>

የጋራ ታሪክ አለን ወይስ የለንም? (መምህር ታዬ ቦጋለ)

የጋራ ታሪክ አለን ወይስ የለንም?
መምህር ታዬ ቦጋለ
በርግጥ ሀሳቡ ለአቅመ ውይይት የሚያበቃ አይደለም። የጋራ ታሪካችን ዘመናት የተሻገረ መሆኑን ለማወቅም ምርምርና ፍልስፍና አይጠይቅም። የታሪክ መፃሕፍትን ወተት በቡና እየጠጡ ቂጣ በማላመጥ ብቻ ገፆቻቸውን እንደዋዛ በመግለጥ ይደረስበታል። ቁም ነገሩ የጋራ ታሪካችንን የመተንተን ጉዳይ ሳይሆን፦
“ሂትለር ከዋሸህ አይቀር ሰዎችን ለማሳሳት የሚያስችል ጠብደል ውሸት እንጂ – ቁጥቁጥ ቅጥፈቶች ብዙም አያስኬድም” – ብሏል።
መረዳት ያለብን የጃዋርን መነሻና ዋነኛ ዓላማዎች ነው።
የጃዋር የመጀመሪያ ቁልፍ ተግባር  የሚያስተሳስሩንን ዋና ዋና አምዶች ዒላማ እያደረገ ማፈራረስና ኢትዮጵያን ለመበተን አበክሮ መሥራት ነው።
ዘመቻ አንድ፦ ከሰማንያ በላይ ቋንቋ የሚናገሩ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰቦች እንዳይግባቡ አማርኛ ላይ መዝመት።
ዘመቻ ሁለት፦ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደ ጋራ ታሪክ መተሳሰሪያ ብትወሰድ ጥንት በ14ኛው ክፍለ ዘመን የወላይታ ማላ መሪ – ሞቶሎሚ ተቀብሎ ያደመቃት፤ ከ15ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ በወላይታና ደቡብ ግዛት ውስጥ የወላይታ ማላን ስርወ መንግሥት ተክቶ የዘለቀው የትግሬ ሥርወ መንግሥት የክርስትና ታሪክ መተሳሰሪያ መሆኑን ጃዋር ተምሮ ይሁን አይሁን እርግጠኛ አይደለሁም።
ከ1434-68 ባለው ጊዜ ኢትዮጵያን የመራው ንጉሥ  ዘርዓያዕቆብ ሚስት የሀዲያው መሪ ልጅ – ክርስቲያኗ እሌኒን በቅጡ ይወቃት አይወቃት አላውቅም።
በዛግዌ ሥርወ መንግሥት ዘመን አዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን መታነጿን ይማር አይማር አላውቅም። (ጃዋርንና ህዝቅኤልንም ያስተማረው የታሪክ መምህር ህንዳዊ ይሁን ጀርመናዊ ማጣራት ያስፈልጋል።-
በኢማም አህመድ ኢብራሂም (ግራኝ አህመድ) ዘመን (1527-43) ዝዋይ ደሴት ላይ ጽላቶቻችን መደበቃቸውን ይወቅ አይወቅ – ፈጣሪ ይወቀው።
(የሀይማኖት ታሪክ – የታሪክ አካል አይሆን ይሆን?)
በአፄ ኢዛና ዘመነ መንግሥት (330-360) አዲስ አበባ የረር ላይ ቤተ ክርስቲያን መተከሉን አያውቅ ይሆን?
*
ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ያስተሳሰረን እስልምና በሰሜን ከአልነጃሺ ጀምሮ በደቡብ እና ምስራቅ በዘይላና በርበራ በኩል የገባው እስልምና፣ በ9ኛው ክፍለ ዘመን ሸዋ ላይ የተቋቋመው የሸዋ ሱልጣን (ማክዙማይት ስርወ መንግሥት)፣ በ1285 ሸዋን አሸንፎ ሥልጣን የያዘው የኢፋት ሱልጣናዊ አስተዳደር (የወላዝማ ስርወ መንግሥት) የሚያስተሳስረን የታሪካችን አካል መሆኑን – አያቶላህ ጃዋር የነገራቸው አይኖር ይሆን?!
አምደ ጽዮን ከ1314-44 በምስራቅ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው ሶማሊያ ውስጥ ዘይላና በርበራ ድረስ፤ በስተሰሜን ኤርትራ ቀይ ባህር ድረስ ማስተሳሰራቸውን አልሰሙ ይሆን?
*
በኦሮሞ እንቅስቃሴ ወቅት ከደቡብ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ደቡብ ትግራይ መደረሱንስ?!
የየጁ ኦሮሞዎች በዘመነ መሳፍንት 1769-1855 ድረስ ከአሊ ጓንጉል እስከ አሊ አሉላ (1853) የጎንደር ቤተ መንግሥትን – በንጉሥ አንጋሽ ራስ ቢትወደድነት መምራታቸውንስ?
*
ከዛሬ 6,000 ዘመን ጀምሮ ጤፍ ዳጉሳ ኑግና እንሰት – እንዲሁም የዘመናት የረጂም ርቀት ንግድ  መላውን ኢትዮጵያውያን እንደገመደንስ አያቶላህ ጃዋር አያውቁት ይሆን?! የህዝቅኤልና የጃዋር ታሪክ መምህር ማን ነበር?!
*
የኩሽ አገው ስርወ መንግሥት (1150-1270) ድረስ ሸዋን ጎጃምን አክሱምንና ላሊበላን በተለያዩ ግዛቶች ከፋፍሎ ማስተዳደሩንስ?! (ማነህ እንቶኔ – ለጃዋር መራራ እውነት በኢትዮጵያ ታሪክ የሚለውን መፅሐፍ ገዝተህ ስጠውና ስለ ሸዋ የማቅለጫ ገንዳነት ያስብ!
*
እኚህን የትግራዩን የጋሞ  መነኩሴ አባ ባህረ / ባህረይን ንክስ አድርጎ የያዛቸው በ16ኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞን ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ፃፉ ብሎ አይደለምን?! ከዛሬ 500 ዓመታት በፊት። የጋራ ታሪክ ማለት የመተቃቀፍ ብቻ በመሳሳም የመጣ አለመሆኑን – እዚያው ዜግነቱ ያለበት ሀገር ሚኒሶታ ጠቅላይ ግዛት ቢጠይቅ – ሰሜን አሜሪካ ውስጥ በደቡቡ 11 ግዛቶችና በሰሜኑ 22 ግዛቶች መሀከል (1861-65) በተደረገ ውጊያ 620,000 ሰው ማለቁን ይነግሩት ነበር። ዳሩ መኖርና ማኗኗር ብቻ ሳይሆን – እየኖሩ አለመኖር የሰከብዳል።
*
ዘመቻ ሦስት – ታሪክን ማጥፋት
(የአማርኛ ቋንቋ፣ የተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የጋራ ታሪክ) – እንዲህ እንዲያ እያለ – የሚያስተሳስሩንን አምዶች መገዝገዝ የጃዋር አደገኛ አካሄድ ነው።
*
እዚህ ላይ “ጃዋር አጀንዳ ሲሰጣችሁ ምላሽ አትስጡ” በሚል የአዋቂ የሚመስል አጥፊ ምክር የተጠመዱ = ከጃዋር እኩል ጎጂ ሰዎች ዕያየሁ ነው። እንኳን በዘላቂ የሀገር ጉዳይ ይቅርና የምርጫ ዘመቻ ሲመጣ በሁለት አቅጣጫ ሙግት የሚደረገው – የተቃራኒህን ሀሳብ ለማፍረስ ነው። ጃዋር ትውልዱን ጥላቻ  ይጋት ማለት  አይጠቅምም። (ዓለም የምትጠፋው ከእኩያን መጥፎ ድርጊት ይልቅ በመልካሞች ዝምታ ነው – የሚለውን ወርቃማ አባባል መሳት ይቅርታ አያሰጥም።)
ጃዋር አጀንዳ እያቀበለ ነው – አዎ። የወረወረውን ሚሳኤል መልሰህ በፀረ ሚሳይል ካልመታኸው ግን እንከፉ አንተ እንጂ እሱ አይደለም። (Counter propaganda / አፀፋዊ የመልስ ምት – የፖለቲካ ሀሁ እንጂ አቡጊዳ እንኳ አይደለም።)
*
አጉል አትላላጡ። ባትፅፉ እንኳ የሚፅፉትን አታዳክሙ!
*
ጃዋር በአባቱ የመኒ፣ በእናቱ አማራ ሲሆን – የአርሲ ኦሮሞ በጉዲፈቻ ስላሳደገው ኢትዮጵያዊ ነው። ተስፋዬ ገብረእባብስ ኤርትራዊ ሆኖ ሳለ – በነጃዋር ጉባኤ ገዳ ገብረአብ ተብሎ የለ። ስናጠቃልል የጃዋር እቅድ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው። የሚፈርሰውን  የኢትዮጵያ አምላክ ያሳየናል።
Filed in: Amharic