>

መረጃ ጠቅሼ ያቀረብሁት ታሪክ ለኦነጋውያንና  አፍ ነጠቅ ደቀ መዝሙራኖቻቸው ምቾች ነስቷቸዋል!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

መረጃ ጠቅሼ ያቀረብሁት ታሪክ ለኦነጋውያንና  አፍ ነጠቅ ደቀ መዝሙራኖቻቸው ምቾች ነስቷቸዋል!!!

አቻምየለህ ታምሩ
1ኛ. በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የእስልምና አካባቢያዊ መንግሥት በመመስረት የሙስሊም ሱልጣኔት ያቋቋሙ አማሮች መሆናቸውን፤
2ኛ.  የሸዋ የሙስሊም ሱልጣኔት የአማራ የሙስሊም መንግሥት መሆኑን፤
3ኛ. በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሸዋ ወደ ምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በመሄድ የአዳልን የሙስሉም ሱልጣኔት ያቋቋሙት የኡመር ወላስማ ዘሮች የአማራ ተወላጅነት ያላቸው መሆኑን፤ እና
4ኛ. የነ አሕመዲ ጀበልን «አባት» የጅማውን ንጉሥ ቀዳማዊ አባ ጅፋርን እስልምና እንዲቀበሉ ያደረጉት የጎጃምና የጎንደር አማራ ሙስሊሞች መሆናቸውን  የጅማውን ዘውዳዊ መንግሥት ታሪክ የጻፉትን የአባ ጅፋር ልጅ የአባ ጆቢርን ድርሳን ጠቅሼ ያቀረብሁት ታሪክ ለኦነጋውያንና ለአሕመዲን ጀበል  አፍ ነጠቅ ደቀ መዝሙራን ምቾች የሰጣቸው አይሰምስልም።
እነዚህ የአሕመዲን ጀበል አፍነጠቅ ደቀመዛሙርት ከኦነግና ከወያኔ የወረሱት አንድ  የድንቁርና ትምህርት አላቸው። ይህም የቀሰሙት የድንቁርና ትምህርታቸው ማናቸውንም እንዲሆን የማይፈልጉትን ነገር «ተረት ተረት»፤ «የደብተራ ታሪክ» ብሎ መፈረጅና ማብጠልጠል ነው።
እነዚህ የማይጥማቸውን ነገር ሁሉ ሳያነቡና ሳይገባቸው ወያኔና ኦነግ በሰጧቸው የድንቁርና ጥበብ እየተመኩ «ተረት ተረት»፤ «የደብተራ ታሪክ» ወዘተረፈ… እያሉ የእውቀት ጾመኛነታቸውን በስድብ ሲደግፉ የሚውሉት አፍ ነጠቆች ስለማያነቡና አጥልቀው ማሰብ ስለማይችሉ እኛ የኢትዮጵያን ምንጮች ስንጠቀም የማይጥማቸውን እውነት ጥላሸት ለመቀባት «ተረት ተረት»፤ «የደብተራ ታሪክ» ወዘተረፈ.. እያሉ መሳደባቸውን እንጂ  እነሱ  የታሪክ አዋቂ አድርገው የሚቆጥሯቸው መምህሮቻቸው [ ኡስታዞቻቸው  ላለማለት ነው] ሳይቀር  ታሪክ ያሉትን ሲደርቱ በዋናነት እዚህም እዚያም የሚጠቃቅሷቸው «ተረት ተረት»፤ «የደብተራ ታሪክ» ወዘተረፈ.. እያሉ በባዶ እጃቸው ሊያጣጥሏቸው የሚሞክሯቸውን የኢትዮጵያ ምንጮች መሆኑን ዘንግተውታል።
የኢትዮጵያን  የታሪክ ምንጮች ኡስታዞቻቸው ሲጠቋቸው ትክክለኛ የታሪክ ምንጮች፤ እኛ  ስንጠቅሳቸው ግን  «ተረት ተረት»፤ «የደብተራ ታሪክ» የሚሆኑት በእውቀት  ጾመኞችና በጥላቻ አረንቋ በሰጠሙ መንጋዎች  ሚዛን ብቻ ነው።
 ተሳዳቢዎችን የሚያሰማሯቸው ዋናዎቹ ኦነጋውያን ቀድሞውንም የኦነግ ባለጉዳይ እንጂ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሌላቸው የአማራ ሙስሊሞችን የሚፈልጓቸው ለኦነግ አላማ ጭዳነት እንጂ የሃይማኖት ወንድሞቻችን ናቸው ብለው አይደለም። ኦነጋውያኑ በታሪኩን የሚኮራውን  የአማራ ሙስሊም አይፈልጉትም። ለዚህም ነው በየሚኖሩበት የውጭ አገር ሁሉ «በኦሮሞ መስጂድ እንጂ በአማራ መስጂድ እንዳትሰግዱ» እያሉ ተከታዮቻቸውን ሲያሰለጥኑ የሚውሉት።
የሆነው ሆኖ የትናንትናውን ታሪክ  በሚመለከት የውሸት ታሪክና የተዘረፈ ታሪክ እያሉ ሲያላዝኑ ለሚውሉ የአማርኛ ስም [አረብ ገባ] የሚል ስም ባለው የአርጎባ ቋንቋና አማርኛ መካከል ስላለው ግንኙነት ችሎታው፣ ጥሞናውና ትግስቱ ካላቸው የሚከተሉትን ምንጮች ያንብቡ፤
1. “Argobba is  a dialect of Amharic”
Soruce Wetter, A. (2006). The Argobba of Tollaha -a comparative overview [A].In S. Uhlig (ed.), Proceedings of 15thInternational Conference of Ethiopian Studies [C]. Verlag: Harrassowitz Verlag,  Page;  899-907 and  Bender, M. L. et al. (1976)  Language in Ethiopia [M]. London: Oxford University Press; Page 30.
2. “Amharic does have one quite divergent dialect: Argobba. This is best considered as a ‘Muslim dialect.”
Source:  Bender, M. L., & Fulass, H. (1978). Amharic verb morphology. African Studies Center, Michigan State University; Page 5.
3. “Argobba and Amharic are dialects of one another, not independent languages.”
Source: Zelealem, L. (1994).  Argobba -The people and the Language [J]. S.L.L.E. Linguistic Report, 22:  Page 1-13.
4. “… while Argobba has certain features found in one or another South Ethiopian language, it is the most closely related to Amharic. It is even safe to say that Argobba presents an older stage of Amharic. And hence Argobba is the dated form of Amharic”
Soruce:   Leslau, W.(1978).  Argobba Vocabulary[M]. Instituto per L’orente VIA A. Caroncini,19; Page 2.
5. “The mutual intelligibility combined with many common features between Amharic and Argobba leads me to the conclusion that Argobba is an Amharic dialect.”
Source:  Leslau, W.(1997).  Ethiopic Document: Argobba Grammar and Dictionary [M]. Wiesbaden: Harrassowitz; Page 131.
Filed in: Amharic