>
7:47 am - Sunday November 27, 2022

"ለዚህ ሁሉ አንድና - አንድ ተጠያቂው የሀገሪቱ መሪ ብቻ ነው፡፡″ (አርቲስት አስቴር በዳኔ) 

“ለዚህ ሁሉ አንድና አንድ ተጠያቂው የሀገሪቱ መሪ ብቻ ነው፡፡″

“አዲስ አበቤዎች እየኖርን ያለነው በከፍተኛ ስጋት ነው!” 

አርቲስት አስቴር በዳኔ 
=>.የምኖረው ጀሞ ነው፤ መሬት በወረራ ሆኖል ወራሪው ደግሞ እራሱን ቄሮ ብሎ የሰየመው ቡድን ነው ሀገሬ ላይ ያለሁ አልመሰለኝም፡፡
=>ከየትም የመጡ ወጣቶች ችካል ይዘው እየተከፋፈሉ ነው ፖሊስም አላስቆማቸውም አንዱን የራስ ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ ማድረግ ፈፅሞ የተሳሳተ መንገድ ነው።
=>ጁሀር   ለምምንድን ነው ሰውን እንደጋማ ከብት የሚቆጥረው፡፡
=>ጁሀር ሳይሆን ተጠያቂው ጠሚው ነው፡፡
=>ጠሚው ግራ ገብቶት ከሆነ ይንገረን ሀገሪቷን እያወዛገባት ነው
=>ሞት እንደው አይቀርም ሀገርን ግን እናድን መፍራት ከመጣብን አደጋ አያድንም።
=>እንጂነር ታከለ ዑማን ሰው ለምን ይጠለዋል እል ነበር በአጋጣሚ የሆነ ፌስቲ በዓል ሆኖ መዘጋጃ ቤት ሄድኩኝ በአማረኛና ኦሮሞኛ ነው ፕሮግራሙ የመጀመሬያው አማረኛ ዘፈን ተከፈተ በአርምሞ ታለፈ ፤ ሁለተኛው ላይ ኦሮምኛ ተከፈተ መሬቱን አነቃነቁት ፤ ቀጥሎ ትግረኛ ከዚያም ወጣቱ ግልብጥ ብሎ ወጣ ደነገጥን “ለምን?” ብለን ስንጠይቅ የአዲስ አበባ ልጅ እኮ የለም ከአዲስ አበባ ውጭ የመጡ ናቸው አሁን ቄሮ የሚባሉት ናቸው የሚል ምላሽ አገኘን። ታዲያ የአዲስ አበባ ልጅ እንዴት  ይውደደው?!?
=>ጠሚው የኖቤል ሽልማት ተሸለመ ተብሎ ስንደሰት አዲስ አበባ ተወረረች አዲስ አበባ ለአዲስ አበቤ ነች ብሎ እስክንድር ሰልፍ ሲጠራ የአዲስ አበባን ልጅ ማሰር ምን ማለት ነው?
መንገድ መዝጋት ከየት የመጣ ነው ፤ ሀገር ማተራመስ ምን ይባላል?
=>ጠሚው የኦሮሞ ብቻ ነው እንዴ በኦሮሚያ ብቻ ሰልፍ የተካሄደው? አሳፋሪ ተግባር ።
=በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ኩራት በሆነችው ባንዲራ አልደራደርም!  የግብፅ ባንዲራ አዲስ አበባን ወሯት ነው የሰነበተው ኧረ አሁንም አልተነሳም ከቤተል አደባባይ እስከ ቤተል መጨረሻ ለአንድ ቀን ተብሎ የአዲስ አበባ ህዝብ ሶስት ቀን መንገድ ተዘግቶ መውጫ ቀዳዳ አቶ ሰነበተ ከዚህ ውጭ ወረራ አለ እንዴ?
=>እስከ ቤት ቁጥሬ ድረስ ያውቁታል ዛቻቸው ልነገራችሁ ዓልችልም ግን አልፈራም። አባቶቼ ቢፈሩ ኖሮ አሁን የአለንባትን ሀገር አናገኛትም ነበር። እኔም አልፈራም በመፍራት ሀገር ማስቀጠል አይቻልም። ከዚህ እንተርቪው በኀላ ያለው ዛቻ ደግሞ አያድርስ ነው እኔ ግን አልፈራም፡፡ ሞትም አይቀርም?
=>እኔ ኦሮሞ ነኝ አሁን ያለው አካሄድ አይዋጥልኝም መታረም አለበት። አንዱን የራስ ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ ሆኖል ነገሩ ግን አያዋጣም ወያኔም ተኮታኩቶ ወርቋል።በአዲስ አበባና በኢትዮጲዊነቴ ለአፍታም አልደራደርም ።
=><ተጠያቂው ግን ማንም በማንም ላይ ማሳበብ አይቻልም ተጠያቂው ጠሚውና(ጠሚው ብቻ ነው ጁሀር ሜዳው ነው የተሰጠው። ሜዳ የተሰጠው ሰው ደግሞ እንደፈለገ መፈርጠጥ ይችላል።ምክንያቱም ተፈቅዶለታል ። ለዚህ ሁሉ አንድና አንድ ተጠያቂው የሀገሪቱ መሪ ብቻ ነው፡፡
Filed in: Amharic