ሀብታሙ አያሌው
በፍቅሩ ጥላ ሥር ቆመናልና ፈጣሪያችን ሊያጠፉን በተማማሉ በታኞቻችን አይተወንም!!!
—
ዛሬ ጎህ ሲቀድ ጀምሮ በባሕር ዳር፣ ቢቸና፣ ቡሬ፣ እንጅባራ፣ መርዓዊ፣ ወልድያ፣ ፍኖተ ሠላም፣ ደባርቅ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ቆቦ፣ ማጀቴ፣ ጫጫ፣ ውጫሌና፣ ላልይበላ በእጅጉ አስገራሚ ትዕይንተ ተካሄደ።
በተጠቀሱት ከተሞች በምዕመናን እና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በሰልፉ ላይ ከታዩት መልእክቶች፦
* “በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም!
* በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ!
* ቤተክርስቲያን አትከፋፈልም !
* የህዝበ ክርስቲያኑን ድምፅ ያፈኑ ሚዲያዎች ይቅርታ ይጠይቁ !
* ከጥላቻ እንደማላተርፍ አውቃለሁ፡፡ አትንኩኝ! አልነካችሁም ነው የምለው፡፡


* በፍቅሩ ጥላ ሥር ቆመናልና ፈጣሪያችን ሊያጠፉን በተማማሉ በታኞቻችን መዳፍ ውስጥ እስከወዲያኛው አይተወንም፡፡ …
* ከእንግዲህ ከዚህ የተሻለም፣ ይበልጣል የሚባልም ምርጫ የለኝም፡፡
* የሚጠሉኝን አልጠላም፡፡ ይልቁኑ ቢራቡ ላጎርሳቸው፣ ቢጠሙ ላጠጣቸው፣ ቢታረዙ ላለብሳቸው በተግባር ዝግጁ ነኝ፡፡
* የማልፈቅደው ማተቤን! ኢትዮጵያዊነቴን! እንዳይነኩና ዝቅ አርገው እንዳይመለከቱ ብቻ ፡፡
———–///———–
…የሚሉ ናቸው፡፡
ይህንን በፍፁም ክርስቲያናዊ ስነምግባር እየቀረበ ያለ የመብት ጥያቄ ለመደገፍ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በማለዳ ወጥቶ እጅ ለእጅ ተያይዞ አጋርነቱን አሳይቷል።
ይህ እንዳይሆን የታሪክ ሰበዝ እየመዘዙ ግጭት ለመፍጠር ሲታትሩ የነበሩ አካላት በህዝቡ እንቢተኝነትና በጋራ መቆም ውጥናቸው ሲከሽፍ በይፋ ከተገለጠው ንዴታቸው ባሻገር የተለያየ አጀንዳ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው።

#ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው !!