>

የአሜሪካ ዜግነቱን በራሱ ፈቃድ ለመተው የፈለገ ግለሰብ ከ5 - 6 ወር መጠበቅ አለበት!!!"  (በሳሙኤል ሃ)  

የአሜሪካ ዜግነቱን በራሱ ፈቃድ ለመተው የፈለገ ግለሰብ ከ5 – 6 ወር መጠበቅ አለበት!!!” 

በሳሙኤል ሃ  
የምርጫ ቦርድ አካሔድስ ማንን ለመጥቀም ይሆን ?
 
– የሌላ ሀገር ዜግነት ለማግኘት ያመለከተበት ማስረጃ ማቅረብ
– አሜሪካ ኤምባሲ በአካል በመገኘት ማመልከት
– በአሜሪካ መንግሥት የተዘጋጁ ቅጾች መሙላት
– የመጨረሻ ዓመት የታክስ ቅፅ መሙላት
– ያለፉት አምስት ዓመታት ግብር ታክስ የሞላ መሆን
– የፋይናንስ ወንጀሎች ማስከበሪያ መረብ ወይም Financial Crimes Enforcement Network በኩል የ Foreign Bank and Financial Account ፎርም 114 መሙላት
– ለቃለመጠይቅ ቀጠሮ ማስያዝ
– በተለያዩ ቀናት የሚደረጉ ሁለት ቃለመጠይቆች ላይ መገኘት
– ዜግነቱን መተው መወሰኑን በቃለ መሃላ መግለጽ አለበት
    ከዚያ ኤምባሲው ቅጾችን እና ቃለመሃላውን አያይዞ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይልካል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ሰነዶቹን ከመረመረ እና ግለሰቡ በታክስ ክፍያ እና ሌሎች ወንጀሎች በአሜሪካ መንግሥት የማይፈልግ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ዜግነቱን ማጣቱን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት Certificate of Loss of Nationality (CLA) DS-4083 እንዲሰጠው ውሳኔ ያስተላልፋል ።
    ውሳኔውንም ለኤምባሲው መልሶ ሲልክ ግለሰቡ ሰርተፊኬት ያገኛል። አሁን ባለው አሰራር የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ሰርተፊኬቱን ለማጽደቅ! 5 ወራት ጊዜ ይፈልጋል ። ስለዚህም ዜግነት የማጣት ሂደቱ ተጀምሮ እስኪያልቅ ከፈጠነ ! 6 ወራት የሚፈልግ እንደሚሆን ይገመታል። በአንዳንድ ሃገሮች እስከ 15 ወራት እንደሚፈጅ ይታወቃል።  የአሜሪካ ዜግነቱን በፈቃዱ የሚተው ግለሰብ በአሜሪካ የመኖር እና የመስራት መብትን ወዲያውኑ ያጣል።በፈቃዱ የተወ ግለሰብ እንደገና ተመልሶ የአሜሪካ ዜግነትን ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው ፣ ይሁንና የመስሪያ ፈቃድ ለማግኘት እንደማንኛውም የውጭ ሀገር አመልካች ማመልከት እና መጠበቅ ይችላል ።

የምርጫ ቦርድ አካሔድስ ማንን ለመጥቀም ይሆን ?

ሕግ ይከበራል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ምርጫ ቦርድ ከቀኑ አይዘልም ያለው የግንቦቱ ምርጫ ለነሐሴ ተላልፏል ተብለን ነበር ። አሁን ደግሞ የነሐሴው ምርጫ ወደ ጥቅምትና ሕዳር 2013 ሊዘል ይችላል። ይህቺ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን  ???
ሐገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሔድበት ቀን አልተቆረጠለትም የሚል አለማማጅ ፕሮፓጋንዳ ከምርጫ ቦርድ በኩል ተለቃለች።ሕግ እየጣሱ በግልጽ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ከሕግ አግባብ መጠየቅ ሲኖርበት ገና ምርመራ አለመጀመሩ የቦርዱን ንዝሕላልነት ያሳያል። የምርጫውን ክራይቴሪያ ያላሟሉ ግለሰቦች ዶክመንታቸውን አስጨርሰው እስከሚመጡ ምርጫ የለም እየተባለን መሆኑን ስንቶቻችን ተገንዝበናል ???
የሐገሪቱ ሕገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ምርጫው መፈጸም ሲገባው በቀነ ቀጠሮ መንዘላዘል ከሕግ አንፃር የሚያስነሳው ውዝግብ ማን ሊፈታው ይችላል የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ ምርጫ ቦርዱ ለተወሰኑ አካላት ጥቅም ሲል በውይይት ሽፋን የሕዝብን መብትና ሕግን እየደፈጠጠ ነው። የምርጫ ቦርድ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ? ልብ ያለው ልብ ይበል !!!
National Electoral Board of Ethiopia- NEBE -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
Filed in: Amharic