>
5:13 pm - Tuesday April 19, 9340

ግርማዊነታቸው በአለም አቀፍ ሚድያዎች እይታ!!! (መሳይ መላኩ)

ግርማዊነታቸው በአለም አቀፍ ሚድያዎች እይታ!!!

መሳይ መላኩ
እጅግ ታላቅ አክብሮት የሚገባቸው የኢትዮጵያዊያን ንጉሠ_ነገሥትና የይሁዳው ንጉስ ኃይለሥላሴ በዛሬው ዘመን ታሪክ ውስጥ ልዩ ሥፍራን የያዙ ንጉስ ናቸው። ኃይለኛውን የኢምፔሪያሊዝም ወረራ በመቃወም……ስለትናንሽ ሀገሮች መብትና ነፃነት እጅግ በሚደንቅ ሁኔታ ቃሉን ያሰማ ወይም የሀገሩን ክብርና ፍፁም ነፃነቱን ለመጠበቅ ሲል በታላቅ ቆራጥነት ሊጋጠሙት የማይቻል ችግርን የተቋቋመ ከእርሳቸው የበለጠ አንዳችም ሌላ ሰው አይገኝም!!”
(ካሃን ኢንተርናሸናል እ,ኤ,አ መስከረም 14/1966)
~
………* “በሀገራቸው በጣም በለዘበ አኳኋን በሌላውም የአፍሪካ ሀገር ውስጥ ባልከረረ ሁኔታ የሚናገሩት ወቃሾቻቸው እንኳን……የይሁዳው አንበሳ ኢትዮጵያን ከወረራ በማዳንና በጣም ወደኋላ ቀርቶ የነበረውን ሕዝባቸውን ወደ 20ኛው ክፍለዘመን በማድረስ እጅግ መልካም የሰሩ መሆናቸውን ይስማሙበታል!!”
(ሎስ አንጀለስ ታይምስ እ,ኤ,አ ሐምሌ 11/1965)
~
………* “የሎስ አንጀለሱ ፕሮፌሰር ሴስሎ ንጉሠ_ነገሥቱንሲያስተዋውቁ…”የትምህርት_ምሳሌ”
ሲሉ ሰይመዋቸዋል። ፕሮፌሰሩ ይህንን ያሉበትን ምክንያት ሲያስረዱ “የተማረ ዜጋ ብቻ ነፃ የሆነ ጠቃሚ ዜጋ ሊሆን መቻሉን ስለተረዱት ነው” ብለዋል።
(ኢስት አፍሪካን ስታንዳርድ እ,ኤ,አ ግንቦት 31/1967)
~
…………* ” አህጉር አቀፍ ጭቅጭቆች ሲነሱ ለሰው_ልጅ ደህንነት ለማስገኘት በፈቃደኝነት አስታራቂ በመሆን……ለአልጄሪያ; ለሞሮኮ; ለኮንጎ; ለቬየትናም; ለቢያፍራ እና ለቼኮዝላቫኪያ; ሲሉ ዓለምን በሰፊው ጎብኝተዋል። ጃንሆይ ሕይወታቸውን ለሕዝባቸው የመደቡ መሪ ናቸው። ሀገራቸው ወደፊት ብሩህ ዕድል የሚጠብቃት መሆኑ የማይቀር ነው ብለው ያምናሉ። ሥራቸው ሁሉ እርምጃውን ለማፋጠንና ለማጠናከር ተብሎ የታሰበ ነው; ዘመናዊቷን ኢትዮጵያም ያበጇት እሳቸው ናቸው። ምናልባትም በሀገራቸው ታሪክ ውስጥ “የአገራችን_አባት” የሚል ስም ይሰጣቸዋል።”
የኢጣልያው መጽሔት ቴምፖ እ,ኤ,አ የካቲት 21/1970)
~
………* ” የግርማዊ ንጉሠ_ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የካፒታሊስትና የኮሚኒስት ሀገሮችን መጎብኘት ዋናው ምክንያት ወደማንኛውም ወገን ሳታዘንብል በገለልተኝነት ላለችው አገራቸው የልማት ሥራ; የገንዘብ ድጋፍ; የሚሊተሪና የቴክኒካል እርዳታ ለማግኘት ነው።”
(ኢስት አፍሪካን ስታንዳርድ እ,ኤ,አ ግንቦት 31/1967)
~
………” ግርማዊ ንጉሠ_ነገሥት ከዙፋናቸው በወጡ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሞላ ጎደል ብቸኛና መንገድም የሌላት አገር ሆና……በኢጣሊያ; በእንግሊዝና በፈረንሳይ ቅኝ_ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ከባሕር ተቋርጣ ነበር። ኢትዮጵያ የነበራት እውነተኛ መውጫ በር ጠቅላላ ንብረትነቱ የፈረንሳይ በነበረ ባቡር አማካይነት በቀድሞይቱ የፈረንሳይ ሱማሌ በኩል ነበር። ስለዚህም መንገዶችና የአየር አገልግሎቶች ባልነበሩበትና……የቴሌግራፍ; የቴሌፎንና የፖስታ አገልግሎት ገና በመጸነስ ላይ በነበረበት ወቅት የሀገር ውስጥ መገናኛዎች የጭነት ከብቶችና የእግር መልዕክተኞች ብቻ ነበሩ። ይልቁንም በንጉሠ_ነገሥቱ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ችሎታ ኢትዮጵያ በቀይ_ባሕር በኩል ያላትን የጥንት በር አስመልሳ አሁን ዘመናዊ የሆኑ ሁለት ታላላቅ የባሕር ወደቦች አሰርታለች። የማመላለሻ መንገዶችም ቢሆን በንጉሠ_ነገሥቱ ጥረት ከዳር እስከ ዳር ግዛት የዘለቁ ሲሆን……ክረምት ከበጋ የሚያገለግሉ አውራ ጎዳናዎች ከሞላ_ጎደል ታላላቅ ከተሞችን ያገናኛሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገሪቱ ውስጥ አርባ የሚያህሉ ሥፍራዎች; በሦስት አህጉሮች ውስጥ ደግሞ አስራ ስድስት ሀገሮችን በማገናኘት ዘውትር ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጣሉ……”
(ዴይሊ ያሚዩሪ ጃፓን እ,ኤ,አ ኅዳር 3/1971)

Filed in: Amharic