>
5:13 pm - Tuesday April 19, 7396

የኮሮና ቫይረስን በተመለከት በጀርመን ካለው ቴክኒካዊ ተሞክሮ በመነሳት ጥቂት ልበላችሁ!!! (ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ)

የኮሮና ቫይረስን በተመለከት በጀርመን ካለው ቴክኒካዊ ተሞክሮ በመነሳት ጥቂት ልበላችሁ!!!

 ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ 
የተከበራቹህ ወገኖች
የኮሮና ቫይረስ በተመለከት ከጀርመን ያለውን ቴከኒካዊ ልምድና አስተያየት በማማከል ይጠቅማል ያልኩትን፣ ከዚህ በፊት ከተነበበው ወይም ክሚታወቀው በተጨማሪ ለማገናዘቢያ ይሆናል በማለትና በማሰባስብ እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራልሁ።
ኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ ስጋቶችም እየጨመሩ ይገኛሉ። መደናገጥ፣ ፍርሃት እና ያለቅጥ መረበሽ ባያስፈልግም። አውሮፓ ውስጥ መንግስት አስፈላጊውን ቁጥጥሮች እና እርምጃዎችን ጀምሮዋል፣ መስሪያ ቤቶች፣ ተቋማት እና ኩባኛዎችም የመከላከያ እቅድ እያወጡ ነው። ስዊዘርላንድ ከአንድሺ ሰው በላይ መሰበሰበን የሚከለክል ህግ በማውጣት ጂኔቫ ላይ የሚካሄደው የመኪና ኤግዚቢሽን ተከልክሏል። ፈረንሳይም ከ5ሺ በላይ ሰዎች ያሉበት ዝግጅቶችን አግዳለች። እዚህ ጀርመን በርሊንም ታዋቂው ወደ መቶ ሃምሳ ሺ ጎብኚዎች የሚጠበቅበት ከ180 አገሮች የሚሳተፉበት የቱሪዝም ትርኢት (ITB – Wolds leading Travel Trade Show) ታግዷል። በጀርመን የኢንፊክሽን ህግ መሰረት እገዳዎች ተግባራዊ ከሆኑ በሲቪል መብቶች እና በግለሰብ መብቶች ለማህበረሰቡ ደህንነት ሲባል ገደብ ሊጣልባችው ይችላል።
በሽታው በወጣት ፣ በጤናማ ሰዎች ላይ ቀለል ያለ ነው። ኢንፌክሽኑ እስካሁን ድረስ በልጆች እና በጉርምስና ዕድሜ ላይ ባሉ ላይ በብዛት አይታይም። ቀዳሚነት የሚሰጥው በእድሜ የገፉት እና ደካማ የበሽታ መካላከል በቃት ያላችውን መክላከሉ ላይ ነው።
ቫይረሱ በቀላሉ የሚተላልፍ እና ደካማ የበሽታ መከላከል ይዘት ያላችውን ለከፍትኛ የህይወት የጤና ስጋት የሚዳርግ ሊሆን ይችላል። ከሌሊቹ ቫይረሶች የሚለየውም ቫይረሱ በጥቂት ሰአታት ከአየር ጋር ሲገናኝ የሚጥፋ ሳይሆን እስከ 9 ቀናት ድርስ ኢንፊክሽኑን እንደያዘ የሚቆይ በመሆኑ ነው። ለምሳሌ አንድ ቫይረሱ ያለበት ሰው አፍንጫውን ነክቶ አንድን በር ወይም የደርጃ መደገፊያ ቢነካ ቫይረሱ ለቀናት እዝው ላይ ሊቀምጥ ይችላል። ብዙ ሰው መያዙንም ላያውቅ ይችላል። በጀርመን በቲዩቢንገር ከተማ ውስጥ በዚህ ኢንፌክሽን የተያዘው ሀኪም ለብቻው ተነጥሎ በተቀመጠበት ሆስፒታል „ደር ሽፒግል“ (der Spiegel) የተባለው ሚዲያ ኢንተርቪው አድርጎት ምንም እይነት ህመም ወይም ምልክት እንደሌለበት፣ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ እና ከጣሊያን እረፍት ስትመለስ ያስያዘችው ልጁም ጉሮሮዋን ከማሳከክ በላይ ሌላ ምልከት ወይም ህመም እንዳልኖረባት ነው የገለፀው።
ኢንፌክሽኑ መድሃኒትና ክትባት ባይኖረው የአስቀድሞ መከላከያ ቅድመ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላለመያዝ፣ ከተያዘም በቀላሉ እንድማንኛውም በትንፋሽ ተላለፊ በሽታዎች ለመቋቋም የሚያስችል ቁመና መፍጠር ይቻላል።
የኢንፌክሽን ተላላፊ በሽታዎችን ማስቀረት ወይም ማዝገም ይቻላል። ቫይረሶች ወይም ባክቴሪያዎች ብዙውን ጊዜ በሳል ወይም ነጠብጣብ ኢንፌክሽን ይተላለፋሉ። የበሽታው አምጪ ቫይረሶች በማስነጠስ ወይም በመጨባበጥ ወደ ሌሎች ይተላለፋሉ። ስናስነጥስም በብዙ ሚሊየን የሚቁጠር ቫይረሶቭ አፍንጫችንን ለቀው ወድ አየር ይወነጨፋሉ። በአለም ላይ በየቀኑ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀላል እስከ ከባድ ጉንፋን ይያዛሉ።
ኮሮናም ሆነ ሌላ ቫይረስ ወይም ጉንፋን እንዳይዘን ዋናው መክላክያ እንደሚከተሉት ማየት ይቻላል ->
• ሰዎች በብዛት የሚሰባብስቡበትን ቦታዎች፣ መተፋፈግ ካለበት መራቅ ወይም ዝግጅቶችንም ካዘጋጀን ይህንን ከግንዛቤ ማስገባት
• እጅን በሳሙና እና በውሃ በተገቢው ደጋግሞ መታጠብ
• ከመጸዳጃ ቤት በፊት እና ከመፀዳጃ ቤት በኋላ የእጅን ንፅህና ማረጋግጥ
• አፍንጫ እና ፊትን በእጅ በተደጋግሚ አለመነካካት
• ወጥ ቤት እና መታጠቢያ ቤቱ ንጹህ መሆናቸውን ማረጋገጥ
• የወረቀት ሶፍት መሃረቦችን አንድ ጊዜ ብቻ መጠቀም
• ከመጨበጥ ይለቅ በፈገግታ እና የአንገት ሰላምታ ማስቀደም
• በርን፣ የሊፍት በተኖችን ቢቻል በክንድ ለመክፈት፣ ለመግፋት፣ ለመጫን መሞከር
• ካስነጠሱ በገዛ እጅጌ ውስጥ ማሳል
• በሚያስልዎት ጊዜ ከሰዎች ለመራቅ መሞከር ቢያንስ 1.5 ሜትር
• ከታመሙ ጋር አካላዊ ግንኙነት አለማድረግ
• ከአየር ማቀዝቀዣ ከቪንትላይዚሽን ከመጠቀም መቆጠብ
• ክፍሎችን ንፁህ አየር ማናፈስ ፣
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳል ፡፡ ጤና ተኮር የሰውነት ማጎልመሻ የሰውነታችንን መከላከያዎች ይጠነክራል። በስፖርት የተገነባ ሰውነት የመከላከል አቅሙ ከፍተኛ ነው።
• በቀን ለተወሰን ደቂቃ ቢያንስ 15 ደቂቃ ያልተጋነነ ብርታት ተኮር የሆን ንቅናቄ መድረግ
• ስንራመድም በቀስታ ሳይሆን ሊያልበን በሚያስችለን መልኩ ረጃጅም እርምጃዎችን ማስቀደም
• በቂ እንቅልፍ ማግኘት
• የአየር ሁኔታን የሚመጥን ልብስ መልበስ (በተለይም ቫይረሱ ቅዝቃዜ ስለሚመቸው እና ለመስፋፋት እድል ስለሚሰጠው)
ጤናማ እና ሚዛናዊ የሆነ አመጋገብ ሰውነታችንን ፀረ-ቫይረስ ተፅእኖ እንዲኖረው የሚስችል የመከላከል አቅም ይገነባል።
• ቫይታሚን ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ፣ ኦሜጋ 3 ያለበትን መመገብ (ለምሳሌ አትክልቶች ፣ ፍራፍሬዎች ፣ ሎሚ፣ አሳ፣ ዝንጅብል፣ ፋሳሽ በብዛት መውሰድ ወዘተ.)
አካላዊ ብርታት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ብርታትን (Resilience ) ለማጠናከር፣ ከመደናገጥ እና ፍራቻ መራቅ በተለይም የሚያሸብሩ የማሴር ቲዎሪዎችን ቢያንስ በዚህ ወቅት አለመከታተል።
የህክምና ባለሙያዎች የበለጥ ሙያዊ ምክር ሊሰጡበት ይችላሉ። በዚህ አጋጣሚ በበርሊን የሜዲካል ዶ/ር በላይ ጥላሁንን ለፅሁፉ ለሰጡኝ ሙያዊው ግምገማው አመሰናለሁ።
Filed in: Amharic