዎች ለማየት እንሞክር።ወደድንም ጠላንም፤የውጭ ኃይሎች እጃቸው እንዳለበትና፤ከእነሱ ዘመናዊ ግዞት ውጭ እንዳልሆንም እንወቅ። ከዚህ አንፃር ሰሞኑን የአሜሪካ መንግስት እንኳን ፊቱን አዙሮ ሲመጣ፤ ቅድሚያ ለመምጣት፤ፈቃዱን የሚያገኘው፤መጥቶ ቅድሚያ የሚያገኘው፤በህግ የተቋቋመውን የክልል መንግስት ነው።ይህ ማለት ደግሞ አዴፖ ነው። ይህ ምን ያሳየናል ምንም ቢሆን “የጤፍ ቅንጣት ታህል ስልጣን የጤፍ ቅንጣት ታህል ታደቃለች” አባባልን ነው። ስለዚህ ከዚች የጤፍ ቅንጣት ታህል ድቀት ሳንወድቅ “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” አባባልን ተጠቅመን፤ አሁን አዴፖን እያጠናከርን ሰፊውን የአማራ ክልል ህዝብ ሰላም ደህንነት ቀጣይነት እናረጋግጥ፤ከዚያ ውስጣዊ ችግሮቻችን ማስተካከልና ማረም እንችላለን። ከዚህ ውጭ መቆሚያችን ተረጋግቶ ሳይቆም ብንቆምበት ውጤቱ ውድቀት ስለሚሆን፤ይህ አመት መወነጃጀልን ወደጎን ትተን፤እንድንሰማማ እንድንወያይና እንቅስቃሴአችን በብስለት ላይ እንዲመስረት ሁላችንም ሰላም እናስብ።
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን መልካም አዲስ አመት።
ፈጣሪ የአማራ ክልልን ኢትዮጵያን ከነልጆቿ ይባርክ ይጠብቅ።
Filed in: Amharic