>
5:13 pm - Tuesday April 19, 0659

" ስለሽመልስ አብዲሳ በሰጠሁት አስተያየት አሳስተህናል ለምትሉ ወገኖቼ ትልቅ ይቅርታ " (ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)

ግልፅ ደብዳቤ ለአቶ ሽመልሽ አብዲሳ፤
 
  ” ስለሽመልስ አብዲሳ በሰጠሁት አስተያየት አሳስተህናል ለምትሉ ወገኖቼ ትልቅ ይቅርታ “
ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
የተወሰንን ግለሰቦች ኦሮአማራ እያልን ስንጮህ ሕውሃት እና የኦነግ አጋሮች ሲሰድቡን ከረሙ፡፡ የእነርሱ መንጫጫት እንብዛም አሳስቦን አያውቅም ነበረ፡፡
አሁን ደግሞ በሚያስደነግጥ እና በሚያሳፍር ትችት እና ዲስኮርስ የአማራን እና የኦሮሞን ግንኙነት ለማክሰም ሞከርክ፡፡ ሆኖም ግን ለብዙ ዘመናት በአብሮነት የኖሩት ህዝቦች፤ በፓርቲና በግለሰቦች ፈቃድ ቀድሞውንም ያልተመሰረተ በመሆኑ ሊፈርስ አይችልም፡፡
እንደዚህ አይነት ሕውሃታዊ፤ኦነጋዊ እና አክራራዊ ገለፃ አንተ ይዘህ በመቅረብህ እኔ ብቻ ሳልሆን፤ ስትሾም “እንኳን ደስ ያለህ” ብለው መልዕክት የላኩልህ የፍልስፍና አሰተማሪዎችህም በእጅጉ አዝነውብሃል፡፡
አማራ ተባለ ነፍጠኛ በታሪኩ ለማንም ተንበርክኮ አያውቅም፤ ይህንን እውነታ እንኳንስ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ያለ ሕዝብ ይቅርና፤ ቱርኮችም፣ ግብፃችም፣እንዲሁም ጣሊያኖችም ጠንቅቀው ያውቀሉ፡፡
ልጅ ሽመልስ እንደአስተማሪህ ያለኝ ምክር፡- በንግግርህ ላስቀየምከው ህዝብ ትልቅ ይቅርታ በይፋ ወጥተህ መጠየቅ ይኖርብሀል፡፡ በተጨማሪም ራስህን ሁን፣ ለሙገሳ እና የግለሰቦችን ቅቡልነት ለማግኘት ስትል ሌላውን ሰው ለመሆን አትሞክር፤ በተቻለህም መጠን የአክራራዊነት መንፈስ ከራስህ ላይ አርቅ፤ መጠቀሚያም አትሁን፡፡
በመጨረሻም፤
ስለሽመልስ አብዲሳ በሰጠሁት አስተያየት አሳስተህናል ለምትሉ ውገኖቼ ትልቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ለነገሩ የተከሉት ዛፍ ቀጥ ብሎ ይወጣል ሲሉ ከፍ ሲል ሊጎብጥ ይችላል እና እንዲሉ፡፡
Filed in: Amharic