>

....እነዚህ ፓርቲዎች የኢህአዴግ ቀለብተኛ ናቸው!!!" (ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና)

“….እነዚህ ፓርቲዎች የኢህአዴግ ቀለብተኛ ናቸው!!!”

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና 
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር
 
ኢህአዴግ ባለፉት 27 ዓመታት  ያደራጃቸውን  ፓርቲዎች ይዞ መቀጠል ሲያቅተው፣ ሌላው የኢህአዴግ ክንፍ ደግሞ ይዞ ለመሄድ እየሞከረ ይመስላል” –
•  ኢህአዴግ ባለፉት 27 ዓመታት  የራሱን ፓርቲዎች ሲያደራጅ ነው የኖረው፡፡ በእርሱ አደራጅነት ከቅንጅት የወጡ ከእኛም ፓርቲ ተገዝተው የሄዱ እንዲሁም ከሌሎችም እንደዚያው አሉ፤
•  መንግሥት ላለፉት 27 ዓመታት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ብሎ ከሁለቱም ያልሆነ አስተዳደሩን በጉልበት ህዝቦች ላይ ሲጭን ነበር፤ የአንድ ፓርቲ ገናናነትን ፈጥሮ ሲያፍን፣ መጠነ ሰፊ የሆነ ዘረፋን ሲያካሂድ ቆይቷል፤ ከዚህ አንጻር በዋናነት ተጠያቂው እርሱ ነው።
•  በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መንግሥታዊ ሰርዓት አልፈጠሩም፤ ፌዴራሊዝም አሉ ግን እሱም ቢሆን ሀቀኛ ፌዴራሊዝም ሳይሆን የነበረው የሞግዚት አስተዳደር ነው።
• አሁን የምናያቸው ብዙ ችግሮች የተፈጠሩት በዚህ ምክንያት ነው። እዚህ ላይ ግን ሌሎች ኃይሎች ደግሞ የራሳቸው ስግብግብነት ገኖባቸው ያበረከቱት አስተዋጽዖ የለም ማለት አይደለም።
•  አሁን ላይ የኢህአዴግ መዋቅር እንደ መዋቅር አንድ ላይ ወደፊት መሄድ አልቻለም። መጨረሻቸውን አናውቅም።
•  ምንልባትም ከዚህ የበለጠ ውዝግብ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ አልያም በስምምንት መፋታት ሊኖር ይችላል።
•  አሁን ዋናው ጉዳይ የእኔ ፓርቲ ስልጣን እንዲይዝ ማድረግ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ፈጣን ምላሽና ለውጥ እንዲያገኝ ማስቻል ነው።
•  አንዳንድ ሰዎች ምርጫ አይቻልም የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። እኔም ቢሆን አስቸጋሪ እንደሚሆን እገነዘባለሁ። ነገር ግን ከዚህ የተሻለ ጊዜ ሊመጣ ይችላል ወይ ? የሚለው ደግሞ መመለስ ያለበት ጥያቄ ይመስለኛል።
•  ከዚህ የተሻለ ሁኔታ ይፈጠራል ብለን ምርጫው ይዘግይ የምንልበት ምክንያት የለንም። የመንግሥት መዋቅርም ሆነ ኢህአዴግ እንደ ገዥ ፓርቲ ችግር ውስጥ ገብቷል።
•  ውህደት የፈጠረው ኢህአዴግ ጥንካሬና ህወሓት እስከምን ለመሄድ ነው ስትራቴጂ የነደፈው የሚለውን አናውቅም።
• ኢህአዴግ ከፈረሰ በኋላ አሁን ያለው መንግሥት ህጋዊ ስለመሆኑም እየተጠራጠረና አላውቅም እስከማለት እየሄደ ነው፤
•  ለማዕከላዊ መንግሥት አልገዛም፤ አልቀበልም ማዕከላዊ መንግሥት ህጋዊ አይደለም ማለት በእርግጥ ይችላል፡፡ ግን ምን ያህል ርቀት አብረው ይጓዛሉ የሚለውን የሚመልሰው ጊዜ ብቻ ነው።
•  የእኔ እምነት በተያዘለት ጊዜ ምርጫው መካሄድ አለበት የሚል ነው። ይህንን ለማለት ያስገደደኝም ሁለት ትላልቅ ስጋቶች ያሉኝ በመሆኑ ነው።
•   አንደኛው ለውጥ የሚባለው ነገር ወደ ታች አልወረደም፤
•   ሁለተኛው የቀበሌና የወረዳ ምርጫዎች እስከአሁን አለመካሄዱ ህዝብ ባልመረጣቸው ሰዎች እየተመራ ባለበት ወቅት ምርጫ ማራዘሙ የከፋ ችግር ያመጣል ብዬ ስለማስብ ነው።
•  የተለያዩ ማህበረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር የሚያስችላቸውን መሪዎቻቸውን ከመረጡ በኋላ በኢህአዴግ ውስጥ ያለው ችግርም ሊረግብ ይችላል።
•  የሚፈጠረው መንግሥትም ምናልባት አሁን ካለው መንግሥት የተሻለ ውክልና፣ ድጋፍና ተቀባይነት ሊያገኝ ስለሚችል ችግሩ ወደ መርገቡና ወደ ድርድር ሊሄድ ይችላል። አሁን ያለው የኢህአዴግ መንግሥት ነው። እሱ ደግሞ ገመድ ጉተታ ውስጥ ገብቷል። ችግሩ ይህ ነው።
•  እኔም ከዚህ ታሪካቸው ተነስቼ ነው እነዚህን ፓርቲዎች የኢህአዴግ ቀለብተኛ ናቸው ወደሚለው የሄድኩት
•  ገዥው ፓርቲ በብሔራዊ መግባባት አቅጣጫ የአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች እንዲሰባሰቡ እንዲደራደሩ ማድረግ ያለበት እርሱ ነው። ብሔራዊ መግባባትና የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ለውጥም ሊመጣ ይችላል ብዬ አስባለሁ።
•  ኢህአዴግ ባለፈው ምርጫ በምን መልኩ ስልጣኑን እንዳራዘመ እየታወቀ አሁንም ምርጫው ይራዘም ማለት ላልፈለግነውና ላልጠበቅነው ችግር ሊያስገባን ይችላል።
•  ወጣቱ ለውጥ የሚፈልገው አሁን ነው። የምርጫውን መራዘም አልታገስም ካለ ይህ ወጣት ማነው ሊያሳምነው የሚችለው? ስለዚህ ኢህአዴግ በዚህ ጉዳይ ላይ ደጋግሞ ማሰብ አለበት።
•  ምርጫውን ነፃና ፍትሐዊ እንዲሁም ሰላማዊ ማድረግ የአንድና የሁለት ፓርቲዎች ፍላጎት ሳይሆን ገዥው ፓርቲም መንግሥትም ተጽዕኖ ፈጣሪ የፖለቲካ ኃይሎች እንዲሁም ማህበረሰቡ ሁሉም የራሱን ድርሻ መወጣትና የቤት ሥራውን መሥራት መቻል አለበት። ምንም እንኳን ዋናው ቁምነገር መንግሥት እጅ ላይ ያለ ቢሆንም።
•  እኔ ማንም ይመረጥ ማንም ብሔራዊ አንድነት መንግሥት ቢሆን ይመረጣል። ዝም ብሎ 50 በመቶ አግኝቻለሁ በሚል አገርን እንመራለን የሚለው ነገር ዋጋ ያስከፍላል። ስለዚህ የእኔ ራዕይ ለአምስቱ መሸጋገሪያ ጊዜ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ቢቋቋም ይሻላል።
•  አሁንም ደግሞ እናገራለሁ አገሪቷና ህዝቧ ወደ ብሔራዊ መግባበት ካልገቡና ፖለቲካዊ ጨዋታው ካልተለወጠ ኢትዮጵያ ከዚህ ጣጣ አትወጣም።
•  በዋናነት የዚህ ስርዓት ፈጣሪዎችና እዚህ ያደረሱት በስርዓቱም ህዝብን የበደሉና ያሠሩ የዘረፉና ያዘረፉ ኃይሎች ናቸው ተጠያቂዎቹ። መቼ የሚለው ግን መልሱ ከባድ ነው።
•  የመጠላለፍ ፖለቲካን መተውና እነዚህን የማስተካከል ስራ ላይ ቢያተኩር ኖሮ የሚደርሱት ችግሮች ይቀንሳሉ የሚል ነገር አለኝ።
•  ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥትን የምመክረው ፖለቲካችንን ለማስተካከል ትኩረት ሊሰጥ ይገባል።
•  በዋናነትም ለአገራችን ብሄራዊ መግባባት መፈጠር የበኩሉን ሚና መጫወት ይጠበቅበታል።
ምንጭ;-  አዲስ ዘመን 
Filed in: Amharic